Tuesday, April 28, 2015

የመልካም አስተደዳር ስኬቶችን በማጎልበት ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ ለውጥ የተዘጋጀ ድርጅት - ኢህአዴግ

የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች
ኢህአዴግ መልካም አስተዳደር በሃገራችን ፈጣን ልማት ለማረጋገጥና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደታችንን ለማሳካት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አበክሮ ይገነዘባል። ልማት፣ ሰላም ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ለሃገራችን ህዝቦች ለምርጫ የማይቀርቡ የህልውና ጉዳዮች መሆናቸውንም በፅናት ያምናል። መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥ ልማታችንና ለዴሞክራሲያችን ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አበክሮ ይገነዘባል፡፡ ለዚህም ነው ድርጅታችን ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት ልማት፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደርን አጣምሮ ተግባራዊ በማድረግ የሃገራችንን ገፅታና የዜጐቿን ህይወት በመቀየር ላይ የሚገኘው።
በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የምንገነባው ዴሞክራሲያዊ ስርአት የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን አሟልቶ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ኢህአዴግ በፕሮግራሙ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ መልካም አስተዳደር በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው መርሆዎች ያሉት ሲሆን ዋና ዋናዎቹም የህዝብ ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ የህግ የበላይነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሁም ቀልጣፋነትና ውጤታማነት ናቸው፡፡
በአገራችን እነዚህ መሰረታዊ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ባለፉት ስርአቶች ፈጽመው የማይታሰቡና የተገደቡ ነበሩ፡፡ በነገስታቱ ዘመን በህገ መንግስታቸው ጭምር ነገስታቱን መውቀስም መክሰስም እንደማይቻል የተደነገገበትና “ንጉስ አይከሰሰም ሰማይ አይታረስም” በሚል መርህ የመሪዎች ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ፈጽሞ የማይጠበቅበት ሁኔታ ነበር። በወታደራዊው የአገዛዝ ዘመንም አስተዳዳሪዎችን መቃወም፣ በፈለጉት አግባብ ተደራጅቶ የተለያዩ ሃሳቦችን ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መግለፅ ቀርቶ ልዩነትን ማሰብ በራሱ በጸረ አብዮተኛነት አስፈርጆ ህይወት ያሳጣ ነበር። ይህ ታሪካዊ እውነታ የሚነግረን በነገስታቱም ሆነ በወታደራዊ አምባገነኖቹ የአገዛዝ ዘመን የአገራችን የመልካም አስተዳደር ችግር የጀመረው ዴሞክራሲን በማፈንና በመርገጥ እንደነበር ነው።
በአንፃሩ በኢህአዴግ መሪነት እተገነባ የሚገኘው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርአታችን በሃገራችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በትጋት መስራት የጀመረው የዜጐችን የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስ ነው። በሃገራችን ልዩ ነባራዊ ሁኔታ በእርግጥም የአፈናና ስርአቱ እንደተገረሰሰ ህዝቡ ውስጥ ለዘመናት ሲብላሉ የቆዩትን የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ሳይመለሱ ልማትም ሆነ መልካም አስተዳደር በቅጡ ሊጀመር ይቅርና ሊታሰብ አይችልም ነበር። በዚህ ምክንያት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርአታችን ፈጣኑን ልማትም ሆነ ስለመልካም አስተዳደር ማሰብ የጀመረው ለህዝቦች የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች አስተማማኝ ምላሽ በመስጠት ነው። ይህም በመሆኑ ለመልካም አስተዳደር ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ የሆነው የህዝቦችንና የዜጎችን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ዋስትና የሚሰጥ ህገ መንግስታዊ ስርአት መኖሩ እንዲሟላ አድርጓል፡፡
የተከበራችሁ  የአገራችን ህዝቦች
