Sunday, July 27, 2014

ከገባበት የጨለምተኛነት አዙሪት መውጣት የተሳነው ኢንዱስትሪ


ልጅ አኪናሆም
በአለማችን የሚዲያ እድገት በርካታ ምዕተ አመታትን እንዳስቆጠረ የየጊዜው በዘርፉ የተሰናዱ ድርሳናት ያትታሉ። ዛሬ ላይ ሁላችንም ሚዲያ የሚለውን ቃል የእለት ከእለት መግባቢያ ቃል  አድርገን እየተጠቀምንበት ሲሆን የቃሉ መሰረት ”neuter of medius (middele)″ ከሚል የላቲን ቃል የተገኘ ሆኖ የተለያዩ የማስ ኮሙዩንኬሽን ማስተላለፊያ ዘዴዎችን ለመግለፅ የምንጠቀምበት እንደሆነ ብዙዎቻችንን ያግባባል። ቴክኒካዊ ትርጉሙም ከማንም ጋር ያልወገነና አንድን መልዕክት ከላኪ ወደ ተቀባይ በብቃት ለማድረስ የሚችል አገናኝ መሳሪያ ማለት ይሆናል። በሌላ አገላለፅ ሚዲያ መረጃን ለማሰባሰብ፣ ለማደራጀትና ለማሰራጨት አገልግሎት ላይ የሚውል በአብዛኛው ጊዜ ከማስ ሚዲያ ጋር ተመሳሳይ ትርጓሜ የሚሰጠው የመገናኛ ዘዴ ነው። ሚዲያ ህብረተሰቡን ለሀገራዊ ግንባታና ለለውጥ የሚያነሳሱና ህዝቡን የሚጠቅሙ መረጃዎችና መልዕክቶችን በብቃት ማስተላለፍ ያስችላል። እናም ሚዲያ በአንድ ሀገር ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ  ሚና ከሚጫወቱ ተቋማት መካከል አንዱ ነው።
በሚዲያ እድገት ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ የሚሆነው የህትመት ኢንዱስትሪው ሲሆን ከ15ኛው እስከ 17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ እንደተጀመረ የታሪክ መዛግብት ያትታሉ። በነዚህ ጊዜያት የህትመት ስራ አነስተኛ ኢንዱስትሪ የነበረ ቢሆንም ጋዜጦች በነበራቸው ተቀባይነት ሲመዘን የፕሬስ ስራ ኢንዱስትሪውን እስከ መምራት የደረሰበት ወቅት እንደነበረም መረጃዎች ያመላክታሉ። በነዚህ ጊዜያት የግለሰቦች የማተም መብት እስከምን ድረስ ሊሆን ይገባዋል የሚለው ብዙ ሲያከራክራቸው ነበር። አንድ አይነት አመለካከት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች (የእምነት ተቋማት) አባሎቻቸው የሚያወጧቸውን ህትመቶች ለመቆጣጠር ያላቸው መብት እስከ ምን ድረስ ነው? የተለያየ እምነት ከሚያራምዱትስ ጋር ተቻችሎ እንዴት መኖር ይቻላል? የአታሚዎች የህትመት ፈቃድና በሚያትሟቸው ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተጠያቂነት ምን ይሆናል? ሳንሱርን ወይም ሌላ የቁጥጥር ዘዴን እንዴት ማከናወን ይቻላል?ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በስፋት ይነሱ ነበር። በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚካሄዱ ክርክሮችም የጋራ መግባባት የተያዘባቸው ባለመሆናቸው በወቅቱ የነበረው ″የኮሙዩኒኬሽን ጦርነት” ተብሎ እስከመጠራትና በህብረተሰቡ ውስጥም የመቻቻል ባህል እየጠፋ የሄደበት ሁኔታ እንደነበር ይጠቀሳል።
በዘመኑ የነበሩ አውሮፓውያን ነገስታት በአደባባይ የሚታተሙ ግብረ ገብነት የጎደላቸው ሀሳቦችን የመቆጣጠር መንግስታዊ ግዴታ አለብን በማለት ሳንሱር የጀመሩበት ወቅትም ነበረ። እናም በቀደምት ዘመናት  በአንድ በኩል የልቅ ነፃነት የሚዲያ ፍልስፍና መሰረት የጣለበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ነፃነትና መቻቻል እየጠፋ እንዳይሄድ ከባድ ፈተና የተደቀነበት የማስ ሚዲያ የእድገት ዘመን እንደነበረ ይታወሳል። ከአንደኛው የአለም ጦርነት በኋላ የኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቷል፤ አዳዲስ የሚዲያ አውታሮች ተፈጥረዋል። ይህ ሁኔታ በህዝብ ሚዲያ አስፈላጊነት፤ አመራርና ቁጥጥር ላይ የራሱን ተፅዕኖ እያሳደረ መጥቷል። በተለይ በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በአንድ በኩል ሚዲያ ትርፍን ለማጋበስ ሲል በስሜታዊ አቀራረብ ህዝቡን ያማረረበት፤በሌላ በኩል ደግሞ መንግስታት ሚዲያውን የመቆጣጠርና የመግዛት ፍላጎት ያሳዩበት ሁኔታ ታይቷል። ሚዲያውን አስመልክቶ በተለያዩ ዘመናት አከራካሪ ጉዳዮች እየተነሱ ያለፉ ቢሆንም ሚዲያው ለህዝብ የሚጠቅም ስራን ማከናወን አለበት የሚለው ግን በተለያዩ ጎራ ተከፍለው በሚነሱ ፍልስፍናዎች ላይ እንኳ ወደ መግባባት   አምጥቷል።
ወደ ሀገራችን ሚዲያዎች በተለይ የህትመት ሚዲያዎች ስንመጣ በአብዛኛው የግል የህትመት ውጤቶች ወደ ኋለኛው ዘመን የአውሮፖውያን መንገድ ተመልሰው እየሰሩ በመሆናቸው ለአንድ ሀገር ልማት አስተዋፆ ከማበርከት ይልቅ ልዩነትን በማስፋትና መቻቻልን በማጥፋት ላይ አተኩረው በመስራት ላይ መሆናቸው ለኛ ኢትዮዽያውያን ግልፅ ነው። እኔም በመግቢያዬ ስለ ሚዲያ ታሪካዊ አመጣጥና የነበሩትን ተግዳሮቶች ለመዳሰስ መሞከሬ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ለማየት ይረዳን እንደሆነ በሚል ነው።
ሚዲያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት የሚያጠያይቅ አይደለም። ምክንያቱም እውነታው የህትመት ሚዲያው በተአማኒነት ላይ የሚያተኩር፤ የዘመኑን የስልጣኔ ደረጃ መዝግበው ለትውልድ የሚተላለፍ ብቃት ያላቸውና መረጃዎቹን እንደማጣቀሻ ለማንበብ የሚያስችሉ ህያው መማሪያ መፃህፍት መሆናቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታተሙ ያሉ የጋዜጣና የመፅሄት ውጤቶች ግን አብዛኞቹ ሙያዊ ኃላፊነታቸው በአግባቡ እየተወጡ እንዳልሆኑ እርዳለሁ። እዚህ ላይ ለማሳያነት ይሆን ዘንድ በቅርብ ጊዜ የታተሙ ጋዜጦችና መፅሄቶች ይዘው ያወጧቸውን ርዕሰ ጉዳዮች በጥቂቱ እንመልከት። እዚህ ላይ ማሳየት የሚፈልገው የግል ምልከታዬን  ነው። ምክንያቴ ሀገር የምትለወጠው ሽብር በመንዛት፤ በበሬ ወለደ ዓይነት መረጃ ህብረተሰቡን በማወናበድና ትንሽ እውነት ይዞ በሀሰት ወሬ ለውሶ እና መርዞ ማቅረብ እጅግ አሳዛኝና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ፤ ውጤቱ ደግሞ በቀጣይ ትውልድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ከመሆን ባለፈ የሚጠቅመው አንዳችም አይነት መልካም ነገር አለ ብዬ ስለማላምን ነው።
