የመለሰ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአቶ መለስ ዜናዊን ሌጋሲ ለማስቀጠል ካለው ፋይዳ አንፃር የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው ህዝብ ለአካዳሚው ግንባታ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ሰልጥነው የሚወጡ የአካዳሚው አመራሮችን ውጤታማነት መከታተልና መደገፍ እንደሚገባ አካዳሚው አስታወቀ፡፡
በመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ባልቻ እንደገለፁት የመለስ ራዕይ ህዝብ ከድህነት ወጥቶ ማየት፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን በፅናት መታገል፣ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደርን ማስፈን በአጠቃላይ የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ በመሆኑ ይህንን ራዕይ ለማሳካት አካዳሚው በሚኖረው የአመራር ድርሻ ህዝቡ ከጎኑ ሊመሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የአመራር አካዳሚው የህዝብ ልጅ የሆነውን የመለስን ሌጋሲ ለማስረፅ የሚረዳ በመሆኑ ህዝቡ ከልቡ እየደገፈው እንደሆነ ያወሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በ2005 ዓ.ም ከህዝቡ በተደረገ 85 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ድጋፍ የግንባታውን 60 በመቶ ማጠናቀቅ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
ህዝቡ ለአካዳሚው የሚያደርገው ድጋፍ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ጓድ መለስ ከመሞታቸው በፊት ባዘጋጁት የአመራር ግንባታና የህዳሴ ጉዞ በሚለው ፅሁፋቸው ላይ ኢህአዴግ በየደረጃው ያለው አመራር ሊሰለጥንበት የሚችል የስልጠና ማዕከል ሊኖር እንደሚገባ አቅጣጫ ማሰቀመጣቸውን ያወሱት አቶ ጌታቸው አቶ መለስ በመላው ህዝብና አመራር ዘንድ እየታወሱ እንዲኖሩ ለማድረግ አካዳሚው የሚኖረው ድርሻ የላቀ ነው ብለዋል፡፡
እስካሁን በአካዳሚው በሶስት ዙር ከ12 ሺህ በላይ ጀማሪ አመራሮች መሰልጠናቸው ይታወቃል፡፡

No comments:
Post a Comment