Tuesday, August 19, 2014

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአሜሪካ የነበረው ቆይታ የተሳካ እንደነበረ ተገለፀ

አሁን ባለን የአፈፃፀም ደረጃ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዳችንን ለማሳካት በሚቻልበት መንገድ ላይ ሲንሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና በአሜሪካ ኩባንያዎች ዘንድ የኢንቨስትመንት ፍላጎት ማሳደር መቻሉም ተጠቅሷል።

በኢትዮ-አሜሪካ የኢንቨስትመንት ፎረመና በአፍሪካ-አሜሪካ ኢኮኖሚ ትብብር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያቀናው በኢፌደሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመና በኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአሜሪካ በነበረው ቆይታ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን ውጤታማ ተግባር ያስተዋወቀችበትና ለአፍሪካውያን አጋሮቿም ተሞክሮ ያስተላለፈችበት እንደነበረ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን እንዳብራሩት በአሜሪካ የሚገኙ ትላልቅ ኩባንያዎች  ወደ ሃገራችን ባለሙያ በመላክ ጭምር በኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን ጥናት እያደረጉ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ይህ የሃገራችን ኢኮኖሚ የፈጠረው ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡  ሚኒስትሩ አያይዘው ይህ ፍላጎት የሀገር በቀል ኩባንያዎች ምርታቸውን የሚቀበል ገበያ እንዲያገኙ እድል ከመክፈቱ ባሻገር በሽርክና ለመስራትም የሚያስችል መልካም እድል ነው ብለውታል፡፡
በአሜሪካ የሚኖሩና ግዙፍ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥረው በመስራት አንቱ የተባሉ ዜጎቻችን ሃብት በመቋጠር ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ነገር ለመስራት ማሰብ የጀመሩበትና እውነተኛ ፍላጎት ያሳዩበት ሁኔታ እንዳለና በሀገራችን እየተመዘገበ ያለው ለውጥም ለዲያስፖራው መነሳሳት የፈጠረ እንደሆነ ልዑኩ በነበረው ቆይታ ማረጋገጡን አቶ ሬድዋን አስረድተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በተገኙበት መድረክም ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በጋራ መድረኩን የመምራት እድል የተሰጣት ሲሆን በተጨማሪም በጤና፣ በተፋሰስ ልማት ስራ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጨመር፣ በሴፍትኔት ፕሮግራም ትግበራ ያስመዘገበቻቸውን ስኬታማ ተግባራት እንድታቀርብ መደረጉን አቶ ሬድዋን በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡ መድረኩ ኢትዮጵያ ልምዷን ያካፈለችበት ከሌሎች ሃገራት ልምድ የወሰደችበት በመሆኑ የተሳካ ነበር ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
አቶ ሬድዋን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመጨረሻ ዓመት ላይ በመሆናችን ባለፉት ዓመታት በርካታ ግዙፍ ተግባራትን ያከናወንን ቢሆንም የተንጠባጠቡና ተረባርበን የምናሳካቸው ተግባራት እንዳሉ ሆነው አሁን ባለን የአፈፃፀም ደረጃ እቅዱን ለማሳካት በሚቻልበት መንገድ ላይ ነን ብለዋል፡፡ እቅዱ ተለጥጦ የታቀደና የተለጠጡ ግቦች ያሉት እንደሆነ መዘነጋት እንደሌለበትም አስታውሰዋል፡፡
በህግ የተጠየቁ የግል ፕሬሶች ከምርጫ ጋር በተያያዘ ነው በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን አቶ ሬድዋን እነሱን ለመክሰስ በቂ ምክንያት እንዳለ በመጠቆም ማንም ይሁን ማንም ሃገር የሚያተራምስ ከሆነ ምርጫ ቢኖርም ባይኖረም የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የማይቀር የመንግስት ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡     
መንግስት ይህን እርምጃ የወሰደው ነገሩን በሆደ ሰፊነት በመመልከት የተለያዩ ማስተካከያዎችን አስቀድሞ ለመውሰድ ከጣረ በኋላ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሬድዋን ይህ የመንግስት ሆደ ሰፊነት ገደቡን ሲያልፍ ኃላፊነትን ያለመወጣት ስለሚሆን አጀንዳቸው፣ የጥፋታቸው ዓይነትና ብዛትን ሚዛን በማስገባት የተወሰደ ሕጋዊ እርምጃ መሆኑን አብራርተዋል፡፡             
የኢትዮጵያና የግብፅ ድርድርን በተመለከተ አቶ ሬድዋን ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን ድርድሩ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ የእኛ ራዕይና አቋም ግልፅ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን የግብፅ ህዝብ ጥቅም ለመጉዳት ሰርታ አታውቅም ያሉት ሚኒስትሩ ወደ ግብፅ የሚፈሰው ውሃ አሁንም ፍሰቱን ጠብቆ ይቀጥላል ነው ያሉት አቶ ሬድዋን፡፡ ከአቋማችን ጋር የሚጋጭ ነገር ቢመጣ አንደራደርም በማለትም የመንግስትን አቋም አስገንዝበዋል፡፡

በተቃዋሚዎች በኩል አባሎቻችን እየተሳሩብን ነው በማለት የሚቀርበውን ክስ አስመልክቶም አቶ ሬድዋን ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ጉዳዩ በግል የሚፈፀሙ ህግን የጣሱ ተግባራት በመሆናቸው በግሉ ህግ የሚጥስ ካለ መጠየቁ የማይቀርና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይም የገዥው ፓርቲ ብቻ መሆን እንደሌለበት አስረድተዋል፡፡

Friday, August 15, 2014

IGAD Special Envoys condemn continued fighting in South Sudan

15 August, 2014, Addis Ababa - The IGAD Special Envoys for South Sudan received  reports from the IGAD Monitoring and Verification Mechanism (MVM) on heavy  fighting that ensued this morning in Bentiu from 6.20 a.m to 10 am. The Envoys condemn in the strongest terms the continued flagrant violation of the Cessation of Hostilities Agreement that was signed on 23 January 2014 by the Government of the Republic of South Sudan (GRSS) and SPLM/A – In Opposition.

The IGAD MVM is currently carrying out investigations to establish details of the fighting which will expose the culprit, as continued violations of COH on ground continue to undermine the ongoing peace process in Addis Ababa.

The Special Envoys are particularly dismayed by the latest fighting that happened just days away from the IGAD Assembly of Heads of State and Government summit meeting, and less than 48 hrs after the departure of the UN Security Council team that visited the region.

The Special Envoys once again call on the parties to adhere to the provisions of the Cessation of Hostilities Agreement and demonstrate full commitment to the ongoing peace process. The Special Envoys also reiterate that military advances to gain more ground by any party will not achieve anything except to worsen the already catastrophic humanitarian situation and to cause further devastation

Wednesday, August 13, 2014

መለስ-በህያው ስራህ አሁንም ህያው ነህ!

በአሜሳይ ከነዓን
እለተ ማክሰኞ 2004 ዓም ነሃሴ ወር አጋማሽ የዓለም ህዝበ ከባዱንን መራሩን የመርዶ ዜና ሰማ፡፡ ጆሮውን ማመን የተቸገረ የሀገሬው ህዝብ እዚህም እዚያም እየደወለ የሰማሁት እውነት ነው ሲል ሲቃ እየታገለው ያረጋግጥ ጀመር፡፡ የማይታመን ምናልባትም ሁሉም ሰው ሊሰማውና ሊያምነው የማይፈልገው ከባድ እውነት ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ተወዳጅ መሪ! የአፍሪካ አንደበት ብልሁንና አስተዋዩን ሰው ዓለም በዚች እለት ከመዳፏ ተነጥቀች፡፡ ጓድ መለስ ዜናዊ እንደ ዓይኑ ብሌን ይመለከተው ከነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ በአካል ተነጠለ፡፡ ይህንን እውነታ ለመቀበል የተቸገረው የሀገሬ ህዝብ ልጅ አዋቂው በእንባ ተራጨ፡፡ ሴቶች ልጃችንን፣ አባታችንን፣ ጠበቃችንን አጣን ሲሉ በምሬት እንባቸውን አዘሩ፡፡ የጓድ መለስ ወዳጅና አድናቂ በሙሉ የተፈጥሮ ህግን አሜን ብሎ ለመቀበል ተቸገረ፡፡ ለምን? ሲል ወደ ሰማይ እያንጋጠጠ ፈጣሪውን ተማፀን፡፡ የሀገራት መሪዎች ከጫፍ እጫፍ ተነቃነቁ፡፡ በእርግጥም ዓለም አንድ ታላቅ ሰው አጣች ሲሉ በየፊናቸው ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ እልፍ ህዝብ ከዳር እዳር ተሰልፎ በአንድ ልቦና እንባ እየተራጨ የሸኘው ተፅእኖ ፈጣሪ ታላቁ የህዳሴአችን መሀንዲስ ጓድ መለስ ዜናዊ፡፡

ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ምን ሊውጠን ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀው ነበር፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በተለያየ የዓለማችን አካባቢዎች የሚገኙ ፀሐፊያን ከመለስ ህልፈት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በስፋት ማተቱን ተያያዙት፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን ያንንም ያንንም ለማለት ጊዜ አልነበረንም፤ ሁላችንም በሀሳብ ባህር ሰጠምን፡፡ ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች ብለው ሟርታቸውን ይነዙ ለነበሩ ሟርተኞች ህዝቡ አንድ ሆኖ እንደ ብዙ፣ ብዙ ሆኖ እንደ አንድ በመተጋገዝ ሀገራችን ቁልቁል እንዳትመለስ በመትጋት ፅናቱን ለዓለም በተግባር ለማሳየት ከጠለቀበት ጥልቅ የሃሳብና የሰመመን ባህር ባትቶ ተነሳ፡፡ በአንድ ድምፅም መለስ በህይወት ዘመኑ ተስፋን እንጂ ተስፋ መቁረጥን ያላስተማረ ጀግና መሪ በመሆኑ “ህያውነትህን ስራህን በማስቀጠል እናሳያለን” ሲል ከመስዋእቱ ማግስት ከዳር ዳር በቁጭት ተነሳ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከታጋይ መለስ ዜናዊ የተቀበልነው የህዳሴ ቃልኪዳን አለንና የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ቃልኪዳናችንን እንደገና በማደስ ወደፊት መገስገሱን ተያያዝነው።