የህግ የበላይነት የዴሞክራሲያችን አንዱ ምሰሶ መሆኑን በማመን ኢህአዴግ በመስመሩና በፖሊሲዎቹ በግልጽ አስቀምጦ ለተግባራዊነቱ ተረባርቧል፡፡ ያለአግባብ መጠቀም ያለንን ውስን ሃብት ለልማት ለማዋል እንዳንችል እንቅፋት የሚፈጥር መሆኑንና ተጠያቂነት የሚያስከትል አሰራር መከተል እንደሚያስፈልግም ይገነዘባል። በእስካሁኑ ጉዟችን የታዩ የመልካም አስተዳደር ስኬቶችና እጥረቶችን አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን የመልካም አስተዳደር መርሆዎች መሰረት አድርጎ በሚዛኑ መመልከት ጥንካሬዎቻችን አጠናክረን እጥረቶቻችን አርመን ለቀጣይ ለውጥ እንድንተጋ የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ድርጅታችን ኢህአዴግ ከህዝቦቻችን ጋር በመሆን በ24 አመታት ጉዟችን በመልካም አስተዳደር ስኬቶችን ያስመዘገበውን ያህል ገና ያልፈታናቸው እጥረቶች እንዳሉም ይገነዘባል፡፡ እነዚህን የመልካም አስተደዳር ስኬቶችን አጠናክሮ ለመቀጠልም ሆነ እጥረቶችን ለማረም ታዲያ ህዝቡ ወሳኝ ሚና እንዳለውም ኢህአዴግ በጽናት ያምናል፡፡ ያለ ህዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲና ልማት ማምጣት እንደማይቻል እንዲሁም የህዝብ ተጠቃሚነት ያላረጋገጠ ዴሞክራሲና ልማት ዘላቂነት እንደሌለው ኢህአዴግ ከጅምሩ አቋም የወሰደበት ጉዳይ ነው፡፡
የህዝብ ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መልካም አስተዳደር ከሚለካባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢህአዴግ ሁሉም ፖሊሲዎቹ ዋነኛ ማእከል የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሆነው፡፡ በአገራችን ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ከተረጋገጠባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የኢፌዲሪ ህገ መንግስትን የማርቀቅና የማጽደቅ ሂደት ነበር፡፡ የህገ መንግስቱ የማርቀቅና የማጽደቅ ሂደት ካለፉት ስርአቶች ህገ መንግስቶች በእጅጉ በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የህዝቦች ተሳትፎና ባለቤትነት የተረጋገጠበት ነበር፡፡ ሁሉም ህብረተሰብ በየአካባቢው በመሰረታዊ የህገ መንግስቱ ጉዳዮች በቀረቡ አማራጮች ላይ ተወያይቶ ድምጽ እንዲሰጥበት ተደርጓል፡፡ የህዝቡን ፍላጎቶች መሰረት ተደርጎ በተዘጋጀው ረቂቅም ህዝቡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተወካዮቹን መርጦ የህገ መንግስት ጉባኤ ተቋቋሞ ጥልቀት ያለው ውይይት ካደረገ በኋላ ህገ መንግስቱ ጸድቋል፡፡ የአገራችን ህዝቦች በከፍተኛ ተሳትፎና ባለቤትነት ያጸቁት ህገ መንግስት ከሌሎች የዴሞክራሲ አገራት ከተለመደው የውክልና ተሳትፎ በተጨማሪ ቀጥተኛ ተሳትፎንም አካቶ ይዟል። ይህም የሚያሳየው በአገራችን በመገንባት ላይ የሚገኘው ስርአት ከጅምሩ የህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት የተረጋገጠበት መሆኑን ነው፡፡
ኢህአዴግ የህዝብ ተሳትፎ ለእውነተኛ ለውጥ ግብአት የሚሆነው የነቃ፣ ነፃና የተደራጀ ሆኖ ሲፈፀም ብቻ መሆኑን አጥብቆ ያምናል። በመሆኑም ድርጅታችን የህዝቡ ተሳትፎ በነፃ ፍላጐትና ውሳኔ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት በሁሉም ፖሊሲዎቹና ስትራቴጂዎቹ አስቀምጧል። በተግባርም ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት የህዝቡ ተሳትፎ ንቁ፤ ነፃና የተደራጀ እንዲሆን ብዙ ሰርቷል። ይህም በመሆኑ ነው ኢህአዴግና የሚመራው መንግስት ያወጧቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ወደ ተጨባጭ እቅድ በመቀየር ተጨባጭ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው፡፡ ባለፉት 12 አመታት በአገራችን የተመዘገበው ፈጣንና ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኘው የኢኮኖሚ እድገት ከትክክለኛ ፖሊሲና ከከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ውጪ ሊታሰብ እንኳን የሚችል አይደለም።
በገጠር አርሶ አደሩ አካባቢያዊ እውቀቱን፣ ጉልበቱንና የተፈጥሮ ሃብቱን አዋህዶ ጥቅም ላይ በማዋል በግብርና ልማታችን ላይ ታይቶ የማይታወቅ እመርታ አስመዝግቧል። ባለፉት አመታት አርሶ አደሩ በተፋሰስ ልማትና በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ላይ ያፈሰሰው ጉልበትና ያስገኘው ውጤት የሃገራችንን ታሪክ የሚቀይር ተጨባጭ አቅም ሆኗል። ከተሞቻችን አፍርሰን ዳግም የመገንባት ያህል እያካሄድን ባለነው ሁለገብ የልማት ርብርብ ውስጥ የነዋሪዎቹ የገንዘብና የጉልበት አስተዋፅኦ መንግስት ከሚመድበው መዋእለ ነዋይ የማይተናነስ እየሆነ መጥቷል። በገጠርና በከተሞች ባለፈ ታሪካችን ከጥቅም ርቀው የቆዩት ሴቶችና ወጣቶች በሁሉም መስክ በተደራጀ መንገድ እየተሳተፉ የስርአቱ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል።  ባለፉት ጥቂት አመታት ደግሞ በልማት ሰራዊት እና በሌሎች የህዝብ አደረጃጀቶች አማካኝነት በገጠርና በከተማ የህዝቡን የተደራጀ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት አድርገናል። በሂደቱም አመርቂ ውጤት አግኝተናል።
