Saturday, June 7, 2014

የግንቦት 20 ፍሬዎች

የግንቦት 20 ፍሬዎች
ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥንት ሰዎች መገኛና የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት እንደሆነች ተደጋግሞ የተረጋገጠ እውነታ ነው። በአህጉራችን አፍሪካ ረዥም የነፃነት ታሪክ ያላት ሀገርም ነች። ለውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ ሰጥታ የማታውቅ ሀገር በመሆኗ በጭቁን ህዝቦች ዘንድ የነፃነትና የአይበገሬነት ተምሳሌት ሀገር ተደርጋ ትወሰዳለች- ኢትዮጵያ።
በአንድ ወቅት ከዓለማችን ገናና ስልጣኔዎች መካከል አንዷ የነበረችው ሀገራችን ስልጣኔዋን ጠብቀው መቆየት ባልቻሉ ገዢዎቿ የተነሳ ቁልቁል ተንደርድራ በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የዓለማችን ድሃና ኋላቀር ከሚባሉት ሀገራት መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለመሆን በቃች። ጥንታዊ የስልጣኔና የነፃነት ምስሏ እየደበዘዘና ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እይታ እየራቀ መጥቶ የኋላቀርነት፣ የረሃብና የስደት ተምሳሌት ሆነች። ዜጎቿ ያልተነካና እጅግ ለም የሆነ ሰፊ የእርሻ መሬት እያላቸው ለልመናና ምፅዋት እጃቸውን ዘረጉ።
በእነዚያ ዘመናት በአገራችን የሕግ የበላይነት፣ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ህዝቦች እንዲሁም የቋንቋዎችና የሃይማኖት እኩልነት፤ የእምነት ነፃነት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት፣ የመደራጀት መብት፤ ወዘተ የሚባሉት ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተረግጠውና ታፍነው ዜጎች በጸረ ዴሞክራሲ አገዛዝ ሲማቅቁ ነበር። በስርዓቱ የተማረረው ኢትዮጵያዊ ፀረ ፊውዳላዊ ስርዓት ትግሉን ከአራቱ የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በማጧጧፍ የፊውዳል ስርዓቱን ከኢትዮጵያ ገፅ  አስወገደ። ህዝቡ ባካሄደው አመጽ የንጉሱ ስርዓት ማስወገድ ቢችልም የተደራጀ ፖለቲካዊ አመራር ስላልነበረው በረዥሙ ያነገበውን ግብ ሳያሳካ ድሉን በወታደራዊ መኮነኖች ስብስብ ተነጠቀ። ሀገሪቱም ከአንድ አምባገነን ስርዓት ወደ ሌላው ዓይነት የከፋ አምባገነን ስርዓት ተሸጋገረች።
በደርግ ዘመን የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች በአስከፊ ሁኔታ ታፈኑ። ዜጎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ተጨፍጭፈዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ትቅደም” በሚል መፈክር ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር በመክተቱ ኢኮኖሚው ደቅቋል። አርሶ አደሩ የምርቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን ነጋዴውም ዕውቀቱንና ገንዘቡን በነፃነት ማንቀሳቀስ እንዳይችል  የአርሶ አደሩን ምርት በርካሽ ዋጋ እየገዙ በተሻለ ዋጋ የሚሸጡ መንግስታዊ የንግድ ተቋማት ተፈጠሩ። በአርሶ አደሩ ላይ የወረደው ክልከላ በርካሽ ዋጋ እንዲሸጥ ብቻ ሳይሆን ከእነዚህ የአፈና መዋቅሮች ውጭ ለማንም ባለሃብት መሸጥ እንዳይችል ጭምር ነበር። ነጋዴውም ከ500ሺህ ብር በላይ ሀብት እንዲያፈራ አይፈቀድለትም። ከተቀመጠው  መጠን በላይ ገንዘብ ያፈራ ነጋዴ ገንዘቡ በቀጥታ በመንግስት ይወረሳል። በነዚህና መሰል አሳሪ ህጎች የተነሳ የሀገሪቱ አጠቃላይ ዕድገት የማሽቆልቆል ጉዞው ተፋጠነ፡፡
በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ በተከታታይ ዓፈናና ጭቆና የተማረረው የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግ ስርዓትን አስወግዶ በምትኩ ዴሞክራሲያዊና ህዝባዊ ስርዓት ለመገንባት ከየአቅጣጫው ዳግም ለህዝባዊ ዓመፅ የተነሳሳው። ፋሽስቱን የደርግ ስርዓት በመገርሰስ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ማቋቋምና የሀገሪቱ ህዝቦችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ግባቸው ያደረጉ ህዝባዊ ሃይሎች በፈተና ውስጥ ሆነው መደራጀታቸውን ቀጠሉ፡፡ የዓላማቸውን ትክክለኛነት የተገነዘቡ  ሃይሎችም ከየአቅጣጫው እየጎረፉ ህዝባዊ ማዕበል ፈጠሩ። በኢህአዴግና በአባል ድርጅቶቹ መሪነት በኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እልህ አስጨራሽ ትግል የደርግ ስርዓት ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ።
ደርግን በግንባር ቀደምትነት ታግለው የጣሉት ህዝባዊ ኃይሎች በግንቦት 20 ማግስት ታግለን ያገኘነውን ስልጣን እኛው እንያዘው ሳይሉ “የመንግስት ስልጣን ሉአላዊ ባለቤት ህዝብ ነው” ከሚለው የማይናወጥ መርሃቸው በመነሳት ሁሉም አካላት የተሳተፉበት ታሪካዊ ብሔራዊ ኮንፍረንስ በማካሄድ የሽግግር መንግስት በማቋቋማቸው የአዲሲቱ ኢትዮጵያ መፃኢ ጉዞ በአዲስ መሰረት ላይ ሊገነባ ቻለ። የደርግ ስርአት ሲወድቅ ሃገራችን እንደ ሶማሊያና ዩጎዝላቢያ ልትበታተን ትችላለች የሚለውም ስጋት በድል ታለፈ፡፡ የሽግግር መንግስቱ ሰላምና መረጋጋት የማረጋገጥ እንዲሁም ሃገሪቱን የዴሞክራሲዊ ህገ መንግስት ባለቤት የማድረግ ዋነኛ ተልእኮውን በማሳካት ስልጣኑን በህገ መንግስቱ መሰረት ለተመረጠው ህዝባዊ መንግስት በማስረከብ ታሪካዊ ሃላፊነቱን ተወጣ፡፡
ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስታችን ከጸደቀ በኋላም በርካታ የግንቦት 20 ፍሬዎች ባለቤቶች ሆነናል፡፡ በህገ መንግስቱ አማካኝነት የተቋቋመው የፌደራል ስርአታችን ብዝሃነትን በሚገባ በማስተናገዱ ዴሞክራሲያዊ አንድነታችንን በአስተማማኝ መሰረት ላይ በመገንባት ላይ እንገኛለን፡፡ የሃገራችን ትልቁ ጠላት የሆነውን ድህነትን ለማስወገድ እያካሄድን በሚገኘው ትግል በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ ለልማታችንና ለዴሞክራሲያችን ወሳኝ በሆነው ሰላምን የማረጋገጥ ጉዳይም ስኬታማ ሆነናል፡፡ የእነዚህ ስኬቶች ባለቤት ለመሆን የበቃነው በብዙ መስዋእትነት በተገኘው የግንቦት 20 ድላችን መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ስለሆነም 23ኛ አመት የድል ቀናችንን ስናከብር የአገኘናቸውን ስኬቶች በማጣጣም ለቀጣይ ስኬቶች እራሳችንን ይበልጥ በማዘጋጀት ሊሆን ይገባል፡፡
በአንድ ወቅት ታላቅ የነበረችውንና በሂደት በማሽቆልቆል ጉዞ ልትጠፋ የደረሰችውን አሁን ደግሞ ወደ ቀድሞ ስላጣኔ ቦታዋ ለመመለስ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰች ላለችው አገራችን  በየተሰማራንበት የስራ መስክ ተግተን ከመስራት ጎን ለጎን የሃገራችንን እድገትና ለውጥ የማይፈልጉ የውጭና የሀገር ውስጥ ተላላኪዎቻቸው ጉዟችን ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን መፍጨርጨርም በአግባቡ ተረድተን ልንመክተው ይገባል፡፡ በዚህ ጽሁፍ በግንቦት 20 ያገኘናቸውን ስኬቶች ከብዙ በጥቂቱ እንዲሁም ለቀጣይ ድል ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
1. የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስኬቶች
ያለፉት ገዥ ስርአቶች የሀገራችን ልዩ መገለጫ ብዝሃነት ሆኖ ሳለ የቡድን መብቶችን ረግጠው፣ የሃይማኖትና የፆታ እኩልነትን ነፍገው፣ በአጠቃላይ የሕዝቦችን ማንነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ እምነት ወዘተ  ክደው እንዳያብቡና እንዳይዳብሩ አድርገዋል። ይህ አስከፊ አገዛዝ ሊገረሰስ በተቃረበበት ጊዜ አደጋው ጫፍ ላይ ደርሶ ሊበታትነን እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ህያው ምስክር ነው።
የብሄረሰቦች እስር ቤት ሆና ለዘመናት ለኖረችው ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝቦቿ ሕልውና እውቅና፣ ለመብቶቻቸው መከበር ዋስትና የሰጠው ሕገ መንግስት የ1987ቱ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ሲሆን ያረቀቁትና ያፀደቁትም ራሳቸው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ናቸው። የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግስቱን ለማርቀቅ በቅድሚያ በየአካባቢያቸው በተዘጋጁት መድረኮች ሰፊ፣ ቀጥተኛና ተከታታይ ውይይቶችን አካሂደዋል። ወሳኝ በሚባሉቱ የሕገ መንግስቱ ይዘቶች ላይም ሕዝበ ውሳኔ ሰጥተዋል። ቀጥለውም የሕገ መንግስት አርቃቂ ጉባኤ አባላት እንዲሆኑ በዴሞክራሲያው መንገድ መርጠው በላኳቸው ተወካዮቻቸው አማካይነት ሕገ መንግስቱን አፅድቀዋል። ይህንኑ ባለቤትነታቸውን ለማረጋገጥም ነው የሕገ መንግስቱ መግቢያ “እኛ የኢትዮጵያ  ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች” በማለት የሚጀምረው።
የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለዘመናት ለታገሉላቸውና ከፍተኛ መስዋዕትነት ለከፈሉባቸው የፖለቲካ ጥያቄዎች በአስተማማኝ ሁኔታ መልስ የሰጠ ነው። ህገ መንግስቱ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ያለ ገደብ መከበሩን አረጋግጧል። ይህ ሕገ መንግስታዊ መብት አንዳንድ ወገኖች እንዳሉት ሀገሪቱን ለመገነጣጠል ሳይሆን በሕዝቦች መከባበርና መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተች አዲሲቷን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ዋና መሰረት ሆኗል። የህገ መንግስቱ አላማ መበታተን ሳይሆን በአገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያው ማህበረሰብ መገንባት እንደሆነ በህገ መንግስቱ መግቢያ በግልጽ መቀመጡ የዚሁ ማረጋገጫ ነው፡፡
በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የእኩልነት መብታቸው ተከብሮ የጋራቸው የሆነችውን ኢትዮጵያ ህዳሴዋን ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘው በመረባረብ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ስኬት የእግር እሳት የሆነባቸው ጠላቶቻችን ግን አሁንም ከማጥላላት ዘመቻቸው አልቦዘኑም፡፡ ይልቁንም ስልታቸውን እየቀያየሩ በአንድ በኩል ህገመንግስቱ ተጥሷል በሚል ማደናገሪያ በሌላ በኩል የሚፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮችን ህገ መንገስቱ የፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ነው ማለታቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡ አንዱ ብሄር በሌላው ላይ ጥላቻ እንዲያሳድርና ግጭት እንዲቀሰቀስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ይህን እኩይ ተግባር በጽናት በመታገል የግንቦት 20 ፍሬ የሆነውን ዴሞክራሲዊ አንድነት አጠናክረን መቀጠል ይገባናል፡፡ 
በሕገ መንግስቱ እውቅና ካገኙ መብቶች ውስጥ የሃይማኖትና የእምነት ነጻነትና እኩልነት ይገኙበታል፡፡ ሕገ መንግስቱ ፣ መንግስትና ሃይማኖት መለያየታቸውና ሃይማኖታዊ ያልሆነ የመንግስት ስርዓት መገንባት እንዳለበት መደንገጉ ሰፊ የሕዝብ ተቀባይነት ያለው ለመሆን ችሏል። መንግስትና ሃይማኖት ባይለያዩ ኖሮ መንግስት ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት ሊያስተናግድ በፍጹም አይችልም ነበርና መንግስትና ሃይማኖትን በመለያየት ሃይማኖታዊ ያልሆነ (ሴኩላር) ስርዓተ መንግስት መመስረቱ ተገቢና ትክክለኛ ውሳኔ ነበር። ይህ መብት በአግባቡ ተከብሮ እያለ ፖለቲካዊ አላማ ያለው በሃይማኖት ስም የሚካሄድ አክራሪነት ለሰላማችን ጠንቅ ሲሆን ይታያል፡፡
በሃይማኖት ስም የሚካሄድ አክራሪነት የመጨረሻ ግቡ ሃይማኖታዊ መንግስት ማቋቋም በመሆኑ ኢ-ህገመንግስታዊ ነው፡፡ አክራሪነት በሃገራችን ለዘመናት የቆየውን በሃይማኖቶች መካከል ተቻችሎ የመኖር እሴት በማበላሸት በመካከላቸው ግጭትና አለመተማመን የመፍጠር ስልትን ይከተላል፡፡ መንግስት ይህን ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ ለመመከት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በሃይማኖት ላይ ጣልቃ እንደገባ በማስመሰል ሲወነጅሉ ይታያሉ፡፡ መንግስት የህዝብ ሰላምና ጸጥታ የማስከበር ህገ መንግስታዊ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ አክራሪነትና ጽንፈኝነትን መታገልና መመከት በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ሊያሰኝ አይችልም፡፡ ይህን የአክራሪነት አኩይ ተግባር ላይ የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክረን መቀጠል ይገባናል፡፡
የጾታ እኩልነትን በሚመለከትም የወንድ የበላይነት ነግሶባት በቆየችው ሀገራችን ዛሬ ሴቶችና ወንዶች በእኩነት የሚታዩበት ስርዓት ተፈጥሯል፣ የሴቶች የሀብት ባለቤትነት፣ የተሳትፎና የመወሰን መብቶች በአገባቡ ከሚተገበሩበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በህገ መንግስታችን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሉአላዊ የስልጣን ባለቤት ሆነዋል፡፡ ህገ መንግስታችን ከጸደቀ ጀምሮየሕዝብ ሉዓላዊነት የተረጋገጠባቸው አራት ስኬታማ አጠቃላይ አገራዊ ምርጫዎች ተካሂደዋል። የምርጫዎቹ ስኬታማነት የሚለካው ከቅድመ ምርጫ እስከ ምርጫው ማጠናቀቂያ ድረስ ያለው ሂደት ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ መጠናቀቁና የምልዓተ ሕዝቡ የመወሰን መብት የተረጋገጠበት ሲሆን ነው። በዚህ ረገድ በአገራችን የተካሄዱትን አራት አገራዊ ምርጫዎች በተለይም የመራጩን ሕዝብ ቁጥርና የተሳትፎ መጠን ስንመለከት የሕዝባችን የዴሞክራሲ ባህል እየተጠናከረ መምጣቱን ያሳያሉ፡፡ በምርጫዎች ድምፅ ለመስጠት ከተመዘገበው ህዝብ መካከል በአማካኝ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው በምርጫዎቹ ዕለት ድምፁን መስጠቱ የህዝቡን ከፍተኛ ተሳትፎ ከማሳየቱ በላይ የመንግስት ስልጣን የሚያዘው በሕዝብ ምርጫ ብቻ መሆኑንም አረጋግጧል፡፡