የሀገራችንን ህዝብ ከድህነት ቀንበር ነፃ ለማውጣት የሀገር በቀል ፖሊሲና ስትራቴጂ መሀንዲሱ በጓድ መለስ ሃሳብ አመንጭነት የተቀየሱት ፖለሲና ስትራቴጂዎች በላቀ ሁኔታ በመተግበራቸው የጀመርነው የህዳሴ ጉዞ በተያዘው አቅጣጫና ፍጥነት ቀጥሏል። የሀገራችን ዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ 550 የአሜሪካን ዶላር ከፍ በማድረግም ከድህነት ወለል በታች ያሉ የሀገራችን ዜጎች በ2005 ዓም ወደ 26 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ የባለራዕዩን አደራ ጠብቀን መገስገሱንም ተያይዘነዋል።

ጓድ መለስ ድህነትን ከጫንቃችን እስከምናወርድ ድረስ እረፍት ሊኖረን አይገባም የሚል አቋም በተደጋጋሚ ሲያሰማ የነበረ የእድሜ ልክ ታጋይ ነበር፡፡ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ደግሞ የመላው ህዝባችን ርብርብ ወሳኝ መሆኑን ሳይጠቅስ አያልፍም፡፡ በተለይ ወጣቶች አፍላው ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ለሀገራቸው ልማት ማዋል እንዳለባቸው ደጋግሞ ይመክር ነበር፡፡ ከወጣቶች ጋር በተደረጉ የተለያዩ መድረኮችም ሁሉንም እንደየደረጃው እና እንደየአመጣጡ መቅረብና ማስተናገድ የሚያውቀው ጓድ መለስ ወጣቶችን ከጎናችን አድርገን መጓዛችን ግዴታችን ነው፣ ያለእናንተ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሃገር አትለማም፣ እናንተ የነገ ሃገር ተረካቢ የኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ናችሁ በማለት ያለወጣቱ ተሳትፎ ልማት ፍፁም ማሰብ እንደማይቻል በተደጋጋሚ ሲናገር ይደመጥ ነበር፡፡ ለጓድ መለስ አርቆ አሳቢነትና የተሟላ ብስለት ሁሌም አክብሮት ያላቸው ወጣቶች ታዲያ ተደራጅተው ሃብት በማፍራት፣ አርሰውና አዘምረው ጥሪት በማከማቸት በከተማም ሆነ በገጠር የመሪያቸውን ራዕይ በማሳካት አኩሪ ተግባር መፈፀሙን ባህል እያደረጉት  ነው፡፡

አገር የምትለወጠው ያለማመንታት ተግቶ በመስራት በመሆኑ ዛሬ ዛሬ በሀገራችን የማይሰሩ እጆች እየተመናመኑ ሄደዋል፡፡ የሀገራችን ወጣቶች በተፈጠረላቸው ምቹ የስራ እድል ተሰማርተው የሀገራችንን ህዳሴ የሚያበስሩ የለውጥ ሃዋርያ እየሆኑ ነው፡፡ መልካምነትንና ልማትን፤ ለሀገር ሰርቶ ለዘመናት ሲያሸማቅቀን ከነበረውና ብሔራዊ ክብራችንን ዝቅ በማድረግ ሲያዋርደን የነበረውን ድህነት በመፋለም አዲስ ታሪክ መስራት እንዳለብን ያስተማረንን ታጋይ መለስ ዜናዊን በስራችንና በመለወጣችን ሁሌም እንደዘከርነው እንኖራለን፡፡

ወጣቶች የተረጋጋች፣ አስተማማኝ ሰላሟ የተረጋገጠባትና በወጣት ላይ እምነትና ክብር ያላት ሀገር እንድትሆን የታገለላቸውን መሪ ራዕይ ለማሳካት ከመስዋእቱ ማግስት በቁጭት ተነስተዋል፡፡ በተግባርም ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በየተሰማሩበት እየታገሉ ይገኛሉ፡፡

ጓድ መለስ ሀገራችን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ መሸጋገር የምትችልበት መደላድል እንዲፈጠር ቀን ተሌሊት ሰርቷል፣ ለፍቷል፡፡ እድገታችንን የሚመጥን ፈጣንና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅማችንን ለማሳደግ በእኛ አቅም የማይታሰቡ የሚመስሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እውን በማድረግ በአመራርነት ዘመኑ ያስተማረን የይቻላል ባይነት እና የአይበገሬነት አርማችን ጭምር ነው፡፡  

የማይታሰብና ተረት ተረት የነበረው የአባይ ወንዝ ለልማት የሚውልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ለሀገር ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ አስተዋፅኦ አልፎ የአካባቢውን አገራት ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ትስስር ጭምር የሚያጠናክር ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲመኙት ነገር ግን በምኞች ብቻ ታጥሮ የኖረው የህልም ዳቦም ዛሬ ላይ እውን ሆኗል፡፡ ህዝቡ ለአባይ ያለውን ቁጭትንጉርጉሮ በመደርደር ከመግለ ወደ ተግባር ምዕራፍ በመሸጋገር አባይን ለልማት እንዲተባበር እያስገደደው ነው፡፡ አሁን ዜማው፣ ቅዳሴውና ሶላቱ ሁሉ ልማት ሆኗል፡፡ ለሩቅ አሳቢው መሪያችን ምስጋና ይጋባውና ኢትዮጵያ የራሷን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብሩ በርካታ ዓበይት ፕሮክቶችን የምትተገብርበትን አቅም ገንብታለች፡፡ ይህም ጓድ መለስ በበርካቶች ልብ ውስጥ በማይፋቅና በማይደርቅ የህይወት ቀለም ታትሞ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ አሁንም መላው የሃገራችን ህዝብም ከዳር እዳር በመነቃነቅ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጨምሮ በታጋይ መለስ የተጀመሩትን ታላላቅ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ በትጋትና በከፍተኛ ወኔ እየሰራ ይገኛል፡፡ ህዝቡ በሚያስገርም ሁኔታ በጉልበቱ፣ በእውቀቱና በገንዘቡ ግድቡን እየደገፈ ይገኛል፡፡ የግድቡ ግንባታም ዛሬ ላይ 38 በመቶ መድረስ ችሏል፡፡

ጓድ መለስ ለሀገሩ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ታማኝ አንደበት በመሆን ሳይታከት አገልግሏል፡፡ አፍሪካውያን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለአህጉራቸው ዘላቂ ልማትና ተሰሚነት በአንድነት መነሳት እንደሚገባቸው በፅናት በመታገሉ የአፍሪካውያን የወንድማማችነት መንፈስ በቀጣይነት ማደስ የሚያስችል መሰረት መጣል ችሏል፡፡ ዛሬም ድረስ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያ ጎረቤት ሃገራት ከጎናቸው የማይነጥሏት ለሰላማቸው በእጅጉ የሚፈልጓት ቀዳሚ ተመራጭ ሃገር መሆን ችላለች፡፡ ለጎረቤት ሃገር ሱዳንና ሶማሊያ ዘላቂ መረጋጋት ዋጋ እየከፈለች ያለች ሃገር ናት፡፡ በአህጉራዊ ድርጅቶች ላይ ያላት ተደማጭነት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

ከሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት አሁንም የውጭ ጉዳይና የብሔራዊ ደህንነት ፖሊሲያችንን መርህ የተከተለ ነው፡፡ የሀገራችን ዋነኛ ጠላት ድህነት መሆኑን አንጥሮ የሚያስቀምጠው ፖሊሲያችን የምንዋጋውም የምንረባረበውም ድህነትን ለማስወገድ በመሆኑ በማንኛውም ሁኔታ የራሳችንን አቋም በግልፅ ማራመድ የሚያስችለን ፖለቲካዊ ስብዕና መገንባት ችለናል፡፡ ዛሬም ፀረ ሰላም ሃይሎችን በማያዳግም መልኩ መመከትና ማምከን የሚችል ስብዕና እንዳለን በተደጋጋሚ እያሳየን እንገኛለን፡፡ ሰላም በሌለበት ያ ሁሉ የምናስበው ልማት፣ ዴሞክራሲና ብልፅግና በፍፁም አይታሰብምና!