በየሳምንቱ የሚታተሙ በርካታ የህትመት ውጤቶችን ለማንበብ ጋዜጦችና መፅሄት ተራ መሰለፍ ግድ ያለኝ ባይሆንም መረጃ ለማግኘት ገዝቼም ሆነ ሳንቲሞችን ከፍዬ የማነባቸው የህትመት ውጤቶች በውስጤ ያለውን መልካም ነገር ከመሸርሸራቸውም ባሻገር አጠገቤ ያለውን ሰው የማላምን፥ ሁልጊዜም በፍርሃትና በጭንቀት የተሞላሁና ጨለምተኛ አካሄድን እንድከተል ያደረጉኝ እነዚህ ፅንፍ የያዙ የተወሰኑ የግል ይህትመት ውጤቶች ናቸው ብዬ እንዳምን ተገድጃለሁ። እዚህ ላይ አንባቢዎቼ እንድትረዱኝ የምፈልገው ነገር አንዳንድ ፀሃፊያን እንደነዚህ አይነት እጅግ በጣም የተጋነኑ፥ የበሬ ወለደ ዓይነት፥ ጨለምተኛነት የሚታይባቸውና በሀገር አንድነት ላይ አሉታዊ አቀራረብ የሚያመዝንባቸው ፅሁፎችን በተደጋጋሚ ለህትመት ሲያበቁ ተመልክቻለሁ። ይህን የሚያደርጉት ለምንድን ነው ብዩ መጠየቄ አልቀረም። አንዳንድ ፀሃፊያን እነዚህ መሰሎችን ፅሁፎች ካነበቡ በኋላ ስህተት መሆናቸውን ለማሳየትና ሚዛናዊ ዘገባ ሲሰሩና እንዲሰሩ ሲጠይቋቸውም የገዥው ፓርቲ ተለጣፊዎች፥ አሸርጋጆች፥ ለሆዳቸው ያደሩ ሆዳሞች፥ አዕምሮ የሌላቸውና ሌላም ሌላም ስነ-ምግባር የጎደላቸው ተራ የስድብ መዓቶች በማዝነብ የማሸማቀቅ ስራ ሲሰሩ ተመልክቼ ታዝቤያለሁ።
እነዚህ የሕትመት ውጤቶች ሁሉም ሰው ገዥው ፓርቲን እንዲጠላና እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ መልካም ተግባራት ጥላሸት በመቀባት ብሎም በማህበረሰቡ ዘንድ ሚዛናዊነት የጎደለው አስተሳሰብና ድርጊት እንዲሰርፅና የተደበቀ አጀንዳቸውን በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ስም በርካታ አስፀያፊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነም አምናለሁ። በየትኛውም ዴሞክራሲያዊ ሀገር እንደሚደረገው ሁሉ የሀገራችን መንግስት ህጎች ተጥሰው ሲገኙ የህዝቦች ጥቅምና ፍላጎት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የመውሰድና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት። ደግሞም በየትኛውም ሀገር ሁሉም ሰው በሁሉም አስተሳሰቦች አንድ ዓይነት ይሆናል፣ የአስተሳሰብ ልዩት ማጥፋት ይቻላል ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ እይታ ሊሆን አይችልም።  የፍላጎት ልዩነት አለመጣጣም አይደለም በሀገርና በህዝቦች መካከል በቤተሰቦቻችን ደረጃም ልዩነት አለ። ይህ ልዩነትም በአግባቡ ካልተያዘ ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል
የኢፌዴሪ መንግስት እነዚህን የፍላጎትና የኑሮ ልዩነቶችን ለማጥበን እንዲሁም ለማጣጣም እየሰራ ቢሆንም እነዚህ ጨለምተኛ ፅሁፎች ግን በየጊዜው ዳንቃራ ሲሆኑ እታዘባለሁ። የእነዚህ ጨለምተኛ የሕትመት ውጤቶች የስርጭት አድማሳቸው እጅግ ጠባብ እና በአዲስ አባበና በአዲስ አበባ ዙሪያ የታጠሩ የፕያሳ ወሬዎች ስለሆኑ ተዕእኖ የኘኛሳደር አቅማቸው እዚህ ግባ የሚባል ቢሆንም!  የተፅዕኖ ደረጃቸው ከራሳቸው እና መሰሎቻቸው የዘለለ ባይሆንም ቅሉ ነጋ ጠባ የሚሰብኩት ግን ሁከትና ብጥብጥን፣ አለመረጋጋትና መናጋትን፣ አለመቻቻልና መናቆርን በመሆኑ በእውነትም የጥፋት መልእክተኞች ናቸው ለማለት እገደዳለሁ! እስኪ የትኞቹ ፅሁፎች ናቸው በሀገር ግንባታና በህዝብ ፍላጎት ላይ ጊዜያቸውን የሚያጠፉት? መልሱ እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ ኃላፊነት የሚሰማቸው ብቻ ብሎ ማለፉ ሳይሻል አይቀርም!
በህዝባችን መካከል ድሮም የሃይማኖት ልዩነት ነበር፤ ድሮም የብሄረሰቦች ልዩነት ነበር፤ ድሮም የወንዜ ልጅ መባበልና የአካባቢን ሰው ከሌላው የማቅረብ ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር፤ ድሮም የአስተሳሰብና የአኗኗር ዘይቤ ልዩነቶች ነበሩ። ልዩነቱ ዛሬ ላይ እንዲህ እንደፈለጉ ለህዝብ ጆሮ ለማድረስ አስፈላጊ የማትሆነውን ጉዳይ ይዞ በፊት ገፆች ላይ ሮጦ መለጠፍ የሚያጣድፍ ጉዳይ ከብሔራዊ ጥቅም ይልቅ ለግል እኩይ ፍላጎት የማዋል ሁኔታ ከየት መነጨ ብዬ ለመጠየቅም ተገደደኩኝ-መልሱ በጣም ግልፅ ቢሆንም! እነዚህ የግል የሕተመት ውጤቶች  ሕገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን አለአግባብ በመጠቀም ከሙያዊ ስነ-ምግባር ባፈነገጠ ሁኔታ ለግል አልያም ለቡድን ፖለቲካዊ አጀንዳ መሳሪያነት እየተገለገሉበት እንደሆነም ለሁላችን ግልፅ እየሆነ መጥቷል።  እንጂ ልዩነታችን እማ ጥንትም የኖረ፣ አሁን ያለ ለወደፊትም አብሮን የሚቀጥል ተፈጥሮአዊ ማንነታችን ነው።
ዛሬ ላይ የፕሬስ ነፃነት በመረጋገጡ እጅግ በርካታ የህትመት ውጤት የሆኑ መፃህፍት፥ መፅሄትና ጋዜጦች ከህዝብ ጋር ተዋውቀዋል። ከነዚህ መካከል ጥቂቶቹ ወጣ ያሉና ይዘታቸውም ለአንባቢያን የማይመጥኑ በሚል የፈረጅኳቸው አሉ። በነዚህ ጫፍ የወጡ የህትመት ውጤቶች አማካኝነትም  ግለሰቦችን ያለ አግባብ እና ኢጠሞራላዊ በሆነ አኳኋን የሚዘለፉባት ሀገር ኢትዮዽያ ሆናለች (እነዚህ የሕትመት ውጤቶች ከአዲስ አበባ የመውጣት ዓቅማቸውም ሆነ ፍላጎታቸው በእጅጉ የታጠረ ቢሆንም)፤ እንደፈለጉ ስሜታቸውን እንጂ የህዝብን ፍላጎትና መንገድ መከተል የቀረባት ሀገር ኢትዮዽያ ብቻ ናት ለማለትም እገደዳለሁ።