በትክክለኛ ፖሊሲ፣ ብቃት ባለው አመራርና በህዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የተረጂነት ቁጥር በእጅጉ እንዲቀንስ በማድረግ፣ በርካታ ዜጎች ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ወጥተው ሃብት ማፍራት መጀመራቸው እንዲሁም የመሰረት ልማትና የማህበራዊ ልማት ለአብዛኛው ህዝብ ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው፡፡ በእነዚህ አመታት የተገኙ ስኬቶች አገራችን ከነበረችበት አስከፊ ድህነት፣ ኋላቀርነትና የሰላም እጦት አኳያ ሲታይ በቀላሉ የማይታዩና ለወደፊቱም ድህነትን አስወግደን የሁሉም ዜጎች ተጠቃሚነት በሚፈለገው ደረጃ ለማረጋገጥ እንደምንችል ብሩህ ተስፋ የፈነጠቁ ሆነዋል፡፡
ኢህአዴግ የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ በእስካሁኑ ስኬቶች ተኩራርቶና ረክቶ የሚቆም ሳይሆን የህዝቦችን ተጠቃሚነት በተሟላ ሁኔታ ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው ያምናል፡፡ በአገራችን አሁንም ድህነት ሙሉ በሙሉ ያልተወገደ በመሆኑ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች መኖራቸውን፣ አሁንም ስራ ያልያዙ ወጣቶች መኖራቸውን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የማህበራዊ ልማት ጥራቱን ጠብቆ ለሁሉም ያልተዳረሰ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ኢህአዴግና የአገራችን ህዝቦች እነዚህን ችግሮች የመቅረፍ ብቃት እንዳላቸው ያለፉት ስኬቶቻቸው ዋነኛ ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡ የእስካሁኑ ጉዟችን የሚያሳየው አሁንም ጠንክረን ከሰራን የማንፈታው ችግር እንደማይኖርና በድህነት ላይ የጀመርነውን ትግል በድል እንደምንወጣ ያሳያል፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፣
ግልፅነት፣ ተጠያቂነት የህግ የበላይነትና ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት ከህዝቦች ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በተጨማሪ የሚታዩ አለም አቀፍ የጋራ ተቀባይነት ያላቸው የመልካም አስተዳዳር መመዘኛዎች ናቸው። በዚህ ምክንያት ህገ-መንግስታችን የመንግስት አመራርና አሰራር ለህዝቡ ግልፅ እንዲሆን ደንግጓል። በህገ-መንግስቱ መሰረት መንግስት በህዝብ ይጠየቃል። ዜጐች በቀጥታና በምርጫ በሚያደራጇቸው የህዝብ ምክር ቤቶች አማካኝነት መንግስትን ይቆጣጠራሉ።
በድርጅታችን የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የዜጐችንና የመንግስት ግንኙነት በግልፅነትና በተጠያቂነት መርሆዎች ላይ የተመሰረተ እንዲሆን  አበክሮ ሰርቷል። በሃገራችን የመጀመሪያው በህዝብ የተመረጠ መንግስት ስልጣን ከያዘ ከ1987 ጀምሮ ህግ አውጪ፣ ህግ ተርጓሚና አስፈፃሚ በመባል የሚታወቁት ሦስቱ የመንግስት አካላት የየራሳቸውን ህገ-መንግስታዊ ተልእኮ በግልፅነትና በተጠያቂነት መንፈስ መፈፀም በሚችሉበት ሁኔታ ተደራጅተዋል። እነዚህ አካላት በተለይም ደግሞ ከተሃድሶ በኋላ አንዱ ሌላውን በብቃት መደገፍና መቆጣጠር በሚችሉበት መንገድ እንዲጠናከሩ ሆነዋል። ዛሬ በመላ ሃገራችን ከቀበሌ እስከ ፌደራል ፓርላማ በተደራጁ የህዝብ ምክር ቤቶች ውስጥ ከ4 ሚሊዮን የማያንሱ ዜጐች  ይሳተፋሉ። ድርጅታችን በየደረጃው በተደራጁ የህዝብ ም/ቤቶች በተለይም ደግሞ በቀበሌና በወረዳ ምክር ቤቶች ውስጥ የዜጐች ተሳትፎ በዚህ ደረጃ እንዲሰፋ ያደረገው የህዝቡን የመወሰን አቅም ከፍ ለማድረግና በተባበረ አቅም አስፈፃሚውን የመቆጣጠር ጉልበት እንዲኖረው ለማስቻል ነው። በዚህ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ም/ቤቶች የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደቱ የሚመራባቸውን ህጐች ያወጣሉ፣ እቅዶችን በብቃትና በጥራት ለማስፈፀም የሚያስችለውን በጀት ያፀድቃሉ። የህዝቡ የተናጠልና የተደራጀ እንቅስቃሴ የሚመራው ምክር ቤቶቹ በሚያወጧቸው አቅጣጫዎች ነው። አስፈፃሚ አካላት ከላይ እስከታች ለም/ቤቶቹ ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት ያቀርባሉ። በየደረጃው በተደራጁ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ተመድበው የሚያገልግሉ ዳኞች የሚሾሙትና የሚሻሩትም በምክር ቤቶቹ ነው። በዚህ ሳቢያ በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የሁሉም የመንግስት አካላት የበላይና የህዝቡ የሉአላዊነት መገለጫ ሆነው እየሰሩ ናቸው።