በፀረ ድህነት ትግላችን ላይ የተጋረጠውን የሀይማኖት አክራሪነትና የአሸባሪነት አደጋ መመከት የሚችል ህዝብ ሆነናል፡፡ በጠንካራ መሰረት ላይ የገነባነው በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን የእግር እሳት የሆነባቸውና የመሪያችን ሞት ሀገራችንን ወደ ቀውስና ሁከት የሚወስዳት አድርገው በመመኘት ያልሙ የነበሩትን ህልማቸውን ቅዠት አድርገን ዛሬም አንድነታችንን ጠብቀን አብበን እየቀጠልን ነው፡፡ የህዳሴ ጉዞአችንን በማፋጠንም የታላቁ መሪያችንን አደራ ለመወጣት በከፍተኛ መነሳሳት እየተረባረብን ነው።

የሀገራችን እድገት ደምቆና ጎምርቶ ወደ ፊት እየተምዘገዘገ፣ ሰላማችንን መላው ህዝባችን ዘብ ሆኖ እየጠበቀ፣ የመንገድና የባቡር ግንባታ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል የህዘቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በቀጣይነት በመሻሻል ላይ ነው፡፡ በገጠር የተፋሰስ ልማቱ ባሰብነውና ባቀድነው ልክ እየተጠናከረ ሄዷል፡፡ የአረንጓዴ ልማት ስራችን ላፍታም ከግባችን ሳይነጠል እየተተገበረ ይገኛል፡፡ የሰብል ምርትና ምርታማነታችን ጨምሯል፡፡ ሀገራችን ብሩህ ተስፋ ያላት ሃገር ሆናለች፡፡ ጓድ መለስ፣ ድህነትን ከእግራችን ስር የማድረግ ህልምህ በእኛ በልጆችህና በጓዶችህ እውን የሚሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡


ትፈራርሳለች የተባለችውን ሃገር ወጣትነትህ ሳይገድብህ ከጥቂት ቆራጥ የህዝብ ልጆች  ጋር በመሆን መስዋዕት ከፍለህ በሁለት እግሯ አቁመሃታልና ሁሌም ስምህ ከመቃብር በላይ ዘላለም ሲነሳ ይኖራል፡፡ በህያው ስራህም ህያው ሆነህ በልቦናችን እናኖርሃለን። እኛም አደራህን በመወጣት የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለመገንባት በአንተና በእነዚያ አእላፍ ቆራጥ የህዝብ ልጆች ስም ቃል ገብተናልና ቃላችንን በተግባር እንጠብቃለን፡፡ 

የመለስን ሌጋሲ ለማስቀጠል አካዳሚው የላቀ ድርሻ እንዳለው ተጠቆመ

የመለሰ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአቶ መለስ ዜናዊን ሌጋሲ ለማስቀጠል ካለው ፋይዳ አንፃር የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው ህዝብ ለአካዳሚው ግንባታ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ሰልጥነው የሚወጡ የአካዳሚው አመራሮችን ውጤታማነት መከታተልና መደገፍ እንደሚገባ  አካዳሚው አስታወቀ፡፡

በመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ  የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ባልቻ እንደገለፁት የመለስ ራዕይ ህዝብ ከድህነት ወጥቶ ማየት፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን በፅናት መታገል፣ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደርን ማስፈን በአጠቃላይ የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ በመሆኑ ይህንን ራዕይ ለማሳካት አካዳሚው በሚኖረው የአመራር ድርሻ ህዝቡ ከጎኑ ሊመሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የአመራር አካዳሚው የህዝብ ልጅ የሆነውን የመለስን ሌጋሲ ለማስረፅ የሚረዳ በመሆኑ ህዝቡ ከልቡ እየደገፈው እንደሆነ ያወሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ 2005 . ከህዝቡ በተደረገ 85 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ድጋፍ የግንባታውን 60 በመቶ ማጠናቀቅ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ 

ህዝቡ ለአካዳሚው የሚያደርገው ድጋፍ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ገልፀዋል፡፡   

ጓድ መለስ ከመሞታቸው በፊት ባዘጋጁት የአመራር ግንባታና የህዳሴ ጉዞ በሚለው ፅሁፋቸው ላይ ኢህአዴግ በየደረጃው ያለው አመራር ሊሰለጥንበት የሚችል የስልጠና ማዕከል ሊኖር እንደሚገባ አቅጣጫ ማሰቀመጣቸውን ያወሱት አቶ ጌታቸው አቶ መለስ በመላው ህዝብና አመራር ዘንድ እየታወሱ እንዲኖሩ ለማድረግ አካዳሚው የሚኖረው ድርሻ የላቀ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን በአካዳሚው በሶስት ዙር 12 ሺህ በላይ ጀማሪ አመራሮች መሰልጠናቸው ይታወቃል፡፡


Tuesday, August 12, 2014

የሙስና ሊቀ ሊቃውንቶች

                                                                                                                                       ዮናስ
ፈረንጅኛው ሳይንቲስት እንዲል ሀበሽኛው ሊቀ ሊቃውንት ይለዋል፡፡ ስማዊ ልዩነቱ  እንደሃገራቸው ይሁን እንጂ ትርጓሜያቸው እና ገቢራዊ ፍቺያቸው ያው ነው፡፡ ሳይንቲስት  ይበሉት ሊቀ ሊቃውንት በመሰረቱ ሰው ነው፡፡ ሳይንቲስቶች እንበለውም ሊቀ ሊቃውንቶች  ሰዎች ናቸው፡፡ እኒህና ሊቀ ሊቃውንቶች የተባሉት ደግሞ በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ  በተማሩበት የትምህርት ዘርፍና መሰል ማህበረሰባዊም ሆነ ሳይንሳዊ ኩነቶች ላይ የበቁ  የነቁ ያወቁ ግን ደግሞ ገና አልበቃንም፤ አላወቅንም ብለው ዘወትር የሚተጉ አይነቶች  ናቸው፡፡ በተለይ በእነዚህ ስያሜዎች የሚታወቁቱ እና መብቃታቸው በተግባር  የተረጋገጠላቸው ግለሰቦች ማወቃቸውና መንቃታቸው ከተወለዱበት፣ ካደጉበትና ከኖሩበት  ቀዬና ሃገር ባሻገርም ለአለም የተረፈላቸው መሆናቸውም እንዲሁ ግልፅ ነው፡፡ 

መብቃታቸውና ማወቃቸው ደግሞ በዋናነት ህዝብን ማዕከል አድርጎ ለህዝብ የሆነና  በየመብቃታቸው ደረጃ ያለውን የሰው ልጆች ችግር የሚፈታ፣ የችግሮች ሁሉ ቁንጮ  የሆኑትን የሚያስወግድና የተሻለና ለሰው ልጆች ምቹ የሆነችን አለም ለመፍጠር መደላደል
በሆኑ ስራዎቻቸውም የሚታወቁቱ ናቸው፡፡  በተለይ እንደኛ ባሉ ደሃ ሃገራት ያሉትን ዘርፈ ብዙ የሰው ልጆች ችግር ለማስወገድ የእነዚህ ሊቀ ሊቃውንቶች መብዛት የግድ መሆኑም እሙን ነው፡፡ የመልካም አስተዳደር  ችግር፣ የፍትህ እጦት፣ የህግ የበላይነት፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል፣ የዋጋ ንረት፣ የኑሮ  ውድነት፣ የቤት ኪራይ፣ የትምህርት ክፍያ፣ የህክምና አገልግሎት፣ ጥራትና ዋጋ መናር 
አገልግሎት አሰጣጥ ወዘተ…እያልን የምንጮህላቸው ጉዳዮቻችን ሁሉ መነሻቸው በዚያም  ተባለ በዚህ ድህነት መሆኑ ላይ ልዩነት የሚኖረው አካል የለም፡፡

ስለሆነም ድህነትን ለማስወገድ በሚረዱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ሳይንሳዊ፣ ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የተለየ አይን የተለየ አፍንጫና የተለየ ጆሮ ያላቸው ጠቢባን  ያስፈልጉናል ማለት ነው፡፡ በእርግጥ ሁሉ ነገር ዜሮ ነው እያልኩ እንዳልሆነ ይታወቅ፡፡ ያም ሆኖ ግን ሃገራችን ያላትን የማይነጥፍ ሃብት መሰረት አድርገን ከድህነት  የምንወጣባቸው ስልቶችን ካበጀን ቆይተናል፡፡ የቆይታችንን ያህል ፍፁም ውጤታችን  ሚዛን አለመድፋቱም ግልፅ ነው፡፡ ለምን? ቢሉ ደግሞ ሊቀ ሊቃውንቶቻችን እና በውሰት  የምናመጣቸው ሳይንቲስቶቻችን፣ መነሻ የሚሆኑን ሳይንቲስቶች ወለድ መፅሃፍቶች  መሰረት ያደረጉት ሳይንሱ (ግብርናው ኢንዱስትሪው፣ ትምህርቱ ጤናው ወዘተ…)ላይ ብቻ  መሆኑ መሰረታዊ ይመስለኛል፡፡ ችግር ፈቺ ሊቀ ሊቃውንቶችን ባመረትን ቁጥር ችግር  ፈጣሪ ሊቀ ሊቃውንቶች መፈልፈላቸውም አይቀሬ መሆኑን የተገነዘብን አይመስለኝም፡፡  ስላልተገነዘብንም በማህበራዊ ዘርፎች ላይ በተለይ በግብረ ገብነት ሙያ፣ በሞራልና  በዜግነት ጉዳዮች ላይ በርካታ ሊቀ ሊቃውንቶች ሳናፈራ ቀርተናል፡፡ አፍርተን ከሆነም  ትንሽ ነው፡፡ ምክንያቱም ችግር ፈጣሪ ሊቀ ሊቃውንቶች በዝተዋልና፡፡ የዚህ ፅሁፍ መነሻ መብዛታቸውን በተጨባጭ ማሳያ ማመላከትና ከችግሩ የምንወጣበትን መንገድ መሻት  ነው፡፡ 

ድህነት መዋጋት የህልውና ጉዳይ መሆኑን ከተናገሩቱ እና ቃል ኪዳን ከገቡቱ ከፊሉ  ሂደቱን ለግል ህልውና መጠበቂያ ማዋላቸው ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትና ህዝብ የሚጮህባቸው ጉዳዮቻችን መነሻቸው ሙስና ነው፡፡ ሙስናን ለመታገል ሊቀ  ሊቃውንቶቻችን ያወጧቸው ህጎች የዘየዷቸው መላዎች እና እየሰጡ ያሉት ስልጠናዎች  ወዘተ…ግን መፍትሄ ያስገኙ አይመስሉም፡፡ በተለይ ከላይ ያሉትና የሙስና ተጋላጭ  በሆኑት አካባቢዎች የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችና ግለሰቦች በአንድ ወቅት ሲያዙና ሲጋለጡ  እሰየው ብለናል፡፡ በእርግጥ ይህ አንዱ የመፍትሄ አካል ነው፡፡ ግን ደግሞ መፍትሄነቱ  እጅግም ስለመሆኑ ለመመስከር የትም ሳንሄድ ጠብ ያለ ነገር እንደሌለ አስተውለን  ለመናገር አይከብድም፡፡ 