በሀገራችን በምርጫ በተቋቋሙት ምክር ቤቶች በአጠቃላይ እስከ 5 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በአባልነት ይሳተፋሉ። በቀበሌ ደረጃ ብቻ ከ 200 እስከ 300 ሰዎች የምክር ቤት አባላት በመሆን ያገለግላሉ። ይህ ቁጥር በአማካይ ከየቀበሌው መራጭ ህዝብ መካከል እስከ 15 በመቶ የሚደርስ በመሆኑ የውክልና ዲሞክራሲያችን በራሱ አሳታፊነቱ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል።
በህገ መንግስታችን የህዝብን ተሳትፎና ውሳኔ ሰጭነት በምርጫ በሚወክሏቸው ተወካዮቻቸው ብቻ ሳይወሰን በቀጥታ በሚያደርጉት ተሳትፎ ጭምር እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ በዚሁም መሰረት ሕዝቡ በየአካባቢው አስተዳደር ውስጥ በማናቸውም መሰረታዊ  ጉዳዮች ላይ በቀጥታ እየተወያየ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎውን በማጠናከር ላይ ይገኛል። የየአካባቢው አስተዳደር አካላት ለህዝብ የቀረቡ መሆናቸውና በሕዝብ ምርጫ የሚመሰረቱ  በመሆናቸው ሕዝቡ ዴሞክራሲን ከልማት ጋር አቆራኝቶና አስተሳስሮ በማየት ሕይወቱን ለማሻሻልና ለማዳበር በሚያስችል አቅጣጫ ዴሞክራሲያዊ ባህሉን እያዳበረ ይገኛል።
የመንግስት አሰራር ለህዝቡ ግልጽ በሆነና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ ሁኔታ መከናወን እንዳለበት በህገ መንግስቱ ተደንግጓል። ማንኛውም ሃላፊና የሕዝብ ተመራጭ ሃላፊነቱን ሲያጎድል ተጠያቂ እንደሚሆን፣ ሕዝቡ በመረጠው ተወካይ ላይ እምነት ባጣ ጊዜ ከቦታው ማንሳት እንደሚችል ጭምር በግልጽ አስቀምጧል፤ በተግባር እየተሰራበት ያለውም ይሄው ነው።
የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታችን መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ ህዝቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎቶችን የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት አለው፡፡ በመሆኑም የመንግስት መ/ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት ይህን ወሳኝ የህዝብ መብት ተግባራዊ ለማድረግ መሆን ይገባዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት መልካም አስተዳደርን በማረጋገጥ ለውጡን ለማስቀጠልና የሕዝቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የለውጥ ፕሮግራሞች ተነድፈው ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ የሪፎርሞቹን ውጤታማነት ማየት የሚቻለው የሕዝቡን እርካታና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ መሆኑም አጠያያቂ አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ በሀገራችን ከፌዴራል ተቋማት ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ደረጃቸው ቢለያይም በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደሚታዩ ሕዝቡ በተለያዩ መድረኮችና አገልግሎት በሚያገኝባቸው ሥፍራዎች ቅሬታዎችን እያሰማ ይገኛል፡፡
በህዝቡ የሚነሱትን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያዎቹ የህዝቡ ፍላጎቶች እያደጉ በመምጣታቸው የሚነሱ ነገር ግን ካለን የኢኮኖሚ አቅም አኳያ በቅደም ተከተል ወደፊት የሚፈቱ ሲሆኑ በጥያቄዎቹ ዙሪያ ከህዝቡ ጋር በመወያያት መግባባት ላይ መድረስን የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ከአገልግሎት ሰጭዎች የአመለካከትና የብቃት ችግር ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ምንም አይነት በቂ ምክንያት የማይቀርብባቸው በአፋጣኝ ሊፈቱ የሚገቡ የአፈፃፀም ችግሮች ናቸው፡፡ ስለሆነም የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ለልማታችንና ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታችን ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ ሃላፊነታችንን ተጠያቂነትን ባረጋገጠ ሁኔታ መወጣት ይጠበቅብናል፡፡
የዜጎችና የሕዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ  መብቶች ሕገ መንግስታዊ ዋስትና አግኝተው በሰፋት እየተተገበሩ ነው። ሐሳብን በነፃ የመግለጽ መብት፣ የመደራጀት መብት፣ የመደገፍና የመቃወም መብት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት፣ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያለመታሰር፣  ንብረት የማፍራትና ንብረትን ያለመወረስ መብት፣ በሕይወትና በአካል ላይ ከሚፈጸም ጉዳት የመጠበቅ መብት ወዘተ በሕግም በተግባርም ተከብረዋል።
ለአገራችን የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መጠናከር ከፍተኛ ሚና ያለው ሌላው ጉዳይ ገለልተኛ የሆነ የዳኝነት ስርዓት መበጀቱ ነው። ሕገ መንግስታችን ሶስቱን የመንግስት አካላት ማለትም የሕግ አውጪውን፣ የሕግ አስፈፃሚውንና የሕግ ተርጓሚውን አካላት ስልጣንና ተግባር ለያይቶ አስቀምጧል።  በየደረጃው የተዋቀረው የዳኝነት አካልም ቀድሞ ከነበረበት የአመለካከት፣ የአደረጃጀትና የሰው ሃይል እጥረት ችግር ቀስ በቀስ በመላቀቅ ላይ ይገኛል። የዳኝነት አካላት በነፃነት የተደራጁ በመሆናቸው ያለአንዳች ጣልቃ ገብነትና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ በሕግና በህሊናቸው መሰረት ብቻ በነፃነት የሚሰሩበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል። የፍትህ ተደራሽነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና እየተጠናከረ ይገኛል። ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ በዘርፉ የሚታዩ የአፈፃፀም ችግሮች በቀጣይነት መሻሻል ይኖርባቸዋል።
2. የኢኮኖሚ ልማት ስኬቶች