በድርጅታችን የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በየደረጃው የተደራጁ የህዝብ ም/ቤቶች በህገ-መንግስታችን የተጣለባቸውን ይህንን ከባድ ሃላፊነት በብቃት ሲወጡ የልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደቱ ተደማሪ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይቀጥላል ብሎ ያምናል። የህዝብ ምክር ቤቶች በሁሉም የመንግስት አካላት ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ሲችሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተቀረፉ እንደሚሄዱም በአፅንኦት ይገነዘባል። ከዚህ በመነሳትም የህዝብ ምክር ቤቶች በአመራር፣ በአደረጃጀትና በአሰራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲጠናከሩና በዕለት ተዕለት አፈፃፀማቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት ሰርቷል። ምክር ቤቶቹ ባለፉት አምስት አመታት አስፈፃሚውን ለመደገፍና ለመቆጣጠር ያሳዩት ተነሳሽነትና የተገኘው ተጨባጭ ውጤት የዚህ ማሳያ ነው።
 የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች
በየትኛውም መንግስት የአመራርና የአሰራር ሂደት ውስጥ የአገልግሎት ቅልጥፍናና ፍትሃዊነትን በማዛባት ስርዓቱንና ህዝቡን ለመልካም አስተዳደር ጉድለትና ለብልሹ አሰራር  ከሚያጋልጡ ችግሮች አንዱ ሙስና ነው። ድርጅታችን እየገነባን ላለነው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ዋነኛ አደጋ በማንኛውም አጋጣሚና የስራ ሂደት ውስጥ እሴት ሳይጨምሩ የመጠቀም ወይም የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር መሆኑን ለይቶ የሞት ሽረት ትግል ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። በተለይም ባለፉት አምስት አመታት ስርአታችንን ለኪራይ ሰብሳቢነት የሚያጋልጡት የስራና የስምሪት መስኮች ተለይተዋል። የገጠርና የከተሞች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፣ የግዢ ስርአታችን እንዲሁም የግብር አስተዳደር እና የንግድና የኮንስትራክሽን ዘርፎች መሆናቸውን ለይቶ ውጤታማ ትግል አካሂዷል። በመሆኑም በከተሞች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዙሪያ የሚታየውን ህገ-ወጥ ወረራና የሙስና ችግር ለመቅረፍ የተዘጋጀው አዲሱ የሊዝ አዋጅ አመርቂ ውጤት አስገኝቷል። በሌሎቹ የስራ ዘርፎች እየተወሰዱ ያሉ ቀጣይነት ያላቸው የማሻሻያ እርምጃዎችም ለውጤት እየበቁ ናቸው።
ሙስናን አስተማማኝ በሆነ መንገድ መዋጋት የሚቻለው በአመራሩና በአጠቃላይ ህዝቡ ዘንድ በሚፈጠር የአስተሳሰብ ለውጥ ነው። ድርጅታችን ሙስናን የልማታችንና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታችን እንቅፋት በማይሆንበት ደረጃ ማስወገድ የሚቻለውም የህዝቡን ሁለገብ ተሳትፎ በማረጋገጥ እንደሆነ ያምናል።  ሙስናን በመከላከል ሂደት የህዝቡን ተሳትፎ አሟልቶ ማረጋገጥ የሚቻለውና ትግሉ ለፍሬ የሚበቃው ደግሞ ሙስናን የሚጠየፍ ህብረተሰብ በመገንባት እንደሆነ አበክሮ ይገነዘባል። ስለሆነም ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት ስራ ላይ በዋለው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በተቀረፀው የስነ-ዜጋና የስነ-ምግባር ትምህርት አማካኝነት በተለይም አገር ተረካቢ በሆኑ ህፃናትና ወጣቶች ላይ ውጤታማ አስተምህሮ ሰርቷል።
በስርአታችን ውስጥ በዚህ መልክ የሚካሄደውን የአስተሳሰብ ትግል እንደተጠበቀ ሆኖ ሙስና ተከስቶ ሲገኝም አጥፊዎችን ለህግ የማቅረብና የማስቀጣት ስራችን የመከላከል ስራውን በሚያግዝ መልኩ እየተፈፀመ ነው። በድርጅታችን የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በሙሰኞች ላይ ጠንካራ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥቦ አያውቅም። በዚህ መንገድ የተወሰዱ ተከታታይ እርምጃዎች በሙስና አማካኝነት የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እየፈታን በልማታዊ መንገድ እንድንቀጥል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።


የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች
ኢህአዴግ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን መርሆዎች ከህዝባዊ አላማዎቹና ከሃገራችን ልዩ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ በስራ ላይ በማዋል ዜጐች የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሌት ከቀን ሰርቷል፤ አሁንም እየሰራ ነው። በሂደቱም እስካሁን በዝርዝር ያየናቸው ውጤቶች በየዘርፉ ተመዝግበዋል። አሁንም በየዘርፉ የተመዘገቡት በጐ ፍፃሜዎቻችን እንደተጠበቁ ሆነው ድርጅታችን በውጤታማ የልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችን ውስጥ እያጋጠሙ ካሉ ፈተናዎች አንዱና ቀዳሚው የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን ይረዳል። ከመሰረተ ልማት አገልግሎት አንፃር የመብራት፣ የውሃ፣ ስልክ እንዲሁም በግብርና በታክስ፣ በመንግስታዊ አግልግሎቶች እና በመሳሰሉት በህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መኖራቸውን ኢህአዴግ ይገነዘባል፡፡
አጠቃላይ የህዝቡ ጥያቄዎች ሲታዩ በአንድ በኩል የልማት ጥያቄ ገጽታ ያላቸውና ካለን አቅም አኳያ ደረጃ በደረጃ መፈታት የሚገባቸው ሲሆኑ በሌላ በኩል ከአመራሩና ከፈጻሚው አካል አግልግሎት አሰጣጥ መጓደል የሚከሰቱ ናቸው፡፡ መንግስት በፌዴራልና በክልሎች ደረጃ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ንቅናቄ በመፍጠር እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እየሰራ ይገኛል። የመልካም አስተዳዳር ችግር ምንጭ ተደርገው የተለዩ ተቋማት ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት የተደራጀ እቅድ እያወጡ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል። አንዳንዶቹ ለውጥ ማምጣት ጀምረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም በብዙዎቹ የህዝብ እርካታ በሚፈለገው ደረጃ አልተረጋገጠም፡፡ ስለሆነም ልማትን በማፋጠን የሚፈቱትን የህዝብ ጥያቄዎች ከህዝቡ ጋር በመወያየት ቅደም ተከተል አውጥቶ መፍትሄ ለመስጠት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ከልማት ጋር የተያያዙ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በየደረጃው ካለው አመራርና ሰራተኛ የአገልጋይነት መንፈስ መጓደልና ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የሚመነጩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ። እነዚህን ችግሮች የግልጸኝነትና የተጠያቂነት አሰራር በማጠናከርና በሂደቱም የህዝቡን የተሟላ ተሳትፎ በማረጋገጥ መፍታት ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን ኢህአዴግ ይገነዘባል። ለዚህም ተግቶ እንደሚሰራ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡
የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተሟላ ሁኔታ የመፍታት ብቃት ያላቸው ኢህአዴግና የአገራችን ህዝቦች መሆናቸው ያለፉት ሁለት አሰርት አመታት ጉዞዎቻችን ያሳያሉ፡፡ ኢሕአዴግ በየጊዜው ከሚያስመዘግባቸው ስኬቶቹ ብቻ ሳይሆኑ ከስህተቶቹም እየተማረ ለድል የበቃ ድርጅት ነው። የአገራችን ተቃዋሚዎች ግን የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ ችግሮችን በፈጠራ ወሬዎች በማጀብ ማራገብ የቀን ተቀን ተግባራቸው ሆኗል፡፡ የአገራችን ህዝቦች በገሃድ የሚያውቁቱን እውነታ ክደው አገራችን ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደገባች አስመስለው ሲስሏት ይታያሉ፡፡ የአገራችን ተቃዋሚዎች ብዙዎቹ ካለፈው ስህተታቸው ሳይማሩ አሁንም በእራሳቸው ውስጣዊ ዴሞክራሲ ማረጋገጥ አቅቷቸው ሲተራመሱ እየዋሉ ለህዝቦች የመልካም አስተዳደር አረጋጋጭ ሆነው ለመቅረብ ይሞክራሉ። ይህም በመሆኑ የአገራችን ተቀዋሚዎች የመልካም አስተዳደር አማራጭ እንደማይሆኑ በቀላሉ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
ህዝባዊ ባህሪ የተላበሰው ኢህአዴግ ሁልጊዜም የውስጥ ድክመቶችን ታግሎ እያረመ አሁን አገራችን ከደረሰችበት ሁለንተናዊ ለውጥ ያደረሰ መሆኑ የአገራችን ህዝቦች የምትገነዘቡት ነው፡፡ ለዚህም ነው የመልካም አስተዳደርን በማረጋገጥ የህዝብ እርካታን አላረጋገጥኩም ብሎ ችግሩን ወደ ውስጡ የሚያየው፡፡ ለዚህም ነው በአገራችን በለውጥ ጎዳና እየተጓዘች ባለችበት በአሁኑ ጊዜ እየታዩ ያሉ ችግሮቹን ሊፈቱ የሚችሉት በኢህአዴግና በአገራችን ህዝቦች የጋራ ትግል ነው የምንለው፡፡   
ኢህአዴግን መምረጥ የህዝቡን ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መልካም አስተዳደር ማስፈን ነው።
ኢህአዴግን ይምረጡ