ለምን ቢሉ የመፍትሄ መሰረታችንን እሴታችን በሆኑት የሞራልና የግብረ ገብ ጉዳዮች ላይ  አላደረግንምና፡፡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት በየደረጃው የሚገኙ የስራ  ኃላፊዎች ተጠርጥረው ሲያዙ የፖለቲካ ልዩነት ነው ያሉ ቢኖሩም እነርሱም ማለታቸው  ለፖለቲካ ትርፍ ስለሆነ አልፈናቸው የሚበዛው ህዝብ ግን እሰየው ማለቱ የቅርብ ጊዜ  ሁነት ነው፡፡

ያም ሆኖ ግን እነዚህ በይፋ ተይዘው ይፋ ስለወጡ እንጂ በየለቱ በየመስሪያ ቤቱ የቅርብ  አለቆች እስከ ቅርብ ባልደረቦች የሙስና ሊቀ ሊቃውንቶች ሆነው በተለያየ መልኩ  ሲዘርፉና ሲመነደጉበት እንኳንስ ልንተነፍስ ‹‹ፕስስ መነጨቀ›› ብለን ማሞገሳችን እርግጥ  ነው፡፡ ጥያቄው ስለምን ነው ማሞጋገሳችን? ስለምንስ ነው ዝምታችን? የሚለው ነው፡፡ ያም  ይቅር በአንድ ወቅት ታምራት ገለታ በተባለ ‹‹ጠንቋይ›› ሊቀ ጠበብትነት የተጭበረበረውን  እና ሞራላዊ ክስረት የደረሰበትን ሁሉ አይተን ብዙ የተደነቅን ቢሆንም ነገርዬው  በአቋራጭ ለመበልፀግ ሳይለፋና ሳይሰራ ለማግኘት የሚሻ ህዝብ ባለቤት ስለመሆናችንም  ስናስተውል ባልተደነቅን፡፡ በዚህ ሊቀ ጠበብት የተደነቁቱ እና ያጨበጨቡትም ያው  ስለመሆናቸው ደግሞ የትም ሳንሄድ ከሰሞኑ ከአንዲት አፍሪካ ሃገር መጥቶ በሚለኒየም  አዳራሽ ገንዘብ ሊያበዛ እና ሀብት በሃብት ላይ የሚጨምር ፀበልና ዘይት እንዳለው  የተናገረውን ተከትለን መናኮራችንን እና አተርፍ ባይ አጉዳይ ሆነን መቅረታችንን  ያስተዋልን እንደሁ ነው፡፡

ሳሙኤል ዘሚካኤል የሚባለውን ቁጩ ዶክተርና ኢንጂነር የፈጠረልንም የኛ የሞራል  ደረጃና እሴታችንን መሰረት ያደረጉ ሊቀ ሊቃውንቶች በማጣታችን ነው፡፡ በአቋራጭ  የመበልፀግ ፍላጎታችንን ያሳየን የሳሙኤል አፈጣጠር ብቻ ሳይሆን በተጋለጠ ወቅት 
አድናቆትን መቸራችን እና መሰስ ብሎ ሲወጣ ዝም ያለው እና ይመለከተዋል ብለን  የጠበቅነው አካል ሁኔታም ነው፡፡ እርሱም ይቅር ሳሙኤል ብዙዎችን ማታለሉ እና  ሳይሰራ ሳይለፋ በብዚ ሺህዎች የሚቆጠር ገንዘብ መቀበሉም ይፋ ሆኗል፡፡ ግን ደግሞ በብዙሃን መገናኛ የሰማናቸው ግለሰቦች ህግ ፊት ቀርበው ሊመሰክሩና ክስ ሊመሰርቱ  ያለመቻላቸው ነገር ቢፈተሽ መቼም ይውሰደው አድናቂው ነን፤ ምንም አይጎዳንም ብለው እንደማይሆን አይጠረጠርም፡፡ ሚዛን የሚደፋው እና የሚጠረጠረው የዝምታ ግምት ከየት  አመጣኸው ሽሽትን ይመስላል፡፡ ወይም ስምና ዝናን ከሃገር ጥቅምና ከህግ የበላይነት  የማስቀደም ጉዳይ ነው፡፡ ከሁለቱ አይዘልም፡፡ ይህ ሁሉ ከየት መጣ ቢሉ ደግሞ  ከግብረገብና ሞራል ሊቀ ጠበብቶቻችን የሙስና ሊቀ ጠበብቶቻችን መብዛታቸው ነው፡፡ 

ሶማሊያ የምትባል ሃገር ስትነሳ ሁላችንም መቼም የትርምስ፣ የሽብርተኝነት መፈልፈያ  ስራ የማይሰራባት የተኩስ አውድማ መሆኗ ቀድሞ በጭንቅላታችን መምጣቱ አይቀርም፡፡  ሶማሊያ እንዲህ የሆነችው የጦርነት፣ የሽብርተኝነትና የትርምስ አራራ ስላለበት
የሚመስለው ካለ ተሳስቷል፡፡ ‹‹ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል›› የተባለ አለም አቀፍ  ተቋም በቅርቡ ይፋ ባደረገው ጥናት በአለም የሙስና ቁንጮ የተባለችው ሀገር ሶማሊያ  መሆኗን አረጋግጧል፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት ሽብርተኝነትና ህግን መገዳደርም ሙስና ወለድ የሆኑ ሁነቶች ስለመሆኑና ሙስና ሲከፋ የመንግስትን ህጋዊ ስልጣንም  በጉልበት እንደሚያስነጥቅ ሶማሊያ ጥሩ ማሳያ እንደሆነች ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በርግጥም ትክክል ስለመሆኑና ሙስና ከጓዳ ወደአደባባይ ሊያውም በመንግስት መዋቅር 
አሰራር ላይ የመሸጋገሩን ሂደትና የሂደቱ ባለቤት ስለሆኑት የሙስና ሊቀ ሊቃውንቶች  አንድ ወዳጄ ሰሞንኛ ገጠመኙን ሲያወራኝ ማረጋገጥ ተችሎኛል፡፡ በዚህ ከቀጠለ ደግሞ በአዋጅና በእቅድ የምንሰራው ሽብርተኝነትን የመዋጋት፤ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ የመናገር  ነፃት፣ የሃይማኖት እኩልነት፤ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ውሃ እንደሚበላቸው የጓደኛዬ  ሰሞንኛ ገጠመኝ ሁነኛ ማረጋገጫዬ ሆኗል፡፡ 

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ‹ፀያፍ›› ገጠመኙን ያወጋኝ ጓዴ እየነገደና ነጋዴው  ከሚሆነውና ህጋዊ ከመሰለው የሙስና ሊቀ ሊቃውንቶቹ የአደባባይ ዝርፊያ አንፃር  እንደሃገሩ መሆን ግዴታዬ ነው ቢለኝም ቢያንስ ከሙስና ሊቀ ሊቃውንቱ ተግባር ተምሯል፤ ደግፏልምና ሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ነው ለኔ፡፡ እኔም ሶስተኛ ተጠያቂ  እንዳልሆን ቢያንስ እንደሙያዬ ጉዳዩን አደባባይ እንዲውል መፃፌ ታሳቢ እንዲደረግልኝ) የእኒህ የሙስና ሊቀ ሊቃውንቶች ቦታ እና ነገርዬው የተከወነበትና እየተከወነ ያለበት ቤት 
ቁንጮዎቹን ይዘናል በተባለውና የነመላኩ ፋንታና ገብረዋህድ ቤት ከነበረው አንደኛው  ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ነው፡፡ አንደኛው ያልኩት ጓዴ ስላልነገረኝ ነው፡፡ (አለመናገሩ  በራሱም ተባባሪነቱን ወይም በዚሁ ተግባሩ የሚቀጥልበት እንደሆነ ያመላክታል) ቦታውን  በተለየ አልነገረኝምና ሊቀ ሊቃውንቶቹንም በስም እንደማይጠቅስልኝ አንባቢያን መቼም  አስቀድማችሁ እንደምትረዱኝ ግልፅ ነው) እዚህ ላይ ግልፅ ሆነን ወደ ሚስተር  ኤክሶቻችን፤ሊቀ ሊቃውንቶቻችን ድርጊት እንዲህ ስናመራ ከጓዴ የሥራ ዘርፍና የጉዳዩን  አፈጣጠር እንጀምራለን፡፡ 