በቅድመ ግንቦት20/1983 አገራችንን የገዟት መንግስታት የአገርን ዕድገትና የህዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚችል የልማት ፖሊሲ አልነበራቸውም። በንጉሱ ዘመን አብዛኛው ህዝብ በአገሩ በጭሰኝነት እየኖረ፣ ምርታማነቱና ተጠቃሚነቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተገድቦ የቆየበት ጊዜ ነበር። በደርግ ዘመንም ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ አምባገነናዊ መንግስት በተከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ የአገራችን ኢኮኖሚ ተንኮታኩቶ ዜጎች የድህነትና የጉስቁልና ኑሮ እንዲገፉ ተገደው ነበር፡፡   
ከግንቦት 20/1983 በኋላ ሀገራችንን ከድህነት ነጻ ለማውጣት የሚያስችሉ የልማት ፖሊሲዎች ተቀርጸው ተግባራዊ በመደረጋቸው ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በተለይ ባለፉት 10 ተከታታይ አመታት ያስመዘገበነው የባለሁለት አሃዝ  አማካይ የኢኮኖሚ እድገት አገራችን በአለም ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ካሉ 10 አገሮች አንዷ ለመሆን አብቅቷታል፡፡ ፈጣኑ የኢኮኖሚ እድገታችን በህብረተሰቡ ኑሮ ላይም ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ይገኛል፡፡የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ በቀጣይነት እያደገ መጥቶ በ1983 ከነበረበት 70 ዶላር በ2005ዓ.ም 550 የአሜሪካን ዶላር ደርሷል፡፡ ከድህነት ወለል በታች ያሉ የሀገራችን ዜጎችም በ2005ዓ.ም ወደ 26 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል። የእነዚህ በኢኮኖሚ እድገት የተገኙ ስኬቶች ሚስጥር የግንቦት 20 ድል ያጎናጸፈን ትክክለኛ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ባለቤት መሆናችን ነው፡፡
የግብርና የልማት ዘርፍ ያለፉት ስርአቶች ሲከተሏቸው በነበረው የተሳሳቱ ፖሊሲዎችና ትኩረት ማነስ የተነሳ ከጊዜ ጊዜ ሲዳከም ቆይቷል፡፡ ለዘመናት በቆየው ኋላቀርና ከእጅ ወደአፍ የሆነ፤ በቴክኖሎጂ ያልታገዘ አመራረትና የተፈጥሮ ጥገኝነት ሀገራችንና ህዝቧ ከዘርፉ ማግኘት የነበረባቸውን ጠቀሜታ ሳያገኙ ለርሃብና ለችጋር ሲዳረጉ ቆይተዋል፡፡ ከ1980-1983 በነበሩት አመታት የግብርናው አማካይ አመታዊ እድገት ወደ 0.2 በመቶ ወርዶ ነበር፡፡
በድህረ 1983  ግብርናንና ገጠርን ማእከል ያደረገ የልማት ስትራቴጂ ዋነኛው የልማት ፖሊሲ ሊሆን እንደሚገባ አቋም ተወስዶበት በቁርጠኝነት ወደ ተግባር ተገብቷል። ግብርናን ማእከል ያደረገ የልማት ስትራቴጂ የተከተልንበት ዋነኛ አላማ ካፒታልን በቁጠባ በመጠቀም መሬትንና የሰው ጉልበትን በሰፊውና በላቀ ደረጃ ስራ ላይ በማዋል ኢኮኖሚውን በፍጥነት ለማሳደግ ስለሚያስችል ነው፡፡ ስትራቴጂው በምግብ እራስን መቻልን እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብአቶች የሚሆኑ የግብርና ምርቶችን በማስፋፋት በኢንዱስትሪና በግብርና መካከል ያለውን ትስስር ማጎልበትን እንደ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በሀገራችን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚቻለው ክፍተኛ ምርት ማምረት ሲቻል በመሆኑ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ የግብርና ልማት ግብአት አቅርቦት (ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ወዘተ)፣የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች አቅርቦት፣ የባለሙያ ድጋፍና የመሳሰሉት በመንግስት ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት በዘላቂነት ለማላቀቅ የተጀመረው የመስኖ ልማት ስራም አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። እያንዳንዱ አርሶ አደር አማራጭ የመስኖ ውሃ (የውሃ ባንክ) ኖሮት ዓመት ሙሉ ማምረት የሚያስችለው ስትራቴጂ በቀየስነው መሰረት ዘንድሮ ብቻ ከ3 ነጥብ 1 ሚልዮን ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት እየተረባረብን እንገኛለን። በ2005 በጀት ዓመት ብቻ 251.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት መቻሉ የነዚህን የተቀናጁ ድጋፎች ስኬታማነት የሚያሳይ  ነው፡፡
መንግስት ለተፈጥሮ ሃብት ልማት በሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ስኬቶች በመመዝገብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በየቀኑ ሚሊዮኖች እንደ አንድ አሃድ ሆነው በመደራጀት ሀገራችን የነደፈችውን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ለማሳካት በሚያደርጉት ርብርብ በዚህ ዘመን በየትኛውም አገር ያልታየ የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር ተችሏል። በ2005 ዓ.ም ብቻ በሃገራችን በተካሄደው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ንቅናቄ ከ16 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የተሳተፈ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲገመት ከ10.2 ቢሊየን ብር በላይ ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ የግብርና ልማታችን ስኬቶች በተበጣጠሰ የአርሶ አደር ማሳ ላይ በተመሰረተ ግብርና የአገር ዕድገት ማረጋገጥ እይቻልም እንዲሁም አርሶ አደሩ መሬቱን የመሸጥ መብት ካልተሰጠው ህይወቱ አይቀየርም የሚለውን መሰረተ ቢስና የተሳሳተ አቋም ውድቅ አድርገዋል።
በከተማ ልማትም እንደዚሁ ፖሊሲና ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ በመደረጋቸው በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፡፡ ከተሞቻችን ለነዋሪዎቻቸው የተመቹ ይሆኑ ዘንድ መንግስት በከተሞች የሚታዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። የስራ አጥነት፣ የመሰረት ልማት፣ የመኖሪያ ቤት ችግሮችንና የመሳሰሉትን ችግሮች የመቅረፍ ጉዳይ የመንግስትን ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል፡፡
በከተሞች የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አላማ የሰነቀ የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባና በክልሎች በሚገኙ ከተሞች በተገነቡና በመገንባት ላይ በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች አማካኝነት ዜጎች የቤት ባለቤት በመሆን ላይ ናቸው፡፡ የተቀናጀ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር በማድረግ፣ ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም በዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማረጋገጥ በኩል አመርቂ ስኬቶችን  አስመዝግቧል። 
የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ልማት በከተሞች የስራ እድል ለመፍጠር፣ ድህነትን ለመቀነስ እንዲሁም ለኢንዱስትሪ መሰረት ለመጣል ትልቅ ሚና ያለው መሆኑ ታምኖበት አስፈላጊው የፖሊሲ ማእቀፍ ተዘጋጅቶለት በተደረገው እንቅስቃሴ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ በዚሁ ዘርፍ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዳችን የ3 አመት (ከ2003-2005) አፈጻጸም ብቻ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ለመፍጠር ተችሏል፡፡
ባለፉት መንግስታት ኢንዱስትሪ ትኩረት ያልተሰጠው የኢኮኖሚ ዘርፍ ነበር። ከግንቦት 20/1983 ወዲህ ግን ለዘርፉ አስፈለጊው ትኩረት ተሰጥቷል። በወቅቱ ምንም እንኳ ሀገሪቱ የተጠራቀመ ካፒታልና በዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያ በተሟላ ሁኔታ ባይኖራትም ባላት ውስን ካፒታልና የሰለጠነ የሰው ሃይል መስራት የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጣ በመነሳት የኢንዱስትሪ ዘርፍ መጫወት የሚገባውን ሚና በአግባቡ እንዲጫወት ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጣለች። በመሆኑም የኢንዱስትሪው አንቀሳቃሽ ሞተር የግል ባለ ሃብቱ እንዲሆን፣ ግብርና መር አቅጣጫውን ተከትሎ ማደግ እንዳለበት፣  ዋና ትኩረቱ ኤክስፖርት ላይ እንዲያነጣጥር፣ በስፋት ካሉን ፀጋዎች መካከል የሰው ሃይላችን በመሆኑ ጉልበት በስፋት መጠቀም እንዳለበት፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በማቀናጀት በአንድ በኩል የካፒታል እጥረት በማቃለል በሌላ በኩል ደግሞ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግን እንደሚገባው፣ መንግስት በዘርፉ ጠንካራ የአመራር ሚና መጫወት እንዳለበት እንዲሁም መላው ህብረተሰብ በኢንዱስትሪ ልማት ላይ በጋራ የሚሰለፍበትን አቅጣጫ መከተል እንደሚገባ በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂው ላይ በግልፅ በማስቀመጥ ወደ ተጨባጭ ስራ ተገብቷል።
በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው በኢንዱስትሪ መስክ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት በማረጋገጥ ዘርፉ ደረጃ በደረጃ ቀጣይ የሀገሪቱ ልማት መሰረት የሚሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው። በመሆኑም ቀጣይ የሀገራችን ዕድገት የሚወስነውና የመሪነቱን ሚና የሚረከበው የኢንዱስትሪ ልማት በተለይ ደግሞ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት በፍጥነት ለመገንባት በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል።
3. የመሠረተ ልማት ስኬቶች
ሀ. የመንገድ ልማት ስኬቶች
የመንገድ ዘርፍ ለአገር ግንባታ ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። በአንድ የአገሪቱ አካባቢ የተመረት ምርት ወይም አገልግሎት ወደ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በፍጥነት መድረስ ይችል ዘንድ ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ሊኖር ግድ ይላል። በየቀበሌው የተመረተ የአርሶ አደሩ የግብርና ምርት ሳይበላሽና ብዙ ውጣ ውረድ ሳያስከትል በተመጣጣኝ ወጪ ወደ ገበያ ወጥቶ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም መንገድ በጣም አስፈላጊ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ የእናቶች ጤና ለመጠበቅና በእርግዝናና በወሊድ ጊዜ ቶሎ ወደ ሕክምና ተቋማት ደርሰው አስፈላጊውን የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ መንገድ መኖር አለበት። በጥቅሉ ሀገራችንን የተያያዘችው አንድ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ የመገንባት ራዕይ ለማሳካት የመንገድ ዘርፍ የሚኖረው ድርሻ ጉልህ ነው።
ልማታዊ መንግስታችን ለመንገድ ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት እስከ 1984 ዓ.ም ድረስ 19 ሺህ 20 ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረውን የሀገራችን የመንገድ ርዝመት በ2005ዓ.ም  ሁሉን አቀፍ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም (URRAP)ን ጨምሮ ወደ 85ሺ 961 ኪሎ ሜትር ከፍ ማድረግ ተችሏል። በመንገድ ዘርፍ እድገት የተመዘገበው በመንገዶች ርዝመት ብቻ ሳይሆን በጥራት ደረጃዎችም ነው፡፡ ለአብነት በ1989 በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ መንገድ 22 በመቶ ብቻ ነበር፡፡ ይህ ምጣኔ በ2004 ወደ 86በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ አገራችን ይህን የመሰለ ስኬት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማስመዝገብ የቻለችው ልማታዊ መንግስታችን የህዝባችን ተጠቃሚነት በቀጣይነት ማረጋገጥ በሚያስችለው ሁኔታ በዘርፉ ላይ ሙሉ በሙሉ ተዋናይ በመሆኑ ነው።
ለ. የኤሌክትሪክ ሃይል ስኬቶቻችን
ኢነርጂ ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ግብአት ነው። የሀገሪቱ ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን ሃይል በማቅረብ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነታችን ለማሳደግ የሃይል አቅርቦት ሚና ተኪ የለውም። በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖረው የሴቶች የስራ ጫና በመቀነስ ረገድም ዘርፉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ስለሆነም የሀገራችንን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ከማረጋገጡ በተጨማሪ የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድም ኢነርጂ ጉልህ ሚና መጫወቱ አይቀርም።