ምልክታችን ጣፋጩን ማር የምታመርተውን ታታሪዋ ንብ ነች!!

ISIS leader declared 'clinically dead' by Israeli doctors in Golan

An encounter in March allegedly left al-Baghdadi mortally wounded, allowing Abdul Rahman al-Sheijlar, also called Abu Ala Afri to succeed him.

Following reports by Iranian and Iraqi media that Islamic State leader, Abu Bakr al-Baghdadi, had suffered critical injuries in Iraq, unsubstantiated rumors have now surfaced that al-Baghdadi has been declared "clinically dead" by Israeli physicians in the Golan Heights.

Iran's state FARS news, quoting two Iraqi media outlets, claimed that the spiritual and military leader of the self-styled caliphate had been injured in Western Iraq during an assault by Iraqi and Shi'ite forces on March 18 and that he had somehow been transferred to the Israeli Golan Heights, where surgeons and physicians had declared him clinically dead.  
 

However, various claims of how exactly al-Baghdadi was injured last month have rendered the truth elusive.  In March, the British daily, the
 Guardian quoted an Iraqi political adviser, Hisham al-Hashimi, and an unnamed Western diplomat as claiming that  al-Baghdadi suffered life-threatening injuries during a US airstrike in the Nineveh region, close to the Syrian border.

A Pentagon official, Army Colonel Steven Warren, swiftly denied that al-Baghdadi had been the target of any strike, however, telling the Daily Beast that there is "no reason to believe it was Baghdadi" who was hit by the war plane's payload.
 

In any case, the encounter apparently left him mortally wounded and unable to resume his post, a position that has been allegedly filled by a new shady figure, al-Baghdadi's successor, Abdul Rahman al-Sheijlar, also called Abu Ala Afri.

According to al-Hashimi, Afri had been a physics teacher and established academic who had penned multiple publications on topics ranging from science to religion. He had had joined al-Qaida after the American invasion however, an supervised its Iraqi branch, known as al-Qaida in Mesopotamia.

Reports from the Iranian and Iraqi media have also suggested that following the decline in al-Baghdadi's health, infighting and disputes have arisen among various factions in the Islamic State group with the group's Syria branch expressing dissatisfaction with the choice of the new leader.