እዲህ ያለገደብ እና ከሙያዊ ስነ-ምግባር ባፈነገጠ መልኩ እየተፃፈም ደግሞ ሃይ ባይ ሲመጣ በግል ብዕራቸው ያለእነሱ አዋቂ፤ ያለ እነሱ ፀሃፊ፤ ያለ እነሱ ታላቅ፤ ያለ የማይመስላቸው በግላቸው የሲኒ ማዕበል ውስጥ የሚናወጡ ግልቦች የእነሱን የነተበ ማንነት በነፃ ማንነታችን ላይ መጫናቸውን ቀጥለዋል። የሚያጠናቅሯቸው ፅሁፎችም በትርጉም ከተራ ልመና ያልዘለሉ (ከገንዘብ ማስገኛነት የማያልፉ) እውቀት የማያስጨብጡ ግራ የሚያጋቡና ለዜጋው ሰላም ማጣትና ስጋት የሚሆኑ ናቸው። አጀንዳቸውም ተደጋጋሚ፤ ወደ ፊት ፈቅ የማይል፤ የጋዜጠኝነት ስነ ምግባርን ያልተከተለ፤ አስልቺና አንዳንዴም በስድብ ስልጠናን የወሰዱ በሚመስሉ ለማጅ ፀሃፊያን እንደተፃፉ ይታወቃል። አንደኛውን ብሄር ከሌላኛው ለማራራቅ፤ አንደኛውን የፖለቲካ ፓርቲ ከሌላኛው ጋር ሆድና ጀርባ በማድረግ፤ አንደኛው እምነት በሌላኛው እንዲነሳ መብቱ የተነፈገ፥ መድሎ የተፈፀመበት በማስመሰል ብዙ ተብሏል።
እርግጥ ነው ፕሬሶችን አምኖ ያሉትን በሙሉ ተቀብሎ ለነውጥና ለሽብር የሚነሳሳ ዜጋ የለም ባይባልም አብዛኞቹ የሀገራችን ህዝቦች ቀኝና ግራቸውን ማመዛዘን የሚችሉ በመሆናቸው የነውጥና የአመፅ ፀሀፊያን ሚዛናቸው ምን ላይ እነደሆነ በህዝባችን ዘንድ ታውቋል። እኔም ለበርካታ አመታት ትክክል መስሎ ይሰማኝ ከነበረው ከጥፋት ወሬ ናዳችሁ አሁን  ተላቅቄ በተረጋጋ መነፈስ መራመድ ጀምሬያለሁ። የዛኔ የህትመት ውጤቶቻችሁን አንብቤ  ወደ ቤቴ ለመሄድ ስነሳ በየመንገዱ፥ በየጥጋጥጉ፥ በየመስጊዱና በየአብያተክርስቲያናቱ ሰው የሚጠፋፋና የሚተላለቅ ስለሚመስለኝ በፍርሃት ቤቴ የምገባባቸው   ቀናት እጅግ በርካታ ነበሩ። እኔ ይህን ያህል ከሆንኩ ሌሎች እንደሚኖሩ አልጠራጠርም። ስለ ሰላም መስበክ ህመም የሆነባችሁ፣ስለ ልማት መዘገብ ሽንፈት መስሎ የሚታያችሁ፤ ስለ መቻቻልና የህዝቦች አንድነት ማመላከት ውርደት እንደሚሆንባችሁ ተገንዝቤያለሁ። በእርግጥ በርካታ ፀሀፊያንና አምደኞች ስለሀገራቸውና ህዝባቸው ተቆርቋሪዎች የህትመት ውጤቶቻቸውም ሚዛናዊና አስተማሪ ብሎም መረጃ የሚሰጡ እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት አንብቤያለሁ።
በዚያን ጊዜ በህትመት ፈቃድና በሚያትሟቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ባለመደረሱ የኮሙኒኬሽን ጦርነት ተከፍቶ በማህበረሰቡ ውስጥም የመቻቻል ባህል ጠፍቶ እንደነበር እንገነዘባለን። በአደባባይ የሚታተሙ ግብረ ገብነት የጎደላቸው ሀሳቦች በየጊዜው ይሰነዘሩ የነበረበት ወቅት በመሆኑም በህዝቦች መካከል መተማመንና የጋራ አብሮነት መንፈስ እንዳይኖር ከማድረጉም በላይ በርካታ የጦርነት ቀውሶች ውስጥ ገብተው ይዳክሩ የነበረውም አንዱ ምክንያት ሚዲያው የሚያሰራጫቸው መረጃዎች በህዝቡ ዘንድ ቅራኔን እየፈጠሩ በመምጣታቸው ነበር። ታዲያ እነዚያ ሀገራት ካካሄዷቸው ተደጋጋሚ ጦርነቶች ተምረው ሀገራቸውን በእድገት ጎዳና የማስጓዙን መንገድ መርጠዋል። ሆኖም አሁንም ድረስ ከሀገራቸው ውጭ ከየትኛውም አካባቢ የሚያጋጥሙ ሁነቶችንና ችግሮችን በአሉታዊ አቅጣጫ በመምረጥና በማስተጋባት አሉታዊ ነገር ማቅረብን እንደ ግብ መውሰድ አላቆሙም። ችግሮችን በማጋነንና የህዝብ ስሜት  የሚኮረኩሩ ዘገባዎችን በማቅረብ ጊዜያዊ ተደማጭነት ማትረፍ ችለዋል።
እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ጉዳይ እነዚህ የሰለጠኑ ሀገራት ሚዲያዎች ምንም እንኳ ጊዜያዊ ተደማጭነት ቢኖራቸውም የሚያቀርቧቸው ዜናዎች ዳፋ ግን በታዳጊ ሀገራት ላይ በአሉታዊ ጎኑ የሚታይ ሆኖ እናገኘዋለን። ምክንያቱም እነዚህ ሚዲያዎች ከእነሱ ውጭ ያሉ ህዝቦች ሁሌም በጦርነትና በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀው እንዲኖሩና ሁኔታዎች እንዲባባሱ በጎደሏቸውና በችግሮቻቸው ላይ አተኩረው በመስራት ያሳጧቸዋል፤ በህዝቦቻቸውም የመነጠልና የነውጥ ስራዎች እንዲባባሱ ያደርጋሉ። እውነታው ግን በነዚህ ሀገራት በርካታ የተለወጡና መልካም ስራዎች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። በሀገራችን ውስጥም ሆነ በሌሎች ታዳጊ ሀገራት ውስጥ ሆነው ስለእኛ የሚዘግቡት የሀገራችን ሚዲያዎችም ከነዚህ ሀገራት የቀዱትን አቀራረብ ተቀብለው በመቀጠላቸውና ሚዲያውን ከልማትና ከሀገራዊ አንድነት ይልቅ ለግጭት ሁነቶች ትኩረት በመስጠታቸው በሀገራችን ልማት ላይ ምንም አይነት አስተዋፆ እያበረከቱ አይደለም የሚል ምልከታ አለኝ።
ከዚህ ቀጥሎ ርዕሶቻቸውን በግርድፉ የማነሳቸው የህትመት ውጤቶች  ይዘታቸው እጅግ በተንሿረረና በተጣመመ የአፃፃፍ ስልት የተፃፉ አንባብያንን ከማደናገር ያለፈ ትክክለኛ መረጃ ያልሰጡ ግን ደግሞ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ጥላሸት የሚቀቡ በህዝቦች መካከልም ቅራኔና መራራቅ የሚፈጥሩ ሆነው አግኝቻቸዋለሁና እናንተም ትዝብታችሁን አክሉበት ብያለሁ። የፌደራል ስርዓታችን ኢትዮዽያዊነትን  እያጠፋ ነው፤ ዩኒቨርሲቲዎቻችን  የእውቀት ሳይሆን የካድሬ መመልመያ እየሆኑ ነው፤በልማት ስም የምትዘረፍ ሀገር፤ የመሪዎች ግፍ በዝቷል የህዝቡ ብሶት ንሯል ወደ አይቀሬው እየተጓዝን ንው?፤ ኢህአዴግ እስከመቼ፤ እነ አቡበክርን በካቴና ማሰር የኢትዮዽያን እስልምና ከማሰር አይለይም፤ በመንደር ማሰባሰብ ስም ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ነው፤ የኢንቨስተሮች የመሬት ወረራ ተባብሶ ቀጥሏል፤ የፌደራል ስርዓቱ ከብተና አዳነን ወይስ ለብተና እያዘጋጀን ነው?፤ ፈንድቶ የታመቀው አብዮት፤ ምሁራኑ ስልጣኝ ሹመኞች አሰልጣኝ የሆኑበት ዩኒቨርሲቲ ሆኗል፤ የፕሬስ ነፃነት በዴሞክራቲክ ዴቨሎፕመንታል መንግስት ድባብ ውስጥ ነው፤ የሙስሊሞች ጉዳይ ከእሳት ወደ ረመጥ፤ ግንቦት 20 የወለደው የመለያየት አደጋ፤ ግንቦት 20 አንድን ፈላጭ ቆራጭ በሌላ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ነው የተካው፥ ኢህአዴግ የመለሰው አንድም ጥያቄ የለም፥ የሚሉና ሌሎች እጅግ በርካታ በአሉታና በተዛባ መልኩ የታተሙና የተዘገቡ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል።