በኢንዱስትሪ የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በመገንባት የአገራችን ህዳሴ ዕውን ማድረግ ይቻል ዘንድ ልማታዊ መንግስታችን የኢነርጂ ዘርፍ በተለይ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ዓቅማችን በቀጣይነት ለማሳደግ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ነው። የአገራችን የኢነርጂ ምንጮች ከታዳሽ ሃይል የሚገኙና ቀጣዩ የአገራችንን የዕድገት አቅጣጫ ግምት ውስጥ በማስገባት እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆኑ የዘርፉ እድገትም ፈጣንና አስተማማኝ ነው። በመሆኑም እስከ 1981ዓ.ም ድረስ ከ469 ሜጋ ዋት በታች የነበረው የሀገራችን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በአሁኑ ወቅት 2 ሺህ 177 ሜጋ ዋት በማመንጨት የህዳሴ ጉዞአችንን እያፋጠን እንገኛለን። በጥቂት አመታት ውስጥ ከ8ሺ እስከ 10ሺ ሜጋ ዋት ሃይል ለማመንጨት ባቀድነው መሰረት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ቀርፀን ስኬታማ ተግባሮችን እየፈፀምን እንገኛለን፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የግልገል ግቤ ቁጥር 3 ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ደግሞ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡
ልማታዊ መንግስታችን ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት ሀገራችን ያላት የታዳሽ ሃይል (የውሃ፣ የንፋስ፣ የፀሃይ፣ የጂኦቴርማልና የባዮ ፊዩል) ምንጮችን በአግባቡ በማልማት ከራሷ የልማት ፍላጎት ባሻገር ለጎረቤት ሀገራት ጭምር ኢኔርጂን በመሸጥ ህዳሴዋን እውን ማድረግ የሚያስችላት ስትራቴጂ ቀርፃ በስኬት መንገድ በመጓዝ ላይ ትገኛለች።
ሐ. የንጹህ መጠጥ አቅርቦት
ኢኮኖሚውንማሳደግና የተዘረጋውን የልማት አጀንዳ መደገፍ እንዲቻል ሀገራችን ያላትን የውሀ ሀብት በአግባቡና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ሰፊ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ ይህም በዋናነት የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦትን በከተማና በገጠርማዳረስ፣ የመስኖ አገልግሎትን ለማስፋፋት እንዲሁም የህብረተሰቡን የአካባቢና የግል ንፅህና ለመጠበቅ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ያካተተ ነው፡፡
በተለይም ንፁህና በቂ የመጠጥ ውሀን በገጠርና በከተማ እንዲዳረስ ማድረግ ጤናማና ምርታማ ዜጋን በማፍራት የዜጎችን የኑሮረጃ ተጨባጭውጥ በማምጣትህነትንማጥፊት በሚደረገው ጥረት ወሳኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህን በሚመለከት በከተማ እና በገጠር ንፁህና በቂ የመጠጥ ውሃንማዳረስ የተደረገው ርብርብ የምዕተ ዓመቱን ግብም ሆነ መንግሥት የዘረጋውን የልማት ዕቅድ ለማሳካት እንደሚያስችል ይታመናል፡፡ በ2004 መረጃ መሰረት አገራዊ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ሽፋናችን 58.3በመቶ ደርሷል፡፡
መ. የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ስኬቶቻችን
በሀገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በማምጣት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴ ቴሌኮም ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ ወሳኝ ዘርፎች ተጠቃሽ ነው። ልማታዊ መንግስታችን የቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽነትን በቀጣይነት በማስፋፋት አርሶና አርብቶ አደሩ ካለበት ቦታ ሆኖ የምርቱን የገበያ ዋጋ የሚከታተልበት የተመቻቸ ሁኔታ ፈጥሮ የህዝባችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት በቀጣይነት እያጠናከረ ይገኛል።
በኢፌዴሪ መንግስት የተነደፈውን የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እውን ከማድረግ አንፃር በቴሌኮም ሴክተር የሚጠበቀውን አስተዋፆ ለማበርከት ሰፋፊ እንቅስቃሴዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡  በመሆኑም እስከ 1983ዓ.ም ድረስ በከተሞች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ላይ ብቻ ታጥሮ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታን ከመሰረቱ በመቀየር በአሁኑ ሰዓት ሁሉንም የሀገሪቱን አካባቢዎች የመደበኛና የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ማድረግ ተችሏል። በመሆኑም በ1982ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ 56ሺህ 557 ብቻ የነበረው የቴሌኮም ደንበኞች ታሪክ በመሰረቱ ተቀይሮ በ2005ዓ.ም 23 ነጥብ 76 ሚሊዮን የተንቀሳቃሽ ስልክ ደንቦኞችን እንዲሁም  790ሺህ የመደበኛ ቴሌፎን ተጠቃሚዎችን የአገግልሎቱ ተጠቃሚዎች ማድረግ ተችላል።
በዘርፉ እየታየ ያለው የኔትዎርክ ጥራት ችግር እስካሁን በነበረን ቴክኖሎጂ ዝቅተኛ የሆነ የተደራሽነት አቅም ምክንያት ያጋጠመ ሲሆን አሁንም ችግሩን በዘላቂነት  በቅርብ ጊዜ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።  በአዲስ አበባ ከተማ ውስን ቦታዎች በተደረገው የማስፋፊያና የጥራት ማሻሻያ ስራዎች የተገኘው ውጤት በቅርቡ በሌሎች አካባቢዎችም ችግሩን በዘለቄታዊነት መፍታት እንደምንችል የሚያመላክት ነው፡፡
4. የማሀበራዊ ልማት ስኬቶች
ሀ. የትምህርት ልማት ስኬቶች
ከደርግ ውድቀት በፊት የነገረው የሀገራችን የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ በዋና ዋና ከተሞች ላይ የታጠረ ስለነበር የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት ከዘመናዊ ትምህርት ተገልለው ኖረዋል። የትምህርት ስርዓቱ ኢፍትሐዊ ከመሆኑም በላይ በሽፋንም እጅግ አነስተኛ የነበረና ከፍተኛ የጥራት ችግር የተጠናወተው ነበር። በእነዚያ የጭቆናና የዓፈና ዘመናት የሀገራችን አርሶና አርብቶ አደሮች የዘመናዊ ዕውቀት ባለቤት ማድረግ ስላልተቻለ ህይወታቸው በቀጣይነት ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንዲመጣ ከፍተኛ ድርሻ ነበረው። የሀገራችን ዕድገትም እንዲሁ በቀጣይነት በማሽቆልቆል በ1983ዓ.ም እንደሀገር የመበተን አደጋ ተጋርጦብን ነበር።
የአንድን አገር ዘላቂ ዕድገት ማረጋገጥ የሚቻለው ሀገሪቱ የነደፈቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በጥልቀት ተገንዝቦ በብቃት መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ሃይል በበቂ ሁኔታ ማሰናዳት ሲቻል በመሆኑ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን ለትምህርት ዘርፍ የሰጠው ትኩረት እጅግ ከፍተኛ ነው። በበቂ ዕውቀት የታጠቀ ዜጋ የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከመፈፀምና ከማስፈፀም በተጨማሪ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱንና ግዴታውን በአግባቡ በመወጣት በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደትም ገንቢ ሚና ለመጫወት የሚያስችለው ዕድል ሰፊ ነው። 