የሙስና ሊቀ ሊቃውንቱ አባሪና ተባባሪ ወይም የወጉ ባለቤት የሆነው ጓዴ በምን ዘርፍ  እንደተሰማሩ ባላውቅም መርካቶ ከሚገኙ ሱቆች የተወሰኑቱ ባለቤት ለሆኑ ነጋዴዎች  የሂሳብ ባለሙያ እና ጉዳይ አስፈፃሚ ነው፡፡ ታዲያም በሆነው አይነት የንግድ ጉዳይ ላይ ሲፒኦ አሰርቶ በዚህና ሊቀ ሊቃውንቱ ባሉበት መስሪያ ቤት ማስገባት ነበረበትና  ያስገባል፡፡ እናም የንግድ ሰው እንዳለመሆኔ ሲፒኦ ተመላሽ የሚሆንበትን አግባብና የጊዜ  ገደብ ባልገነዘብም የተያዘው ሲፒኦ ጊዜ ገደቡ አልፎ ይሁን በሌላ እኔ በማላውቀው ግን ደግሞ ተገቢ በሆነ ምክንያት የሚቀርበትና ወደ መንግስት ገቢ የሚደረግበት እድል  ይፈጠራል፡፡ እንደመንግስት የተያዘው ሲፒኦ ወደመንግስት ገቢ የሚደረግበት ህጋዊ  አግባብ መኖሩን የተረዳው ጓዴ ሲፒኦው ይለቀቅለት ዘንድ የራሱን የንግድና እኔ የማላውቀው ምክንያቶች ይዞ አቤት ሊል የእነዚያን ሊቀ ሊቃውንቶች ደጅ መርገጥ ግድ  ይሆንበታል፡፡ ከሊቀ ሊቃውንቱ አንዱም ያለእርሱ ሊቀ ጠበብትነት በቀረበው አቤቱታ  መነሻነት አንዳች ነገር እንደማይፈጠር አስቀድሞ ያውቃልና ጉዳዩ እርሱን የሚመለከተው  ሆኖ ሳለ ጓዴ ወደሚፈልገው መስመር ይገባ ዘንድ ወደ በላይ አካል ይመራዋል፡፡ ጉዳዩ  ወደተመራበት ክፍል የሄደው ጓዴ ከበላይ ኃላፊዋ በምንም ምክንያት የተያዘው ሲፒኦ  የሚለቀቅበት ህጋዊ መሰረት እንደሌለ እና ችግሩም የራሳቸው የእነጓዴ መሆኑን ‹‹አሳምና›› ሸኘችኝ በማለት ወጉን ቀጠለልኝ፡፡ ስለሆነም የሙስናው ሊቀ ጠበብት  አመቻችቶ ለቆታልና ወደ እርሱ ለተመለሰው ጓዴ እስኪ ነገ ብቅ በልና እገሌን አናግር  ‹‹ይገባና አይገባ እንደሆነ ደውልልኝ ብሎ ስልክ ቁጥሩንም ጨምሮ ጓዴ በያዘው አቤቱታ  ሰነድ ላይ በ‹‹ስታይል›› አስፍሮ ህዝብ ተሰልፎ በሚጠብቅበት መስኮት ያቀብለዋል፡፡ ጓዴ ይኼኔ የሙስናው ሊቀ ጠበብትነት ገብቶታል፤ ለምዶትም ይሆናልና ምሽቱን ወደሊቀ ሊቃውንቱ ስልክ ይመታል፡፡ ከወዲያኛው መስመር ደግሞ ሲፒኦው ሊለቀቅ  የማይችልባቸውን አሳማኝና ህጋዊ አግባብነቶችን ያዳምጣል፡፡ ግን ሊለቀቅ የሚችልበትም  እድል እንዳለና እድሉም ያለው እዚሁና ቀን ያገኘው ሰው ላይ እንጂ ሌላ ጋር  አለመሆኑንም በስልኩ ይሰማል፡፡ አማራጩም ከባዶ የተሻለ እንደሚሆን ጓዴ እንደሚገነዘብ ልምድ የሚያውቀው ሊቀ ጠበብት የሀያ አምስት ሺህ ብር ሲፒኦውን ይወስድ ዘንድ  ወደመንግስት ገቢ የማይሆንበትን ምክንያት አበጅቶ ከምክንያቶቹም አንዱ የወሰደበትን  ቀን ወደ ኋላ ወስዶ በመፈረም በእጁ ላይ ይጥልለት ዘንዳ ጓዴ ደግሞ ሰባት ሺህ ብር  ለሊቀ ጠበብቱ ኪስ ማዋል ግዴታው እንደሆነ ተነገረው፡፡

በእርግጥም እንደአብዛኞቻችን እና ከላይ በተገለፁቱ በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎቶቻችን  መነሻነት ወደፊቱን ሳይሆን የዛሬውን እንደሚያይ የሚጠበቀውና ከምንም አንድ  ሶስተኛውን መውሰድ የተሻለ እንደሆነ የተገነዘበው ጓዴ እሺ ሲል ይስማማና ጉዳዩ ሙስና  ጉቦ ነውና አፈፃፀሙን በተመለከተ ለሊቀሊቃውንቱ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ እንደተለመደውና  እንድምንገምተው እዚህ ካፌ ወይም እዚህ ሆቴል ምናምን ጠብቀኝ ያለ  እንዳይመስላችሁ፡፡ የሙስና ሊቀ ሊቃውንቶች ስል ስያሜ መስጠቴም ለዚሁ ነው፡፡ ‹‹ሰባት  ሺህ ብርህን ይዘህ ጠዋት እንደማንኛውም ባለጉዳይ ተሰለፍ›› ብቻ ነው የሊቀ ሊቃውንቱ ትዕዛዝ፡፡ ስልኩ ተዘጋና ጓዴም እንዳወጋኝ ግራ በመጋባት በጠዋት ተራ ከሚጠብቀው  ባለጉዳይ እኩል ይሰለፋል፡፡ ከዚያም ይህ ፈፃሚ እንደየጉዳዩ ተገልጋዩን በመስኮት እየጠራ  የሚያስተናግደው በድርጀቱ ወይም በንግድ ስም እየጠራ ነው፡፡ እናም እንደባለጉዳዩ  አሰላለፍ የባለጉዳዮች ሰነድም ሰልፍ ይዞ ሊቀ ጠበብቱ እጅ ላይ ነውና የጓዴ ንግድ  ድርጅት ሲጠራ አቤት ይላል፡፡  ልብ በሉ እዚያው ሰልፍ በያዘበት ቦታ ላይ ሆኖ ነው አቤት ያለውና ነገሩም እየተፈፀመ  ያለው፡፡ አቤት አለ ጓዴ፡፡ ሊቀ ሊቃውንቱም ቲን ነበር አልተመዘገበም ይዘሃል? ኧረ  ረሳሁት በቃሌ ግን አውቀዋለሁ ሲልም ጓዴ ይመልሳል፡፡ ሊቀ ሊቃውንቱም በድንፋታ እና  በቁጣ እናንተ ደግሞ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዳንሰጥ የተሟላ መረጃ ይዛችሁ አትመጡ፤ ከዚህ በኋላ የተሟላ መረጃ ያልያዘ ወዘተ… ቀረርቶ ሲያሰማ አዳሜ ሰልፈኛ ያላሟላሁት ይኖር ይሆን ብሎ ቀልቡ ግፍፍ፤ ሀሳቡንም ወደራሱ ሰብሰብ ያደርጋል፡፡ ጓዴም ጉዳዩ  የሙስና ጨዋታው አካል እንደሆነ ወዲያው ገባውና (እዚህም ጋር ልምዱ እንዳለውም ሆነ  የሚቀጥልበት እንደሆነ አስቀድሜ መናገሬ) ባለአራት ይሁን ባለአምስት ዲጂት እርሱም  የማያስታውሳቸውን ቁጥሮች ጮክ ብሎ ይነግረዋል፡፡ 

ሊቀ ሊቃውንቱም በአቤቱታ ሰነዱ ላይ ቲን ነበሩን የሚፅፍ ይመስል አቀርቅሮ  እስኪሪብቶውን ወረቀቱ ላይ አንቀሳቀሰና፤ እንደገናም የደመረም የቀነሰም መሰለና ሰባት  ሺህ ብር ይክፈሉ ይለዋል፡፡ ጓዴም ሰባት ሺህውን ሊቀ ጠበብቶቹ በመንግስት የስራ 
ሰዓት፤ በመንግስት መስኮት፤ በርካታ ተገልጋይ ባለበት በማያስጠረጥር መልኩ ሙስና ላይ  ተጠበው ዘይደዋልና በይፋ ሰባት ሺህውን አስቀድሞ የተዘጋጀ እንዳይመስል እና እንዴትስ  ገምቶ እንዳይባል ከታሰረው አስር ሺህ ብር ላይ ሰባት ሺህ ቆጥሮ በመስኮት ለሊቀ ጠበብቱ ጀባ ሲለው፤ ምንም ከጉዳዩ ጋር ባልተያያዘ ሰነድ ላይ ጓዴን ያስፈርመውና  ሲፒኦውን ይቸረዋል፡፡ ጓዴም እየደነቀው በመሄድ ላይ ሳለ ከቆይታ በኋላ የሊቀ ሊቃውንቱ ስልክ ያቃጭልበታል፡፡ ጓዴም ምን አጎደልኩ ሲል እየተጨነቀ ስልኩን ሲያነሳ  ‹‹ብዙም አልተጨዋወትንም፣ እንግዲህ ሌላ ጊዜም እንገናኛለን፡፡ ፍትህ የተጠሙ እና  ፈጣን አገልግሎት የሚሹ ጓደኞችህንም ላካቸው እኛ መንግስት የጣለብንን አደራ  ለመወጣት ዝግጁ ነን፤ መልካም አስተዳደርና ፈጣን አገልግሎት በመፈክር እና በመግለጫ  ሳይሆን አብሮ በማደግ ተግባራዊ እንደሚሆን መገንዘብ ያስፈልጋል›› ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡  ጓዴም የመቀባበሉን ጨዋታ የለመደ ቢሆንም ያስገረመውና ለእኔ የመንገሩም ሚስጥር  በአደባባይ መስጠቱና ለዚህም የተበጀው ዘዴ ሳይሆን ቢያንስ ሆዳቸው የሚያውቀውን  ህገወጥ ድርጊት ህጋዊና ይልቁንም የመንግስት አደራ እንደሆነ ሊቀ ሊቃውንቱ ሳያፍር  ማውጋቱ ነው፡፡ እኔም ገርሞኝ ሳለ አንድ ደግሞ ልጨምርልህ አለኝና እንዲህ የሙስና  ሊቀ ጠበብቶችን ‹‹የጥበብ ደረጃ›› እንዲህ ይተርክልኝ ገባ፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህና ከላይ  ከተመለከትነው ሊቀ ጠበብት ጋር ጓዴ ጓደኝነቱን እንደቀጠለና ሌሎችም አገልግሎት  የራቃቸው ጓዶች እንደሚልክለት ጭርሱንም መበዳደር እና መገባበዝ ደረጃ ላይ የደረሰ  ጓደኝነት እንደመሰረቱም አውግቶኛል፡፡ አደጋው እንዴት እየሰፋ እንደሚሄድ ልብ በሉ፡፡ ወደገጠመኝ ሁለት የጓዴ ትርክታችን እናምራ፡፡ ጓዴ የሚያማክራቸውና ከላይ ለተመለከተው ጉዳይ ባለቤት የሆኑት በንግድ ስራ ላይ  ተሰማርተው የሚገኙት ነጋዴዎች በጥምረት ደግሞ በሪል እስቴት ይሰማሩ ዘንዳ ጥናት  አስጠንተው አስፈላጊውን የጥምረት ውልና የህግ ስምምነት ከከወኑ በኋላ የከተማው አስተዳደር ለዚህ ዘርፍ ካዘጋጃቸው መሬቶች ስሙን ባልነገረኝ አካባቢ የሚፈልጉትን ካሬ  ስፋት መሬት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ዘርፉ እንደመበረታታቱ እና  እነርሱም አስፈላጊ የህግ ሰነዶችን እንደመያዛቸው ወደ ስራ ለመግባት ብዙም ጊዜ እንደማይወስድ የተገነዘቡት ተጣማሪ ባለሃብቶች ጓዴ እና ሁለት በሌላ የስራ መስክ  ለባለሃብቶቹ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ባሉበት ተጣማሪዎቹ ላቀረቡት  የካሬ ስፋት ቦታ በአስተዳደሩ መረጃ መሰረት በጀት ለመያዝና ስለአፈፃፀም ሁኔታ ቃለጉባኤ ይዘው ውይይት ይቀመጣሉ፡፡ ቃለጉባኤ ያዡ ደግሞ የዚህ ወግ ባለቤት ጓዴ  ነው፡፡ 