በኢህአዴግ መሪነት በመሰረተ ልማት የተመዘቡ አንጸባራቂ ስኬቶችን በማስፋት የአገራችንን የህዳሴ ጉዞ አጠናክረን እናስቀጥል

የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች
ኢህአዴግ በአገራችን የመሰረተ ልማት መስፋፋት ለአጠቃላይ አገራዊ ልማት ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ ከግምት በማስገባት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በትጋት እየሰራ ይገኛል።  መሰረተ ልማት በአገራችን አንድ ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ ለመፍጠር፣ የአገራችን ኢኮኖሚ በአለም ተወዳዳሪ እንዲሆን በማድረግና በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት ለማምጣት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ኢህአዴግ በሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲዊ መንግስት ልዩ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ከዛሬ 23 አመት በፊት የአገራችን መሰረተ ልማት ለአብዛኛው ህዝብ ተደራሽ ያልነበረ፣ የነበሩትም በጥገና እጦት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ የደረሱበት ሁኔታ ነበር፡፡ የ24 አመታት ጉዟችን የጀመረው እጅግ ከፍተኛ የሚባል የመሰረተ ልማት ክፍታት ከነበረው አገራዊ ሁኔታ በመሆኑ በዘርፉ ያስመዘገብነው ውጤት የሞት የሽረት ትግል የጠየቀ ነበር፡፡  የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ስራ ከፍተኛ የካፒታል፣ የሰለጠነ የሰው ሃይልና ማሽነሪ የሚጠይቅና በአገራችን እነዚህ ሁኔታዎች ተሟልተው የማይገኙበት መሆኑ ሌላው ፈታኝ ሁኔታ እንደነበር ማንም በቀላሉ የሚገነዘበው እውነታ ነው። የመሰረተ ልማት ስራ በአብዛኛው በግል ባለሃብቱ ሊሞላ ስለማይችል በመንግስት ትክሻ ላይም የወደቀ ነበር፡፡ በኢህአዴግ በሚመራው መንግስት የመሰረተ ልማት ለአጠቃላይ ልማታችን ካለው ቁልፍ ሚና አኳያ የነበሩ ፈታኝ ሁኔታዎችን በጽናት በማለፍ በዘርፉ ተጨባጭ ስኬቶች አስመዝግበዋል፡፡
በመሰረተ ልማት ከተመዘገቡ ስኬቶች መካከል በመንገድና በሌሎች የትራንስፖርት መስኮች የተመዘገበው ተጠቃሽ ነው፡፡ ለትራንስፖርት መሰረተ ልማት የተመዘገበው ስኬት  ኢህአዴግ በእርግጥም ልማትን ለማረጋገጥ ከሰፊው ህዝብ ጋር ሆኖ ሌት ተቀን የሚተጋ፣ ድህነትና ኋላቀርነትን ታሪክ ለማድረግ የቆረጠ እንደሆነ ማሳያ ተደርጎ የሚቀርብ ነው። ኢህአዴግ መላ አገሪቱን በትራንስፖርት መረብ በማስተሳሰር አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ በመንገድ፣ በአየር፣ በባቡርና በመርከብ ትራንስፖርት ልማት ዘርፍ አንጸባራቂ ድል አስመዝግቧል።
የመንገድ ግንባታ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም የሚጠይቅ ቢሆንም ዘርፉ ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በመነሳት የኢትዮጵያን የመንገድ አውታር መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር የመገንባት ራዕይ ሰንቆ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በዚህም መሰረት በ1983.ም በመላ ሀገሪቱ 18 81 ኪሎ ሜትር  ብቻ የነበረው የመንገድ  አውታር  በአሁኑ ወቅት በብዙ እጥፍ  አድጎ ከ105 ሺ ኪ.ሜ በላይ ሆኗል። ባለፉት 24 ዓመታት የመንገድ አውታር በአማካይ በዓመት ከ16% በላይ እያደገ መጥቷል፡፡ ያለፉት አራት ዓመታትን ብቻ ለይተን ካየን ደግሞ የአገሪቱ የመንገድ አውታር ከእጥፍ በላይ አድጓል፡፡ 10 ሺ 765 የገጠር ቀበሌዎችን ከዋና መንገዶች ጋር ማገናኘት ተችሏል። በዚህም አርሶ አደሩ ለምርቱ የሚፈልገውን ግብአትም ሆነ የሚያመርተውን ምርት ወደ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችለው ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለታል።
ባለፉት አመታት ከፍተኛ ለውጥ በመመዝገብ ላይ ከሚገኝባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የባቡር ትራንስፖርት ልማት ስራ ነው። ምንም እንኳን አገራችን ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የጀመረች ቢሆንም ዘርፉ በበርካታ ተግዳሮቶች ተተብትቦ ቆይቶ በመጨረሻም ተንገራግጮ ቆሞ ነበር። የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ 2 ሺህ 395 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ለመዘርጋት ታቅዶ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው። የአዲስ አባባ የቀላል ባቡር ፕሮጄክት ከ95 በመቶ በላይ ተጠናቅቆ የፍተሻና ሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ ጂቡቲ መስመር የተጀመረው የባቡር መንገድ ግንባታም በተያዘለት እቅድ እየተፈፀመ ይገኛል። የባቡር መስመር ዝርጋታው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በማቃለል እንዲሁም በኢኮኖሚያችን በተለይ የወጪና የገቢ ንግድ በማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል። የባቡር ልማት ከፍተኛ ካፒታልና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ የባቡር ፕሮጀክቶቻችን እየገጠማቸው ያለውን የፋይናንስ እጥረት ፈተናዎች እየፈታን በመረባረብ ላይ እንገኛለን፡፡ 
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፣