በመሆኑም ሁሉም የሀገራችን ህዝቦች ትምህርት በቅርብ ርቀት የሚያገኙበት ፍትሐዊ ስርዓት ተበጅቶ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የዘመናዊ ዕውቀት ተቋዳሽ ማድረግ ተችሏል። በዚህ መሰረትም በ1982ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በነበሩ 8ሺህ 830 ትምህርት ቤቶች  ገብተው የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ከ2.9 ሚልዮን በታች የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2005ዓ.ም በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ቁጥር በስድስት እጥፍ ገደማ አድጎ 17 ነጥብ 3 ሚልዮን ደርሷል፡፡ መንግስታችን ፍትሐዊ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባለው ቁርጠኝነት መሰረትም በተለይ ከ1997ዓ.ም ወዲህ በየዓመቱ በአማካይ 1ሺህ 750 የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እየገነባ ይገኛል። በከፍተኛ ትምህርት ረገድም በ1982ዓ.ም በሀገሪቱ በነበሩ ሁለት ብቸኛ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር 17ሺህ ብቻ ሲሆን ይህን ቁጥር በ2006ዓ.ም ከ300 ሺህ በላይ ማድረስ ተችላል። የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥርንም እንዲሁ ከ2 ወደ 32 ማሳደግ ችለናል።
ከመደበኛው ትምህርት አገልግሎት ጎን ለጎን በአርሶ አደሩ፣ በአርብቶ አደሩና በከፊል አርብቶ አደሩ አካባቢ አማራጭ የመሰረታዊ ትምህርት ስርዓት ተዘጋጅቶ በመተግበር ላይ ሲሆን በዘርፉ መሰረታዊ ድል ማስመዝገብ ችለናል። በመሆኑም በ2005ዓ.ም ብቻ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች የአማራጭ ትምህር ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ መደበኛ ትምህርት በቋሚነት መገንባት በማይቻልባቸው የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎችም ተንቀሳቃሽ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ልጆች ከትምህርት ስርዓቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስታችን ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። በአጠቃላይ ሲታይ የኢፌዴሪ መንግስት የቀየሰው ዜጎችን ማዕከል ያደረገ የዕድገትና የልማት አቅጣጫ ምን ያህል ውጤታማና ስኬታማ እንደሆነ በግልፅ የሚያሳይ ነው።
ለ. የጤና ልማት ስኬቶች
ከደርግ ውድቀት በፊት በነበሩ ዘመናት ፍትሐዊ የሆነ የጤና ተደራሽነት ስርዓት ባለመኖሩ የሀገራችን ህዝቦች በመከላከል ብቻ በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች የተነሳ ለከፋ ችግር ሲጋለጡ ኖረዋል። በእነዚያን ዘመናት በሀገሪቱ የነበሩ የጤና ተቋማት ብዛት እጅግ አነስተኛ ከመሆናቸው በተጨማሪ ያሉትም በዋናዋና ከተሞች ላይ ብቻ የታጠሩ በመሆናቸው ህዝቡ የእነዚሀ ተቋማት ባለቤትና ተጠቃሚ አልነበረም። የተስተካከለ አደረጃጃት ያለመኖር፣ የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት፣ የመድኃኒት አቅርቦት ችግሮች ተብትበው የያዟቸው ነበሩ።
ጤንነቱ በአግባቡ ያልተጠበቀና በተደጋጋሚ በበሽታ የሚጠቃ ዜጋ ምርትና ምርታማነት በመጨመር የራሱን ህይወት በቀጣይነት በማሻሻል የሀገር ቀጣይ ዕድገት ማረጋገጥ እንደማይችል ከጧቱ በትክክል የተገነዘበው የኢፌዴሪ መንግስት ህዝቡን ማዕከል ያደረገ እንዲሁም በመከላከል ላይ የተመሰረተ የጤና ልማት ፖሊሲ በማሰናዳት በቁርጠኝነት ተረባርቧል፡፡ በመሆኑም በ1983 ዓ.ም በመላ አገሪቱ 74 ሆስፒታሎች፣ 154 ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም 2ሺህ 119 ክሊኒኮች ብቻ የነበሩ ሲሆን ልማታዊ መንግስታችን ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረት ይህ ቁጥር በ2005ዓ.ም ወደ 229 ሆስፒታሎች፣ 3ሺህ 100 ጤና ጣቢያዎችና 16 ሺህ 48 የጤና ኬላዎች በማሳደግ ሀገር አቀፍ የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ሽፋንም 1983ዓ.ም ከነበረበት 41 በመቶ 2005 ወደ 93 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል። በድምሩ ባለፋት 8 ዓመታት ብቻ 14ሺህ ገደማ የጤና ተቋማት ተገንብተዋል።
በአሁኑ ወቅት ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ የጤና ኤክስቴንሽን ሙያተኞች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ቀበሌዎች ተመድበው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ሀገራችን የእናቶችና ህፃናት ሞት በመቀነስ እንዲሁም የኤችአይቪ ኤዲስ ስርጭትን በመግታት ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አርአያ እንድትሆን አስችሏታል። በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችና ህፃናት ቁጥርንም ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ ችለናል። በዚህም 1990ዓ.ም 871/100000 የነበረው የእናቶችን ሞት 2003 ወደ 676/100000 ዝቅ ማድረግ የተቻለ ሲሆን 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ሞትደግሞ በ1990ዓ.ም ከነበረበት 190/1000 2003ዓ.ም ወደ 88/1000 ዝቅ ብሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ 1 ዓመት በታች ያሉ ጨቅላ ህፃናት ሞትም እንዲሁ1990ዓ.ም ከነበረበት 123/1000 2003ዓ.ም ወደ 59/1000 ማውረድ ተችሏል፡፡
5. የሰላም እና የውጭ ግንኙነት ስኬቶች
በቅድመ 83 የነበሩ ዓፋኝና ጨቋኝ ስርዓቶች ሀገሪቱ በታሪካዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም ሌሎች ጠላቶች እንደተከበበች አስመስለው በማቅረብ ኢትዮጵያውያን ከጎረቤቶቻቸው ጋር በጋር ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዘላቂ ጉርብትና እንዳይመሰርቱ ደንቃራ ሆነው ቆይተዋል። በኛና በጎተቤቶቻችን ህዝቦችና መንግስታት መካከል የነበረው ግንኙነትም በመተማመን ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በመጠራጠርና አንዱ የሌላኛው የጥፋት መልዕክተኛ አድርጎ እስከመቁጠር የደረሰ ነበር። በመሆኑም ሀገራችን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመቀራረብ ለጋራ ጥቅምና ብልፅግና በጋራ ከመረባረብ ይልቅ በራሷ ዛቢያ ላይ ብቻ ታጥራ እንድትሽከረከር ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