እናም ባለው መረጃ መሰረት ላቀረቡት የመሬት ጥያቄ አምስት መቶ ሺህ ብር ቅድሚያ  መከፈል ስላለበት ያለምንም ተቃውሞና ክርክር በጀቱን ያፀድቃሉ፤ ግን ደግሞ  የተለመደው ተከፍሎም ወዲያው ወደስራ ለመግባት ለመንግስት ገቢ ከሚደረገው አምስት መቶ ሺህ ብር ከፊል ያህል ጉዳዩን ፈፃሚ ለሆኑት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መግባት  ስላለበት፤ ሁሉም ቦታ ሊቀ ሊቃውንቱ አሉና ለእነርሱም የባለሃብቶቹ ጉባኤ በጀት መያዝ  ነበረበት፡፡ ያም ሆኖ ግን በግልፅና እነጓዴ ባሉበት አይሆንም፡፡ ግን ለስራቸው ቅልጥፍና  ሲሉ መሆንና በቃለ ጉባኤም መያዝ ነበረበትና ለጉቦ ሳይባል ለተለያዩ ጉዳይ ማስፈፀሚያ  እና ስራ ማስኬጃ የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ይፀድቃል፡፡ በጥቅሉ  ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ይያዛል፡፡ ይህንንም ተከታትለውና ክፍያ ፈፅመው የመሬት ርክክብ ያደርጉ ዘንድ ጓዴን ጨምሮ የተቀሩት ሁለት አማካሪዎችን የባለሃብቶቹ ጉባኤ 
ይወክላል፡፡

ጉዳዩና በህግ አግባብ ያቀረቡት ጥያቄና በመንግስትም የመሬት ሰነድ ላይ ያለው አምስት  መቶ ሺህ ብር እንደሆነ በግልፅ የሚገነዘቡት ጓዴና ጓዶቹ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህው  ለምን እንደሆነ ስለገባቸው እነርሱም በተራቸው ሊቀ ጠበብት መሆን ይሹና እያንሰላሰሉ  ወደ ቢሮው ያመራሉ፡፡ በጥያቄያቸው መሰረት ሰነዳቸው እንዳለቀ እና ክፍያ ፈፅመው  መሬቱን መረከብ እንደሚችሉ የነገራቸው ሊቀ ሊቃውንት ስንት እንደያዙ ይጠይቃል፤ እዚያው በቢሮውና በግልፅ ሌላ አገልግሎት ፈላጊ ባለበትና ሌሎች ሰራተኞች ባሉበት፡፡  (ቢፒአር ተብሎ ሁሉ ነገር ፊት ለፊት መሆኑ ሙስናን ለመከላከል ሊቀ ጠበብቶቻችን  ያመጡትን ዘዴ ከእነርሱ የሚከፉት ሊቀ ጠበብቶች ደግሞ እንዲህ አደረጉት) እነ ጓዴ  በየድርሻቸው ሊቃረጡ እነርሱም አለቆቻቸው ላይ ሊቀ ጠበብት ሊሆኑ ቢሹም ስድስት  መቶ ሺህ በቂ እንዳልሆነ እና አሰራሩም የዋናውን ከፊል እንደሆነ በአለቆቻቸው መቼና 
እንዴት እንደሆነ ባያውቁትም እንደነገሩና መስማማታቸውንም ይገልፅላቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ  እርሱን ሳይሆን ማጋለጥ ቢፈልጉም አለቆቻቸውን እንደሚሆን እንዲያውም አስቀድሞ  የተሰጣቸውን ከመፈፀም የዘለለ ሚናም እንደማይኖራቸው የኃላፊው መልዕክት 
አረጋግጧልና ያለአንዳች አተካሮ እንደሚስማሙም ኃላፊው ያውቃልና፤ ጓዴ  እንደነገረኝም የኛም ሌላ መሻት በፈጠረው ክፍተት እንጂ አሰራሩ ስለሆነ ከሂሳብ ጋር  የተያያዘ ጥያቄ እዚያ አይነሳም፤ በማንሳታችንም አፈርን አለኝ፡፡ ከዚያም ሊቀ ሊቃውንቱ ሰባት መቶ ሺህ ብር ካሸሯ ጋር ክፈሉና ሪሲት ይዛችሁ ኑ ሲለን ደግሞ ዋጋው  ነው ብለን ተደናግጠን ልንሞግት ነበር፤ ምክንያቱ ደግሞ በሰነዱ የተመለከተው አምስት  መቶ ሺህ ብር ሆኖ ሳለ ሰባት መቶ ሺህ ብር ካሸሯ ጋር ክፈሉ ሊለን አይገባምና ብለን  ነበር፡፡ ያም ሆኖ ደግሞ የእነርሱ ጥበብ አያልቅምና የት ድረስም እንደሚረዝም ከልምድ  ተረድተናልና የተሰጠንን ሰነድ ይዘን ካሸሯ ጋር ገባን፡፡ ሰነዱን አይታ ምንም  እንልተፈጠረ ኮስተር ብላ እዚህ ላይ ፈርም አለች፡፡ ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ስትልም  አስከተለች፡፡ ቼኩን አስረክበን ደረሰኝ ሰራችና አስፈርማ ሰጠችን፤ ደረሰኙ ደግሞ አምስት  መቶ ሺህ ብር ነው የሚለው፡፡ ከዚያም የመንግስትን እዚያው በገዛ ሳጥኑ የሊቀ ሊቃውንቱን ድርሻ ደግሞ በየአካውንቱ ቼኳን መንዝራ በተን፤ በተን ነው ጨዋታው ሲል  አወጋኝ፡፡

ስለሆነም አሁን ጨዋታው በመንግስት ሰነድና በመንግስት ሰአት በአደባባይ እንጂ በስውር  ምናምን ለሰጪውም ለተቀባዩም የማይመች ሆኗል፤ ሌላውንም ለእስር የዳረገው ይኸው  እንደሆነ የተረዱት የሙስና ሊቀ ሊቃውንቱ ሌላ መላ ዘየዱና በገዛ በራሱ በመንግስት ቢሮ  ሙስና ላይ ተጠበቡ፡፡ ደረሰኙ አምስት መቶ ሺህ ብር ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ሰጠሁ፤ ብሎ ቢጮህ ደግሞም እኮ እንዴት ሊጮህ አለቆቹ ሰጥተውታል፤ ጠበብቶቹ የማህበረሰቡን  በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት ደረጃ ጠንቅቀው አውቀዋል፡፡ ታምራት ገለታ  የተጫወተበትን ህዝብ፣ ሁለተኛ አላሙዲ ተብሎ የመጣውና በአካውንቱ አምስት ሺህ ብር  ብቻ የተገኘው ግለሰብም ከምሁር እስከ ባለሃብት ከድምፃዊ እስከ ሞዴል ከዝነኛ እስከ  ምናምን ያሞኘውን ህዝብ፣ በልዩ የአቀራረብ ስልቱ በፋክት መፅሄት ላይ ‹‹የጎመጀ ህዝብ››  ሲል በብር አብዢውና በፈዋሹ ፓስተር የተሸወደውን የጎመጀ ህዝብ የኃይለጊዮርጊስ ማሞ 
ፅሁፍ ያጤነ ህዝብ፣ ለሳሙኤል ዘሚካኤል ኢንጂነር ወዶክተር ልዩ ብቃት ከሊቅ እስከ  ደቂቅ ከመዋእለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ተቋም ከምሁር እስከ ፕሮፌሰር ያጨበጨበና  ያልተጠራጠረ ህዝብ፤ የተገነዘቡት ሊቀ ሊቃውንቶች፡፡ ሙስና በቴሌቪዥን ድራማና  ማስታወቂያ ሊቀ ጠበብቶቻችን ፍልስፍና እንደማይገታ ቀድመው ተረድተዋልና  የሞራልና ግብረገብ ሊቀ ሊቃውንቶች ተፈልፍለው፤ ነገን የሚያስቡና የስራን ክብርና  ኃላፊነትን የተገነዘበ ትውልድ እስኪመጣ፣ ማታ አባቱ ያልዘራውን ሲያጭድ የሚያመሽ  ትውልድ እስካለ ሙስና ላይ ከዚህ በላይ ቢጠበቡም አይገርመንም፤ የሚያሳስበን ነገር ግን  አለ፡፡ ሶማሊያ የሆነችውን የሆነችው እንዲህ ባለ ሂደት ነው፤ ስለሆነም ከመግለጫ ከእስርና  ከማስታወቂያ የሚያላቅቁንና ማህበረ መሰረታችንን መሰረት ያደረጉ መፍትሄ  የሚያመጡልን ሊቀ ጠበብቶችን እንሻለን፡፡ 