እኔ እንደተረዳሁትና እንደገባኝ እንደዚህ ለማፃፍ፥ ለመዝለፍና የፈለጉትን ለማለት ያስቻላቸው ባለፉት ዓመታት መንግስት ለፕሬስ ነፃነት በሰጠው ህገ መንግስታዊ ዋስትና  የተረጋገጡና የመጡ ናቸው። ይህን እውነታ እውቅና ከመስጠትና ከማበረታታት ይልቅ ተቃርኖ ይቀድማቸዋል። በሀገሪቱ ጉዳዮች ያለገደብ መፃፍ የተቻለው በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግስት ባረጋገጠው ነፃነት ነው። ግን ሁሌም ህግ የማይገዛቸውና እንደልባቸው የሚፅፉ አካላት በተቃርኖ በመቆም የተሰጠው እንዳልተሰጠ፥ የተደረገው እንዳልተደረገ፥ የሆነው እንዳልሆነ፥ የተመዘገበው ልማት እንዳልመጣ፥ የተረጋገጠው የሀይማኖትና የህዝቦች እኩልነት እንዳልመጣ አድርገው ያቀርባሉ፤ ይዘግባሉ። ለልማት ቀናኢነት ቢኖራቸውማ ኖሮ፤ ሀገርንና ህዝብን ቢወዱማ ኖሮ የሚከሰቱ ችግሮችን በሚዛናዊነት በማቅረብ፤ የችግሮችን ምንጭ በመተንተንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት ህዝቡ  የነዚህ  ችግሮች   የመፍትሄ አካል እንዲሆን  የሚያደርግ አዎንታዊ ሚዲያ መሆን ይችሉ ነበር።
ይህም ማለት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በማራገብ “ተነባበቢ” ለመሆን ከመስራት ይልቅ በማንኛውም ደረጃ የሚከሰቱ  ችግሮችን ትክክለኛ ገፅታና የችግሮችን ምንጭ በመተንተን የመፍትሄ ሀሳቦችን በማቅረብ ህዝቡንም ለመፍትሄው ተሳታፊ ለማድረግ መስራትና አቅጣጫ ማመላከት ይቻል ነበር። እውነታው ግን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። በሀገራችን እጅግ በርካታ የልማት ስራዎች እየተሰሩ እያለና እነዚህን በሚገባ በመዘገብ መረጃውን ለህዝቡ በማድረስ መስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ እያለ ሁሉም ነገር በተቃርኖና በጥፋት  የሚቆሙ  የህትመት ሚዲያዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።
በየጊዜው የምዕራቡ አለም የነተበ ቲዮሪ ጋር ተቆራኝተው የሀገራችንን ብሩህ ዘመን ለማዳመን ይታትራሉ። ለሀገርና ለህዝብ ብልፅግና መባተል ክብርና ሞገስ ያለው  ተግባር ነው፤ ውሳኔንና ቀናነትን ይጠይቃል፤ የተጣመመውን ለማቅናት፤ የቆሸሸውን ለማፅዳት፤ ኋላ የቀረውን ወደ ፊት ለማምጣት፤ የተጓደለውን ለማሟላት ሚዲያ ወሳኝ መሳሪያ እንደሆነ አምናለሁ። በየሳምንቱ እየታተሙ ከሚወጡ የተዛቡ፤ የተንሻፈፉና ህዝብን በሽብርና በፍርሃት እንዲኖር ከሚያደርጉ ሚዲያዎች ግን ምንም ባይኖር እመርጣለሁ። ቁም ነገር ለመገብየት፥ እውቀት ለመቅሰም መፅሀፍቶችንና ጋዜጦችን ለመግዛት ወጥቼ ስመለስ ጤናማው አዕምሮዮ ተቀይሮ፥ የምራመድበት መንገድን በፍርሃት እየቃኘሁ ቤቴ የምገባባቸው ቀናት ቀላል አይደሉም። ሆኖም በፅሁፎቻቸው እንዳሉት ሀገሬን አላገኛትም፤ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም ይገባል፤ የልማት ስራዎች እዚህም እዚያም እየተፋጠኑ ቀጥለዋል፤ ኢትዮዽያም በልማት ወደ ፊት ግስጋሴዋን ተያይዛዋለች። የሀገሬ ቀና መንገድ የማይታያቸው አንዳንድ ጨለምተኛ ፕሬሶችም በዳመነው ብዕራቸው ውሃ የማይቋጥር፤ እዚህ ግባ የማይባል፤የፍርሃት ፅሁፎቻቸውና የኋልዮሽ መንገዳቸውን መምራታቸውን ቀጥለዋል። ይህን የእኔን ምልከታ የተጋሩና የተረዱ አንባብያን እስኪ ዛሬ ደግሞ ምን አሉ? ከማለት ያለፈ ቁም ነገር የሚገኝባቸው የህትመት ውጤቶች እንዳልሁኑ ብዙዎቹ ግንዛቤ በመያዛቸው ትዝብት ውስጥ ማስገባታቸውን ለማከል እወዳለሁ። የእነሱን የጥላቻ ወሬ በማንበብ ቤተሰቦቻቸውን የበተኑ፤ በውስጣቸውም ጥላቻን ያረገዙ ነበሩ። ሆኖም ለበርካታ ዓመታት ይዘት አልባ ፅሁፎቻቸው ያመጡት ምንም አይነት መልካም ውጤት እንደሌለ በመረዳታቸው መንገዳቸውን አስተካክለዋል።
እነሱ ግን ዓላማቸው አንድና ያው ነውና ዛሬም አጧጡፈው ቀጥለውበታል።ምንም እንኳ ብዙዎቻችን ከእነሱ የጨለምተኝነት አስተሳስብ የራቅንና የምናመዛዝን ብንሆንም እነሱ ግን በሀገርና ህዝብ ስም ስሜቶቻቸውን፤ ህልማቸውን፤ ቅዠታቸውን፤ ከመፃፍ አልቦዘኑም። ለዚች ምልከታዬም ባልበሰለ የብዕር ብትራቸው እንደሚወራጩ አውቃሁ። ከመንቃት ይልቅ ባሉበት ሆነው እንደሚያቃትቱና እንደሚወራጩም ይሰማኛል። ግን ስሜቴን ሳይሆን ለዓመታት ያስተዋልኩትን ትዝብቴን በተሟላ መልኩ ባይሆንም ለመጠቆም ሞክሬያለሁ ቀሪውን አንባቢዎቼ እንደሚሞሉት አልጠራጠርም።  እኔ ግን ዛሬም ሌላ ቀን ነው ለመለወጥ ጊዜ አላችሁ፤ ስለ መቻቻል፥ ስለ አንድነት፤ ስለ ሰላም፤ ስለ ፍቅር፤ ስለ ልማት፤ ስለ አብሮነት፤ ስለ አዲሲቷ ኢትዮዽያ፤ ስለ ብልፅግና፤ ስለ ታላቅነት፤ ብቻ እጅግ በርካታ ጉዳዮች ላይ መፃፍና ተነባቢነትን ማግኘት ላቅ ሲልም ለሀገር ዕድገት እርሾ ማኖር ይቻላል ባይ ነኝ። አበቃሁ!!    