የዓፈናና የጭቆና ዘመኑ የመጨረሻው ቅሪት የነበረው ፋሽስታዊ የደርግ ስርዓት በህዝቦች የተባበሩ ክንዶች በታሪካዊቷ ዕለት ግንቦት 20 ተወግዶ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከተቋቋመ ወዲህ ግን የባለፉት ስርዓቶች ይከተሉት የነበረውን የጦረኝነት አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ በመቀየር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን  መነሻና መድረሻ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥቅም ማስጠበቅና የሀገሪቱ ሉአላዊነት ማክበር እንደሆነ በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት በግልፅ ተደንግጓል። ሀገሪቱ ከማንኛውም ሀገር ጋር የምታካሂዳቸው ግንኙነቶች የመንግስታቱን ሉአላዊነትና እኩልነት በማክበርና በሀገራቱ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ባለመግባት እንደሆነም እንዲሁ።የኢፌዴሪ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ህዝብን ማዕከል ያደረገና ውስጣዊ ጥንካሬያችንን በማጎልበት ለአደጋ ተጋላጭነታችንን በመቀነስ ላይ ያተኮረ ሆኖ በመቀረፁ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገብ አስችሎናል። ኢትዮጵያ ከጎረቤትና ከአፍሪካ ወንድም ህዝቦች ጋር በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነትና ትብብር ለመፍጠርና ለማጠናከር በቀየሰችው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አማካይነት ከኤርትራ በስተቀር ከሞላ ጎደል ከሁሉም አገራት ጋር ሰላማዊና ጠንካራ ወዳጅነት መመስረት ችላለች። አገራችን ሁከትና ብጥብጥ በማይለየው የአፍሪካ ቀንድ ውስጥ የራሷን አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት በማረጋገጥ የቀጠናው የሰላም ሃዋርያ ለመሆን ችላለች። በዚህም በጎረቤት አገሮች በተለይ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መንግስታት የተፈረመው ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት ማእቀፍ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም በትጋት ሰርታለች። የግጭት ቀጠና በሆኑ የሁለቱ አገራት አዋሳኞች ላይም በሁለቱም አገሮች ተመራጭ አገር ሆና የሰላም አስከባሪ ሰራዊቷን በማስፈር ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር አረጋግጣለች፡፡ በደቡብ ሱዳን የተከሰተውን ያለመግባባት ለመፍታት ባለፉት 4 ወራት ያለማሰለስ ባደረገችው ጥረትም የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የፊት ለፊት ውይይት በማድረግ የሀገሪቱን ህዝቦች ተጠቃሚ ከሚያደርጉ ስምምነቶች ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ችላለች፡፡ ይህም ጥረቷ በሁለቱም ተቀናቃኝ ወገኖች ምስጋናን አስችሯታል፡፡
በሶማሊያም በተመሳሳይ ሁኔታ ሀገሪቱ መንግስት አልባ በመሆን ዜጎቿ የሰላምና መረጋገት ወጋገኑ ጠፍቶባቸው ለበርካታ ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ሲታመሱ ከቆዩበት ፈታኝ ሁኔታ ተላቀው የተረጋጋች ሀገር መገንባት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ የሀገራችን ድጋፍ ከፍ ያለ ነው። በተለይም ለአገራችን እንዲሁም ለአካባቢው አገሮች ጭምር ስጋት ሆኖ የነበረውን ራሱን የእስልማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት ብሎ የሚጠራውንና በኋላም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደረሰበት ጠንካራ ምት ተበታትኖ የቆየውን የአልሸባብ ሽብርተኛ ቡድን በመታገል በምትኩ የተረጋጋ ማዕከላዊ መንግስት እንዲመሰረት ሀገራችን በትጋት ሰርታለች።
የዲፕሎማሲ ስኬታችን ይበልጥ ደምቆና ጎልቶ የሚታየው በናይል ተፋሰስ ዙሪያ ጊዜ ያለፈባቸውን ኢ-ፍትሃዊ የሆኑና አሮጌ የቅኝ ግዛት የተናጠል ስምምነቶች ውድቅና ፈራሽ እንዲሆኑ ደግፈው የተፋሰሱ የራስጌ ሀገራትን ከጎናችን ማሰለፍ መቻላችን ነው። ይህ ውጤት የተገኘውም የተፋሰሱ የራስጌ አገራትን በአገራችን ትክክለኛና ፍትሃዊ አጀንዳና መርህ ዙሪያ በብቃት ማሰባሰብና አንድ አይነት አቋም እንዲይዙ ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ በመንቀሳቀሳችን ነው። በዚህም ዘመን ያለፈበት የግብጽ ኢፍትሐዊ አቋም ትክክል እንዳልሆነና አግባብነትም እንደሌለው የላይኛው ተፋሰስ አገራት እንዲገነዘቡት በማድረጋችን የግብፅ ፖለቲከኞችን ኢፍትሃዊ አቋም ማጋለጥ ችለናል።
በሌላም በኩል አገራችን የመላው የዓለማችን ጭቁን ህዝቦች በአጠቃላይ የአፍሪካውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ በዓለም አቀፍ አደባባይ መከራከሯ  ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ ከፍ ያለ ዕውቅና አስገኝቶላታል። በነዚህ ሁሉ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ አዲስ የለውጥ አስተሳሰቦችን በማራመድ ረገድ ባለ ራዕዩ መሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ሚና በመላው የአፍሪካና የአለም ጭቁን ህዝቦች ዘንድ ሁሌም የሚታወስና በአፍሪካውያን ታሪክ ውስጥ ጉልህ  ስፍራ ይዞ የሚኖር ነው።
በአጠቃላይ ሀገራችን በተከተለችው ትክክለኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ምክንያት ከጎረቤት ህዝቦችና መንግስታት ጋር ለዘመናት የነበረን ያለመተማመን ግንኙነት በመሰረቱ በመቀየር በወዳጅነትና በጋራ ጥቅም መርህ ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት መመስረት ችለናል። ይህም የሀገራችን የሰላም እጦት የጎረቤቶቻችን የሰላም ጠንቅ መሆኑን እንዲሁም የእነሱ ሰላምና መረጋጋት ደግሞ በቀጥታ እኛንም እንደሚመለከተን ከጋራ መግባባት ላይ በመድረሳችን ጎረቤቶቻችን የየራሳቸው ብቻም ሳይሆን የእኛም ሰላም ደጋፊ የሚሆኑበት የተመቻቸ ሁኔታ በመፍጠራችን እነሆ ሀገራችን ከአፍሪካ በኢንቨስትመንት መዳረሻነታቸው ከሚታወቁ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ መሆን ችላለች።

No comments:

Post a Comment