Monday, August 11, 2014

“መለስ! ሀገራችን ለዓለም ያበረከተችው የህዳሴ መሪ”

በልጅ አኪናሆም
በአለማችን ውስጥ ከ194 በላይ ሀገራት እውቅና አግኝተው ህዝባቸውን እያስተዳደሩ ይኖራሉ። እነዚህን ሀገራት ለማስተዳደር እድሉን ያገኙ አንዳንድ መሪዎች ለህዝባቸው ጠብ የሚል ነገር ሳይተዉ ለራሳቸው እንደባዘኑ፤ ሀገራቸውን በልማት ወደ ፊት መግፋት ሳይችሉ ያልፋሉ። ሌሎች ደግሞ ለህዝባቸው ሰርተው የተመዘገበውን ልማታዊ ለውጥም በአይናቸው ተመልክተው ይቺን አለም ይሰናበታሉ። ጥቂቶች ግን ለህዝባቸው እንደባተሉ፤ ከሀገራቸው አልፈው አለምአቀፋዊ ተፅዕኗቸው ድንበር ሳይገድበው አሻራቸው በጉልህ የሚታይ ሆኖ እናገኘዋለን። ለዚህ አገላለፄ የቀድሞው የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጥሩ ማሳያ ናቸው፡፡ አቶ መለስ ብዙ በሚሰሩበት እድሜያቸው ከአጠገባችን  የራቁ ቢሆንም አይረሴና ዘመን ተሻጋሪ ስራቸው ዛሬም ነገም የሚታወሱ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህንንም እንኳን እኛ ኢትዮጵያውያን መልካምነታቸውን ማጣጣም የቻልነው ይቅርና    የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ታላላቅ ሰዎች አቶ መለስ አይረሴ መሪ መሆናቸውን ደጋግመው መስክረውላቸዋል፡፡ ስለእርሳቸው የተባሉትን ነገሮች በሙሉ መዘርዘሩ አዳጋች ቢሆንም በወፍ በረር ጥቂቶቹን ላስቃኛችሁ፡፡

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የቤኒን ፕሬዚዳንት ቦኒ ያያ የአቶ መለስ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ ለአፍሪካና ለአለም የነበራቸውን አስተዋፅኦ ሲናገሩ “ለአፍሪካ ሁለተናዊ ነፃነትና ብልፅግና የታገሉ በዚህ ድንቅና ወደር የማይገኝለት አስተዋፅኦም የአፍሪካ ህብረት የተመካባቸው የፓን አፍሪካኒስት ኃይል” በማለት ገልፀዋቸው ነበር። ሊቀመንበሩ አቶ መለስ አፍሪካ የራሷ የፖሊሲና አማራጭ የእድገት መስመር እንዲኖራት ለማድረግ ብዙ ሞግተዋል፤ ሳይሰለቹ ለማስረዳትና ለማሳወቅ ደፋ ቀና ብለዋል ነበር ያሉት። በበርካታ አለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካን ልኡካን ቡድን በመምራትም አፍሪካን ወክለው በቡድን 8፤ በቡድን 20፤ በአለም አቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች፤ በአፍሪካ ቻይና፤ አፍሪካ ህንድና የአፍሪካ አውሮፓ ብሎም የአለም የኢኮኖሚ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የሀገራቸውና የአፍሪካ መብት እንዲጠበቅና ባንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ  ማድረግ ችለዋል በማለት ነበር ቦኒ ያያ ስለአቶ መለስ ምስክርነታቸው የሰጡት።

ለአፍሪካ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በተመለከተ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሚሶቬኒም ይህን አሉ “ የኔፓድ ሊቀ መንበር ሆነው ያገለገሉት መለስ ዜናዊ አፍሪካ የእድገት ማዕከል ሆና እንድትወጣ ያስቻሉ መሪ ናቸው” በእርግጥም ከአድዋ የነፃነት መንደር ብቅ ያሉት የያኔው ጨቅላው መለስ አድገውና ተመንድገው ሀገራቸው በልማት ጎዳና እንድትራመድ ከማስቻል አልፈው ለአፍሪካውያን የልማት መፍትሄ ይሆን ዘንድ የኔፓድን ሀሳብ በማመንጨትና በመምራት ብዙ ተራምደዋል፤ ብዙ ሰርተዋል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮቭ ዙማ ደግሞ በአቶ መለስ ሞት ላይ ተገኝተን እየሰጠነው ያለነው ክብርና አድናቆት በህይወት ስለተለየን ብቻ የምንናገረው አይደለም በማለት አፅንኦት በመስጠት ንግግራቸውን ጀምረዋል። “ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በህይወት ዘመናቸው ለሚሊዮን አፍሪካውያን እና ለአለም ህዝቦች ህይወት መሻሻል ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ስናከብረው እንኖራለን” ሲሉም ዙማ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። አቶ መለስ ተጋባዥ በሆኑባቸው አለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተው የሚሰጧቸው ገንቢ ትችቶች፤ የሚያቀርቧቸው የመፍትሄ አማራጮች፤ የቃላት አጠቃቀማቸው፤ የመሪነት ግርማ ሞገሳቸው፤ እንግዳ አቀባበላቸው፤ ፈገግታቸውና ሰው አክባሪነታቸው በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ እንዲታወሱ የሚያደርጋቸው ነውና  የህልፈተ ህይወታቸው ዜና መሰማት ለእኛና ለበርካታ ሃገራት መሪዎች ሀዘናችንን መሪር አድርጎታል። በእለተ ህረፍታቸው ጃኮቭ ዙማ ያደረጉት ንግግርም ይህን ነው የሚያመላክተው፡፡ “ማንኛውንም ችግር በፅናት ለማለፍ በወኔ የተሞላ ምሁራዊ እሳቤውና ጥበቡ ለማንኛውም ችግር መፍትሄ የሚያመጣ ታላቅ ባለራዕይ ነው። ይህንን ሰው አህጉራችን በማጣቷ የተፈጠረውን ክፍተት ሁላችንም ለመሙላት መረባበር አለብን” ነበር ያሉት፡፡ አቶ መለስ አንድ ቢሆኑም እንደ ብዙ ማሰብ፤ እንደ ብዙ መስራት፤ እንደ ብዙ መጣርና ለውጥ ማምጣት የቻሉ ፅኑ መሪ ናቸው። ለዚህም ነው ኢትዮዽያውያን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ መሪያቸው የልባቸውን ከመናገር ያልተቆጠቡት።

ባለፉት 3 ዓመታት ነፃነቷን የተቀዳጀችው ደቡብ ሱዳን በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ሞት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ያወጀችው የታላቁን መሪ ህልፈት መራር መሆኑን በመገንዘብ ነበር። የአዲሲቷ ሀገር መሪ ሳልቫኪር ማያርዴትም “የወጣትነት ጊዜውን በነፃነት ትግል ያሳለፈው መለስ የታላቋ ሀገር ኢትዮዽያ መሪ ከሆነ በኋላ ባለው ብሩህ አዕምሮ ምክንያት ከፖሊሲ አውጪዎች፤ ከዲፕሎማቶችና ከምሁራን ጋር ለመወያየት ሁሌም ዝግጁ ነው።” ሲሉ አቶ መለስን በአጭር ቋንቋ ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አቶ መለስ በታላላቅ ሀገራት ጉባኤዎች እንዲሳተፍ ይጋበዝ የነበረው የታላቅና ታሪካዊ ሀገር መሪ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የትልቅ ብሩህ አዕምሮ ባለቤት መሆኑና የእርሱ ማለፍ ትልቅ ጉዳት፤ ሁሌም የሚያንገበግብና ቁጭት ውስጥ የሚከት ነው ሲሉም ህልፈታቸው የፈጠረባቸውን የሀዘን ስሜት በምሬት ገለፁ። አቶ መለስን በቅርበት እንደሚያውቋቸው የሚያረጋግጥ እማኝነት የሰጡት ሳልቫኪር “በፍትህ፤ በነፃነት እና በልማት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመጋፈጥ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በምንም መልኩ እጅ የሚሰጥ አይደለም። ችግር በሚፈጠርበት ወቅት በርካቶች ምን ማድረግ አለብን ብለው ግራ ሲጋቡ መለስ በፍጥነት ትክክለኛ የመፍትሄ እርምጃ ያፈልቃል” ሲሉም ሳልቫኪር የአቶ መለስን መፍትሔ አመንጭነት አረጋገጡ፡፡   አዎን! አቶ መለስ በትግል ወቅትና በመሪነት ዘመናቸው ያረጋገጡት ይህንን ነው፡፡ በልማትና በነፃነት ጉዳይ የማይደራደሩና ለምርጫ እንኳን የማያቀርቡ ብልህና ሩቅ አሳቢ መሪና ነበሩ።