Wednesday, July 23, 2014

IGAD-LED SOUTH SUDAN PEACE TALKS TO RESUME ON 30 JULY

                             
                   PRESS RELEASE (IGAD)
23 July 2014, Addis Ababa: Following the adjournment of the Fourth Session of IGADled South Sudan Peace Process in Addis Ababa on 23rd June 2014, the IGAD Special Envoys have carried out broad consultations with various actors and stakeholders in the South Sudan peace Process.

The main objective of the consultations was to take stock of the progress, challenges and chart the way forward, particularly in the implementation of the resolutions of the IGAD Assembly of Heads of State and Government Summit meeting of 10th June 2014. 
The resolutions of the Summit included the commitment by the two Principals to the conflict, H.E. Salva Kiir Mayardit, the President of the Republic of South Sudan (RSS) and Dr. Riek Machar, former Vice-President of the RSS and leader of SPLM/A (in opposition),“to end the war”; and to establish a Transitional Government of National Unity (TGoNU) that will offer the best chance for the people of South Sudan to take the country forward. 
The essence of stopping the war is to create a conducive environment for negotiations; and, facilitate humanitarian operations to reach the needy populations and pre-empt the looming famine in South Sudan that is likely to affect millions of the displaced populations.

The Envoys carried out extensive consultations in Addis Ababa, Nairobi and in Juba during which they met and held discussion with the Principals of the warring Parties; the President of the Republic of South Sudan and the leader of the SPLM/A (in opposition).The Envoys further held consultative meetings with the delegations of stakeholders to the peace process namely: the Government of the Republic of South Sudan, the SPLM/A (in Opposition), the SPLM Leaders(Former Detainees), Political Parties, Civil Society Organizations and Faith based Organizations.

All the stakeholders have reiterated their commitment to the negotiation process, which is tentatively scheduled to commence on 30th July 2014 to 10th August 2014.

