በዝቅተኛ የደመወዝ እርከን ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች 46 በመቶና ለከፍተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ደግሞ የ33 በመቶ ጭማሪ እንደተደረገ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ ገልፀዋል።
በዝቅተኛ የደመወዝ እርከን ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች 46 በመቶና ለከፍተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ደግሞ የ33 በመቶ ጭማሪ እንደተደረገ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ ገልፀዋል።
አቶ ሱፊያን ሐምሌ 26 ቀን 2006 ዓ∙ም በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራሩት ለሰራተኞች የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ በዋጋ ግሽበት ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ አይፈጥርም።
የደመወዝ ጭማሪው ከሀምሌ 2006 ዓ∙ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን ያስታወሱት ሚንስትሩ የተደረገው ማስተካከያ ክፍያ ከነሀሴ ወር ደመወዛቸው ጋር እንደሚከፈላቸው በመግለፅ ጭማሪው በሁሉም የመንግስት እርከን ያሉ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎችን እንደሚያካትት አረጋግጠዋል።
አቶ ሱፍያን እንዳሉት ለዩኒቨርሲቲ መምህራን፥ በጥናትና ምርምር ዘርፍ ለተሰማሩ ተመራማሪዎችና ለህክምና ባለሙያዎች መንግስት ልዩ የደመወዝ ጭማሪ ያደርጋል።
ከመጭው መስከረም ወር ጀምሮ የሰራተኛውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ 420 ዘመናዊ አውቶብሶች ተገዝተው ሀገር ውስጥ መግባታቸውን የገለፁት አቶ ሱፊያን የትራንስፖርት አገልግሎቱ በተደራጀ ሁኔታ ለመምራት ሰራተኞች በስልጠና ላይ ናቸው ብለዋል።
ሚንስትሩ ክለውም የሰራተኛውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ ስራዎች በመስራት ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
የሲቪል ሰርቪስ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ምስራቅ መኮንን በበኩላቸው የአሁኑ የመንግስት የደመወዝ ጭማሪ መነሻ የመንግስት የመክፈል አቅም ከፍ ማለቱ ማሳያ መሆኑን አስታውሰው አጠቃላይ ፈጣን ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ዝቅተኛ ኑሮ የሚኖረው የመንግስት ሰራተኛ ኑሮው እንዲሻሻል ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
የመንግስት ሰራተኛው በሚሰራበት አካባቢ ራሱን በማደራጀት ለኑሮው አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን ማቅረብ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ላይ መሆናቸውንም ዶክተር ምስራቅ ገልፀዋል።
የአሁኑ የደመወዝ ጭማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ∙ም ሀገር አቀፍ የሲቪል ሰርቪስ ቀን ሲከበር መንግስት ለሰራተኛው የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የተደረገ ሲሆን ሀምሌ 25 ቀን 2006 ዓ∙ም የሚንስትሮች ምክር ቤት የደመወዝ ጭማሪውን እንዳፀደቀውም ሂደቱን ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ምንጭ
http://www.eprdf.org.et/web/guest/home/-/asset_publisher/6RcW/content/sivilcervice-empeeloy-salery-increment-news-4-agu-2014
No comments:
Post a Comment