የሀገራቸውን ዙሪያ መለስ ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ለበርካታ አመታት በጥናትና ምርምር እየታገዙ ለአዲሲቷ ኢትዮዽያ የሚሆኑ ፖሊሲዎችን፤ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን በማመንጨት ወደ ተግባር አስገብተዋል። ሀገራቸውንና አለምን በተሻለ ለመረዳትም የእድሜ ዘመናቸውን በማንበብና ተማሪ በመሆን ማለፋቸው የተሻለች አለምና ሀገር እንዲኖር ስለሚፈልጉ መሆኑን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቡ ኤምቤኪ ጥልቅ ሀዘናቸውን በገለፁበት ወቅት ተናግረዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሱዛን ራይስ  በተከፋው አንደበታቸው፤ በተስረቅራቂውና ቢደመጥ በማይሰለቸው ለዛቸው መለስ “በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት መሆኑ ህይወቱን በሙሉ ራሱን በማስተማርና በማብቃት ያመጣው እንደሆነና ይህን እውቀቱንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሙሉ ጊዜውን ለሀገሩ ያዋለ ግን ደግሞ ራሱን የማይወድ ለህዝብ የኖረ መሪ” ሰሊ ስለታላቁ መሪ ተናግረዋል፡፡ 

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለአፍሪካ የዋሉት ውለታ ላቅ ያለ ነበር ለዚህም ትልቅ ክብር የነበራቸው መሪ ሲሏቸው፤ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ደግሞ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሙሉ ኃይላቸውን ሲጠቀሙና ሲጥሩ የነበሩ፤ ከሀገራቸው አልፈውም ጠንካራና የተባበረች አፍሪካን ለመፍጠር በታማኝነትና ከልብ በመነጨ ፍቅር በመስራት ምስጋና የተቸራቸው መሪ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተረጋጋችና የበለፀገች አህጉር ለመፍጠር አፍሪካውያን ከእርሳቸው እውቀትና ልምድ ለመቅሰም በተነሱበት ወቅት ማረፋቸው ሀዘናችንን ጥልቅ አድርጎታል ሲሉም ህልፈተ ህይወታቸው ልባቸውን እንደነካው ገልፀው ነበር።

ቶኒ ብሌር፤ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ፤ ኮፊ አናን፤ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፤ የሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት አህመድ መሀመድ፤ አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ፤ የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ኸርነስት ቤይኮሮማን፤ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖልካጋሜ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ የተባበሩት መንግስታት ድረጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪ-ሙን፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ የኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ፤ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን፤ የላይቤሪያዋ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰንና ሌሎች ያልጠቀስኳቸው የሀገራት መሪዎች በአንድ ድምፅና በአንድ ምልከታ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የመጠቀ አስተሳሰብና የሀሳብ ልዕልና መስክረዋል፡፡ ስለ ብሩህ አዕምሯቸው፤ ፓን አፍሪካኒስትነታቸው፤ ለሚሰነዘሩ ጥያቄዎች የሚሰጧቸው አጥጋቢና አሳማኝ መልሶቻቸው፤ አንደበተ ርቱዕነታቸው፤ ሀገራቸውን ከድህነት ለማላቀቅ የተከተሏቸው የልማት መስመሮች፤ ልማትን፤ ሰላምንና ዴሞክራሲን የሁሉም ነገር መነሻም መድረሻም አድርገው መከተላቸው፤ በአየር ንበረት ለውጥ ልዩ ተደራዳሪ ሆነው መቅረባቸው፤ ባለራዕይነታቸው  በቻሉት ሁሉ አገላለፅ ብዙ እጅግ ብዙ ብለዋል። በእርግጥም አቶ መለስ የሀገራት መሪዎች ከገለጿቸው በላይ የእውነት የህዳሴ መሪ ነበሩ። 

የአቶ መለስ ህልፈተ ዜናቸው ከታወጀ በኋላ የአለም አቀፍ በርካታ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች  ከጫፍ ጫፍ ተቀባብለው የዘገቡላቸው በእርግጥም ለህዝብ የኖሩ፤ አደባባይ የወጣ፤ በአይን የሚታይ ሚዛን የሚደፋ አሳማኝ የልማት ስራን እየሰሩ ግን ደግሞ ጉዟቸውን ሳይጨርሱና የአዕምሯቸውን ልቀት ጫፍ ሳይደርሱ፤ የሀገርና ለአለም የሚጠቅመው ማንነታቸው ያለ ጊዜው መገደቡ አስቆጭቷቸዋል።

ታዋቂው ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ፤ሱዳን ትሪቢዩን፤ዘጋርድያን፤ዴይሊ ስታር፤ቢቢሲ፤ዘ ቴሌግራፍ፤ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያን፤ኒውስቫይን፤ቪኦኤ፤ ፋይናንሻል ታይምስ እና ሌሎች በርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ አይረሴውና የህዝብ ልጅ ስለሆኑት መሪያችን በተባ ብዕራቸው፤ በአንደበታቸው፤ በገላጭ የዜና ዘገባቸው፤ በሰበር ዜናቸው፤ በልዩ ፕሮግራሞቻቸውና በትንታኔዎቻቸው ስለ አስደንጋጩና ቀስም ሰባሪው የመሪያችን ህልፈት ለአለም አሰምተዋል።
አለም ኢትዮጵያ ለየት ባለ እውቀትና የአመራር ፍልስፍና ይመራት የነበረውን መሪዋን አጣች አሉ፤ አፍሪካ ተደራዳሪዋን አጣች፤ የላቀ አዕምሮ ባለቤቷን፤ ሀገራቸውን ከእርስ በእርስ ጦርነት ፍርስራሽ አውጥተው በአፍሪካ እጅግ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እንድታሳይ ያደረጉ፤ በህመማቸው ላይ ሆነው እንኳ በግጭት ውሰጥ የሚገኙ ሀገራትን የማሸማገልና የማደራረር ሂደት ያላቋረጡ፤ የፖለቲካ መረጋጋት የፈጠሩ፤ ለአፍሪካ አሳቢ መሪ፤ ለአፍሪካ ራዕይ የቆሙ፤ የምስራቅ አፍሪካ የሰላም አራማጅ ሲሉ አወድሰዋቸዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የበሰሉ የፖለቲካ ሰው፤ ለአፍሪካ ጥብቅና የቆሙ፤ አስገራሚ የማስታወስ ችሎታ የነበራቸው፤ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ምንም አይነት ፈታኝ ጥያቄ ቢቀርብላቸው ፊታቸው ላይ ፈገግታ የማይጠፋባቸው፤ በስራቸው ጠንቃቃና ሰዓታቸውን የማያዛንፉ፤ ራሳቸው ትክክል ነው ባሉት የስነ ልቦና መርህ ያመኑና በዚያው የሚገፉና በቅኝ ግዛት ድሪቶ ስር ሲማቅቁ ከኖሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መካከል ጎላና ለየት ብለው የታዩ መሪ ሲሉ በአራቱ የዓለማችን አቅጣጫዎች የሚገኙ ሚዲያዎች ህልፈታቸውን ለመሪው ካላቸው አድናቆት ጋር ለአለም ህዝቦች አድርሰዋል።

በእርግጥም ታላቁና አርቆ ተመልካቹ መሪ አቶ መለስ አርፈዋል። ለኢትዮዽያውያን በተለይ ለዓለማችን ጭቁንና ድሃ ህዝቦች ደግሞ በአጠቃላይ የሚሆን ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቻቸው ግን አንገታችንን ቀና አድርገን እንሄድ ዘንድ መንገድ ሆኖናል። ታላቁ መሪ የሀገራችህ የህዳሴ መሰረት የሚጣልበት ፅኑ መሰረት በግልፅ አሳይተውንና አስተምረውን አልፈዋል። አዎን ዛሬ በአቶ መለስ ለማመን ከራሳችን በላይ እማኝ የሚሆን ሌላ ማንም የለም። ከስራ ስብዕናቸው እስከ ተምሮ አስተማሪነታቸው ሙሉ የእድሜ ዘመናቸውን ለህዝብና ለሀገራቸው ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ፤ ድህነትን አምርረው በመጥላት በድህነት ላይ የሚደረገው ትግል ከፍ እንዲል ያደረጉ፤ በኢትዮዽያ የነገስታትና መንግስታት ታሪክ ውስጥ የተለየና ለንፅፅር የማይቀርብ ስራን ሰርተው ያለፉ ልዩ  ስብእና  የነበራቸው የቁርጥ ቀን መሪ ነበሩ። ይህ ጎልቶ የወጣው ማንነታቸውም በእኛ በኢትዮጵያውያን፣ በአፍሪካውያንና በመላው ዓለም ህዝብ ዘንድ ሲወሳና ሲዘከር ይኖራል፤ እንርሳው ብንል እንኳን እውነታው በራሱ መንገድ እየተመላለሰ እንዳንረሳው ያስገድዳልና!
          


Wednesday, August 6, 2014

The IGAD-led mediation convened the fifth session of negotiations


PRESS RELEASE  (IGAD)

5 August 2014, Addis Ababa: After six weeks of extensive consultations with the  stakeholders, IGAD member states, and international partners, the IGAD-led  mediation convened the fifth session of negotiations on 4 August 2014. The  stakeholders, including the Government of the Republic of South Sudan and the 
SPLM/A (In Opposition) had repeatedly assured the mediation of their commitment  to the inclusive, multi-stakeholder roundtable peace process and the modalities for  comprehensive talks.

On 5 August 2014, the SPLM/A (In Opposition) failed to attend the peace process for  South Sudan. The mediation renews its call to the SPLM/A (In Opposition) to honour  its commitment to resolve the crisis. The mediation expects the SPLM/A (In  Opposition) to immediately return to and fully participate in the multi-stakeholder  negotiations, which will continue on 6 August 2014. The mediation further calls on  the people of South Sudan, IGAD Member States and international partners to urge  the SPLM/A (In Opposition) to return to the ongoing peace talks without further  delay.