The agenda of the next session will be to finalize and sign the Cessation of Hostilities Matrix; and negotiation on details of the Transitional Government of National Unity

Tuesday, July 22, 2014

ይድረስ ለ"ኢንጅነር" ይልቃል ጌትነት


ልጅ አኪናሆም
ይቺን አጭር ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በባለፉት ጊዜያት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን አስመልክቶ የሰጧቸው ማብራሪያዎች እና በኢትዮ ምህዳር የረቡዕ ሀምሌ 9 ቀን 2006 ዓ∙ም እትም ሰማያዊ ፓርቲ መሰዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን ማስታወቃቸውን ማንበቤ እኚህ ሰው ምን ነካቸው? በማለት ብቻ ለማለፍ ባለመፈለጌ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ በሕጉ መሰረት ተመዝግቦ በምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አውቃለሁ። በህጋዊነት መዝገብ ላይ የሰፈረ ፓርቲ ደግሞ ህግን በተከተለ አግባብ ብቻ ተንቀሳቅሶ  ወደ ስልጣን መምጣት ያለበት ይመስለኛል፡፡ እርስዎ ግን ከዚህ በተቃራኒው ሲጓዙ ተመልክቻለሁ። በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን መግለፅና ብረት አንግቦ ጎራ ለይቶ መፋለም በተግባር ፍፁም የማይገናኙ ናቸው፡፡ እርስዎ ግን በሰላም ጥላ ስር ራስዎትን ወሽቀው “አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅቻለሁ” አሉን። ኢንጂነር እንደው ይህች እከፍላታለሁ ያሏት "መሰዋዕትነት" ራስዎትን የጀግና ስም ሰጥተው ለመሸለል ባልሆነ፡፡

ምን ይሄ ብቻ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን መረከብ እፈልጋለሁ በሚለው ፓርቲዎ ስምም "መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም" ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ እኔም እኚህ ሰው የሽብርተኝነት ትርጉሙ ተዛባባቸው እንዴ ስል እራሴን ጠይቄ ተገረምኩ። መቼም መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመከላከል ስራ ገልብጠው መንግስት ሽብር  እየነዛና ህግ እየጣሰ ነው ይህን ለመከላከልም ለትግል እየተዘጋጀን ነው ያሉት እንደው እስኪ የቀዘቀዘው ስሜ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በሚዲያው ይወራጭ ብለው ባልሆነ፡፡ ኢንጂነር በመጀመሪያ ሀገሩንና ህዝቡን የሚወድ መሪ ለግላዊ ህይወቱ ቅድሚያ አይሰጥም። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እየተዟዟሩ  በተቃዋሚ ፓርቲ ስም ለሚሰበስቡት ገንዘብ ሲሉ ሌላ ፓርቲን መክሰስ፤ ማንቋሸሽ ምን አመጣው? እርስዎና መሰሎችዎ እያወራችሁ፤ እየዛታችሁ የምትኖሩትስ ምን ሊባል ነው? ኢህአዴግን ካልተሳደቡ፣ በእውነት ላይ ሸፍጥ ካላነሱ እና እውነታውን ሸምጥጠው ካልካዱ እርዳታና ድጋፍ አይገኝም የተባሉ ያህል ተሰማኝ።

 ሀገሪቱን የሚመራው መንግስት እኮ ህዝቦቹን የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ዛሬ ላይ በሽብር ጥቃት እየተናጡ ያሉ ሀገራትን በመመልከት ብቻ የመንግስትን ሚና ምን መሆን እንዳለበት ለመገንዘብ በቂ ነው። ሶማሊያ፤ ኬንያ፤ ናይጄሪያ፤ ማሊ፤ ግብፅ፤ ሊቢያ፤ ቱኒዚያና ሌሎችን ማንሳት ይቻላል። የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን አቅም ሁሉ በፀረ ሽብር ዘመቻው መጠቀሙ ህዝቦቹን ከስጋት ለመጠበቅ እንዳስቻለው እርስዎና መሰሎችዎ ለመቀበል ፈቃደኛ ባትሆኑም ለበርካቶቻችን ግን ሃቅ ነው። መቼም ይሄ የኢንጅነርነት ማዕረግ እንዲሁ እንዳልሆነ ልገምት፡፡ ለነገሩ ፖለቲከኛ ነኝ ብለው አይደል ፓርቲ እየመሩ ያሉት በእርግጠኝነት የአፍሪካን የፖለቲካ ሁኔታ ለመገንዘብ አይቸግርዎትም እኛ በሽብር ተጋላጭነታችን ቢሆንማ ኖሮ የርካታ አስከፊ አደጋዎች ሰለባ በሆንን ነበር።

ሆኖም ኢትዮዽያዊ ሁሉ ለሽብር ድርጊትና ለፅንፈኝነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑና መንግስት ዜጎቹን ለመጠበቅ የሚያደርጋቸው በብቀት የተሞሉ የቅድመ መከላከል ጥረቶች ባይኖሩ ኖሮ ዛሬ ላይ መካከለኛው ምስራቅ፣ ምዕራብ አፍሪካና ሌሎች ሀገራት ላይ ያለው የሽብር ስጋት እና እልቂት ውስጥ በገባን ነበር። አንድ ነገር መጨመር እፈልጋለሁ። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን አስመልክቶ የሰጧቸው ማብራሪያዎች  እሳቸው እንግሊዛዊ ሆነው ለኢትዮዽያ ህዝብ የነፃነት ታጋይ መስለው እንዴት ሊቀርቡ ቻሉ? ኤርትራ ድረስ ሄደው ቡና ጠጥተው ተመለሱ ነው የሚሉት? የኤርትራ መንግስት በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮዽያ ጋር ያለው ግንኙነት እንደሆነ ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ምናልባት ኢንጅኔር ሌላ ስም ካልሰጡት ማለቴን ነው። የእነ አቶ አንዳርጋቸው የቀውስ ስምት ኃላፊውና አዛዡ ኢሳያስም ቢሆኑ ሀገራችንን ሲመለከቱ የጥፋት አዕምሯቸው እረፍት የማያገኝ፤ ሁሌም ጠፍተን ማየትን የሚፈልጉ ናቸው።

ታዲያ የአቶ አንዳርጋቸውና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ግንኙነት ለሀገራችን ሰላም ሊወያዩ ነው ለማለት ምን ቀረብዎ ኢንጅነር? ባለፉት ዓመታት ያሴሩብንና ለጥቃት ያጋለጡንን መመልከት እንደማይፈልጉ በመዘንጋት እንዳልሆነ ግን ልብ በሉ። ከዚያ ውጭ ይቺን ሀገር የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግስት በሽብር ድርጊትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ቡድኖችና ግለሰቦች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ቢወሰድ ምንድን ነው ጥፋቱ? የእርስዎ ቅሬታስ መነሻው ምን ይሆን!? ኢትዮዽያ ለማንኛውም አይነት የሽብር ድርጊት መናኸሪያ እንድትሆን የሚፈልጉ ሁሉ እሪታቸው ይታወቃል። በፈለጉበት ቦታ የማፈንዳት፤ ህዝቡ እየኖረ ያለውን ሰላማዊ ህይወት የማመሰቃቀልና የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ ነው። እናም ይህ ግልፅ ዕቅድ መጨናገፉ እንዴት ኢንጅነር ሊያስኮርፋቸው ቻለ ብዬ እንዳልጠይቅ ምላሹ ግልፅ ስለሆነ ለጊዜው ልለፈው!

ኢንጅነር ይልቃል ምላሹን ከእርስዎ የማልፈልገውን አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ሆነው እየተንቀሳቀሱ ነው። የመረጡት መንገድ ሰላመዊ ወይስ መሰዕዋትነትን የሚያስከፍለውን መንገድ?  ባለፉት 10 ቀናት እያስተላለፉ ያለው መልዕክት ግን ለሀገራችን የሚበጅ ምንም ነገር የለውም፤ የማይጠበቅ ቢሆንም! እዚህ ሰላማዊ ትግል አካሂዳለሁ እዚያ ደግሞ የሚከፈለውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተናል ይላሉ። ወይ “መስዋዕትነት” እንዲሁ በእርስዎ መቀለጃ ከመሆኗ በፊት ለህዝብ ጥቅም ሲባል የራስን ጥቅምና ፍላጎት ላይ ሁሉም ዓይነት ገደብ ማድረግ የሚል ግርድፍ ትርጉም ነበራት! በአንድ ሀገር ውስጥ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ግን መስዋዕትነት ብሎ ነገር አልነበረም፣ለወደፊቱም በፍፁም አይኖርም! ሆኖም መታሰራቸው ወንጀለኛነታቸውን አያረጋግጥም፣ እርስዎ የሚሉት ነገር ከሌለ ማለቴን ነው።

መቼም እርስዎን ህጋዊ አካሄድን ለማሳወቅ የሕግ ሀሁ ማለቱ አስፈላጊ ነው ብዬ አልወስድም። ግን እርስዎ እያነሷቸው ያሏቸው የተውገረገሩና የተምታቱ የፖለቲካ አጀንዳ የሚመስሉ እዚህም እዚያም የሚረግጡ አስተያየቶችና አቋሞች የ21 ክፍለ ዘመን ስለመሆናቸው እያጠራጠሩን ነው። እንዲህ እንደፈለጉ የሚያስፈራሩት፤ የሚዘረጥጡት፤ የሚናገሩት፤ በነፃነት የሚንቀሳቀሱባት ሀገር እኮ ይህ ፓርቲና መንግስት የሚመራት ኢትዮጵያ ናት። በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰጧቸውን መግለጫዎች እከታተላለሁ፤ ሆኖም ይህን በማድረግዎ ሲጠየቁ አላየሁም፤ በነፃነት ይወጣሉ ይገባሉ። መንግስትም አሸባሪ ነዎት አላለዎትም ምክንያቱም ሰላማዊውን መንገድ መርጠው እስከተንቀሳቀሱና ከሽብር ድርጊት እስከራቁ ድረስ ማለቴ ነው። ይህ ስል ካልተሳሳትኩኝ ማለቴ ነው ኢንጅነር!  ግን እርስዎ የሀምሌ 9 ቀን 2006 ዓ∙ም መግለጫዎና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን አስመልክቶ የሰጧቸው የተንሿረሩና ላይና ታች የሚረግጡ “ትንታኔዎች” ወይ ኢንጅነር ምን ነካቸው እንዲል አስገድስደውኛል!

በመግለጫ”ዎ” ሀገራችንንም ህዝባዊ በአምባገነን ስርዓት ከምትመራው ኤርትራ ጋር አነፃፅረው መግለጫ ማውጣትዎን አንብቤያለሁ፤ትዝብት ላይ መጣሌንም አልሸሽግም። በእርግጥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እርስዎን መሰል ተቃዋሚ እንዳለው ሁሉ በርካታ ደጋፊዎች ያሉት ድርጅት ስራውን በተግባር እያሳየ ያለ መሆኑን በሌላ ነገር ተሸብበው ካልሆነ ይጠፋብዎታል ብዬ አልገምትም። ምክንያቱም በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ የሀገራችን ለውጥ ተገቢውን እውቅና እየተቸረው ነውና! ለንፅፅር የማይበቃ ተራ ነገርን ከሀገራችን ፈጣን፣ ተከታታይና ፍትሐዊ ዕድገት እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ካለው የዴሞክራሲ ስርዓታችን ጋር ማነፃፀር የሚጠበቀው ከማን እንደሆነ ጠፍቶኝ ግን አይደለም!

ከምንም በላይ ደግሞ ህዝቡ ይወክለኛል ላለው የፖለቲካ ፓርቲ ማለትም ኢህአዴግ በአደባባይ ድምፁን ሰጥቶት ኢህአዴግም የተሰጠውን አደራ ለመወጣት ቀን ተሌሊት እየተጋ ባለበት ወቅት እን ኢንጅነር እና መሰሎችዎ ትወጡና ባልተሰጥዎት ስልጣን “ስለህዝባችን” እያላችሁ ውስጣዊ ማንነታችሁ ታሳዩናላችሁ! በመቀጠልም ያለገደብ በማውገርገር ህዝቡን ለማደናገር በማለም ህዝቡ እንዲሰራለት የመረጠውን ድርጅት ተልዕኮውን እንዳይወጣ እናንተ ራሳችሁ ስራ ትሆናላችሁ! ወይ መቃወም!!

ኢንጅነር አልተመረጡም ማለት ኢህአዴግ አልተመረጠም ብሎ መደምደም ሀገርን እመራለሁ ብሎ ዝግጅት እያደረገ ካለ የተቃዋሚ ፓርቲ የሚጠበቅ አይመስለኝም። ኢህአዴግን ለመፎካከር አቅሙና ሞራሉ ሰማይ እንደሆንብዎ በውል ስለሚገነዘቡም ቀድመው ጥላሸት በመቀባት ወደ ፊት በመራመድ ለሀገሩና ለህዝቦቹ እየሰራ ያለን ድርጅት መንቀፉን ይመርጣ፣ ይዝታሉ፣ ይነቅፋሉ፤ ይዝታሉ፣ ይፎክራሉ ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ይላሉ። ዴሞክራሲ ማለት የህዝቡን ጥቅም ለማረጋገጥ እንጂ የግለ ሰዎች ፍላጎት እና የቀን ሕልም ለማሳካት የሚዘጋጅ በሰው ልክ የሚሰፋ ቀሚስ መሆን አይችልም! ሰዎች ሀሳባቸውን የመግለፅ፤ስሜታቸውን የማንፀባረቅ፤ ይሁን እንጂ ሀገራችን በዴሞክራሲያዊ ባህሏ ዳብራ አድጋና ተመንድጋ ለማየት ጭፍን ተቃዋሚዎችና ጭፍን ደጋፊዎች መስመር ሊይዙ ይገባል። በምክንያት የሚያምን፤ በምክንያት የሚቃወምና የሚደግፍ ፓርቲ ያስፈልጋል። እናንተ ስለ ሀገራችን ከምታውቁት በላይ ህዝባችን በዝርዝር ያውቃል። እንዲያውም የሀገራችን ህዝቦች ግራ ቀኙን ማመዛዘን የሚችሉ በመሆናቸው እንጂ እርስዎን መሰል “የፖለቲካ መሪዎች” የሚያጨልሟት ኢትዮዽያን ባናውቅ ኖሮ ተጨራርሰንና ተላልቀን ነበር። ይህን ሁሉ የተንሿረረና የተዛባ መረጃ እየሰጣችሁት ጆሮ ነፍጓችሁ ሰላሙንና ልማቱን የመረጠውን የሀገሬን ህዝብ እያየሁ እደመማለሁ። ግልብ የፖለቲካ መሪዎች ከግራና ከቀኝ በሚያላትሙት ተራ ወሬ ቢሆን ኖሮ ኢትዮዽያ ዛሬ አትኖርም።

አሁንም ግን ኢንጅነር ቆም ብሎ በማሰብ ሽብርተኝነትንና የሽብርተኝነት ድርጊትን ከሰላማዊ ትግል ለመለየት ጊዜው ያንሳል የሚል እምነት የለኝም። እናንተ ግራ ተጋብታችሁ እኛንም ግራ አታጋቡን። በተለያዩ ሚዲያዎች የምትሰጧቸው “መግለጫዎች” እኮ ህዝብን ያደናግራሉ። እንዴት ነው የተምታታ እና የተውገረገረ “መግለጫ” እየሰጣችሁ አመኔታ የሚኖረን? ጥሩውን ጥሩ፤ መጥፎውን መጥፎ የሚል ግልፅ አቋም ሳይኖራችሁ ሀገርና ህዝብ ስለማስተዳደር ትነግሩናላችሁ። እናም ኢንጅነር ጣትዎን ወደ ውጭ ከመቀሰርዎ በፊት ራስዎን በመመርመር መራመድ ይገባዎታል እላለሁ። በሰላም ሀገር ኡኡታ፤በተረጋጋ ህዝብ መካከል ሽብር እየፈጠሩ ያሉት እርስዎ እንጂ መንግስት አይደለም። ሰማያዊ ፓርቲ “መሰዋዕትነት” ለመከፈል መዘጋጀቱንም ነግረውናል።  እስከ ምን ድረስ ነው? ኢሳትን እንደሚጠቀሙም አውጀዋል። መጠቀም ከጀመሩ እኮ ሰነባብተዋል፤ በርካታ ማብራሪያዎችን ለኢሳት እየሰጡ እንደነበረም እከታተላለሁ። ታዲያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረና ነው ኢሳትን እንደሚጠቀሙ አዋጅ መንገር ያስፈለገዎ? ልብ ማለት ያለብዎት ነገር ደግሞ ግንቦት ሰባት ሀገራችን የሽብር ድርጊት ከሚፈፅሙ ዝርዝር ውስጥ ከተካተተ ሰነባብቷል። ኢሳት ደግሞ የግንቦት ሰባት ልሳን ነው። ታዲያ ኢሳትን መጠቀም ከግንቦት ሰባት ጋር ውህደት መፍጠርዎ ይሆን? ወይስ ሌላ አጀንዳ ማንሳት ፈልገው? አበቃሁ      

      

Wednesday, July 2, 2014

Eritrea president targeted by new Swedish law


Swedish law firm reports Isaias Afewerki and several ministers to the police for crimes against humanity.

Last updated: 02 Jul 2014 13:02
Listen to this page using ReadSpeaker
Email Article
 
Print Article
 
Share article
 
Send Feedback
President Afewerki and several ministers targeted by Swedish crimes against humanity law [Reuters]
Several top Eritrean leaders have been reported to the police for crimes against humanity by a Swedish law firm, as a new law took effect enabling such crimes committed anywhere else in the world to be prosecuted in Sweden.
The report lists a series of alleged crimes including torture and kidnapping, and targets Eritrean President Isaias Afewerki and several of his ministers by name.
TThere is a lot of evidence from human rights groups, particularly about indefinite imprisonment without trial (in Eritrea).

"This is not only symbolic. We believe there are legal grounds to prosecute the people we have named," human rights lawyer Percy Bratt told the AFP news agency on Tuesday.
The legal move, the first of its kind in Sweden, was filed the same day that crimes against humanity were introduced into the Swedish penal code.
The code enables judges to prosecute crimes regardless of where they have been committed or by whom.
"There is a lot of evidence from human rights groups, particularly about indefinite imprisonment without trial (in Eritrea)," Bratt said.
"There are also many Eritreans in Sweden who could give information about the conditions in the country in general."
According to the latest figures, 12,800 Eritreans live in Sweden, and the number of asylum seekers from the country keeps growing.
Swedish-Eritrean journalist Dawit Isaak has been imprisoned in Eritrea since 2001, and 13 years on little is known of his fate.
Bratt said that even if the case was taken on by the prosecutors, it could take years before criminal charges were laid, given the complexity of the allegations.
Eritrea, with a population of five million and a size about the same as Britain, is one of the most isolated and secretive countries in the world.
According to the United Nations, 4,000 Eritreans flee the country every month to escape ruthless repression, including unlimited forced labour for the government.

SOURCE-Aljezeera


Seven Sugar Factories Start Production Next Year

Seven of the ten National Sugar Factories are to start production at the end of the coming Ethiopian year, Ethiopian Sugar Corporation announced.
Tendaho- 1 & 2, Omo-Kuraz-1, Kesem, two of the Tana Beles projecta and Arjo- Dedesa are the seven factories expected to start full scale operation.
When these factories go in to full scale production, they will raise nation’s annual sugar production to 1.58 Million Tons, Ethiopian Sugar Corporation’s Communication Director Zemedkun Zawde said.
At the end of the next Ethiopian budget year, Ethiopia will have 10 sugar factories with a total annual production capacity of 2.25 Million Tons.

Ethiopia and Russia Sign Cooperation Agreement

ethio russia

Ethiopia and Russia have signed an agreement that would enable them to cooperate in areas of agriculture and energy, Ministry of Foreign Affairs.
The 5th session of the Joint Commission established to enhance their collaboration in economy, science and techniques was held from June 24-28 in Moscow.
The Ethiopian Ministry of Foreign Affairs stated that the joint commission evaluated the performance of the 4th meeting and further explored new fields of cooperation.
The two countries subsequently signed an agreement that would enable them to further collaborate in areas of trade, economy, science and technics.
The Ethiopian delegation that represents 15 institutions was led by HE Alemayehu Tegenu, Minister of Water, Irrigation and Energy. 
During its stay in Moscow, the delegation held talks with Russia’s Deputy Minister of Mine Resources and Ecology, Valery Pak.
SOURCE-The Ethiopian News Agency-ENA

Tuesday, July 1, 2014

Yemen Arrested Terrorist Andargachew Tsige


Andargachew Tsige, Secretary General of the Terrorist Group, Ginbot 7, has been arrested by Yemeni government.

 
According to the press statement of the Terrorist Group-Gibot 7-, Andargachew was on a transit flight en route to Eritrea when he made a stop in Yemen.
Andargachew is an Ethiopian origin and British citizen who has been working to destabilize Ethiopia and the region at large. He along with his terrorist group Ginbot 7 and its members is responsible for many of the terrorist acts and attempts in Ethiopia.

The Eritrean Government has been engaged in supporting and training Terrorist Groups such as the Union of Islamist Courts and Alshaba of Somalia, Ginbot 7 and other anti Ethiopia groups and individual as well.  That is why the UN Peace and Security Council Sanctioned the Nation-Eritrea.