በ24 አመታት ጉዟችን እመርታዊ ለውጥ ከተመዘገበባቸው የመሰረተ ልማት ዘርፎች መካከል የኤሌክትሪክ ሃይል ልማታችን አንዱ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት በማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ የሚዘልቅ ኢኮኖሚ  ለመገንባት፣ የዜጎችን ህይወት ለመቀየርና የአኗኗር ዘይቤአቸውን ለማዘመን፣ በዓለ ገበያ ተዳዳሪ ምርት ለማቅረብና ዘላቂ የኢንዱስሪ ዕገት ለማረጋጥ ያለው ድርሻ የላቀ መሆኑን የሚያምነው ኢህአዴግ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቁርጠኝነት እየፈታ እመርታዊ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ነው።  የኤሌክትሪክ ሃይል ልማታችን የየወቅቱን ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የሀገራችንን ፈጣን ዕድገት ቀጣይነት በሚያረጋግጥ መልኩ ራዕይ የሰንቀ ነው ።
በአገራችን የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረብ ከተጀመረ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ቢቆጠርም እስከ 1983 ዓ.ም በአገራችን የነበረው የሀይል አቅም  ከ370 ሜጋ ዋት ያልበለጠ ነበር። በዚህ ምክንያትም ትንንሽ ከተሞችና ገጠሮች ቀርቶ ለዋና ዋና ከተሞችም ቢሆን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን በተሟላ መልኩ ማቅረብ የማይታሰብ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።  በአሁኑ ወቅት 2 ሺህ 313 ሜጋ ዋት ማመንጨት የተቻለ ሲሆን በያዝነው አመት መጨረሻ ግንባታው የሚጠናቀቀው የጊቤ ሶስት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ኃይል በማመንጨት ከ4 ሺህ በላይ ከፍ ያደርገዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጨምሮ የሌሎች ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲጠናቀቅ አገራችን 10 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት ደረጃ ላይ ትደርሳለች ።
ከሃይል ልማታችን እጅግ ገዝፎ የሚታየው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአይቻልም አስተሳሰብን የሰበረ፣ ታላቁ መሪያችን ጓድ መለስ ዜናዊ እንዳለውም መሃንዲሶቹም፣ ግንበኞችም፣ የፋይናንስ ምንጮችም እራሳችን ሆነን እየገነባነው ያለ የህዳሴያችን ታላቅ ፕሮጀክት ነው። ህዝቡ ከዳር ዳር ተነቃንቆ ለግድቡ ግንባታ አቅሙ የፈቀደውን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ይህም ለሀገራችን በጎ የማያስቡ አካላትን አስደንግጧል። የግድቡ መሰረት ድንጋይ ሲጣል ጀምሮ የማጥላላት ዘመቻ በማድረግ ላይ የሚገኙት የውጭ ሃይሎችና የሀገር ውስጥ ተላላኪዎቻቸው ምን ያህል ከህዝብ ፍላጎት ያፈነገጠ አስተሳሰብ እንዳላቸው ያጋለጠ ታላቅ ፕሮጀክትም ሆኗል።
ከኤሌክትሪክ ሃይል ልማታችን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው የሚያምነው ድርጅታችን ከ1998ዓ.ም. ጀምሮ “የኤሌክትሪክ ኃይል ለሁሉም” በሚል መርሀ የገጠር ኤሌክትሪፌኬሽን ፕሮግራም በመንደፍ ከተወሰኑ ከተሞች ውጪ የማይታሰብ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ለገጠሩ ህዝባችንም እንዲዳረስ በማድረግ ላይ ነው። ፕሮግራሙ ሲጀመር ከ648 ያልበለጡ ተጠቃሚ ከተሞችና ከ17 በመቶ ሽፋን ያልበለጠ የነበረው በአሁኑ ስዓት 5 ሺህ 100 በላይ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ሽፋኑም 54 በመቶ ያህል ለማድረስ ተችሏል።
በኤሌክትሪክ ሃይል ልማት ያስመዘገብናቸው ስኬቶች አልጋ በአልጋ የተገኙ ሳይሆን በርካታ ፈተናዎችንና ችግሮችን ተጋፍጦ በማለፍ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ዘርፉ የሚፈልገው ከፍተኛ ካፒታል አኳያ የፋይናንስ እጥረት ዋነኛው ፈተና ነበር፡፡ የኒዮሊበራል ሃይሉ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቻችን የውጭ ብድር እንዳያገኙ ባደረገበትና በእራሳችን አቅም የገነባናቸው ከመሆኑ አኳያ ሲታይ ኢህአዴግ እና የሚመራው መንግስት ለልማቱ የሰጡት ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡
በኤሌክትሪክ አገልግሎት በአንድ በኩል ልማቱ ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የልማቱ ተጠቃሚ የመሆን ጥያቄ በሌላ በኩል አገልግሎቱ በተዳረሰባቸው አካባቢዎች ከሃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ቅሬታዎች እንዳሉ ኢህአዴግ ይገነዘባል፡፡ የህዝቡን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ለመፍታት ልማቱን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ይገነዘባል፡፡ የሃይል መቆራረጡንም በአስተማማኝ መፍታት የሚያስችል እቅድና አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፣
ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ከተንቀሳቀሰባቸው የመሰረተ ልማት መስኮች ሌላው የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ነው፡፡ ዘርፉ የተፋጠነ የንግድ ልውውጥ ለማረጋገጥ ፣ መንግስት የሚሠጣቸውን አገልግሎቶች ቀልጣፋ ለማድረግና የመንግስትን አሰራር ግልጽ ለማድረግ የሚጫወተው ሚናም የጎላ ነው፡፡ ወጣቶች፣ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ዘመናዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ለራሳቸውና ለሀገራቸው አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ያስችላል፡፡ በአጠቃላይ የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለልማታዊና ዲሞክራሲ ግባችን መሳካት ከፍተኛ ድርሻ በማበርከት የህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ  መሆኑን በማመን ኢህአዴግ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል፡፡
በ1982 .ም በመላ ሀገሪቱ የነበረው የቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 56 ሺህ 557 ብቻ ነበር። አሁን በተንቀሳቃሽ ስልክ ብቻ 33 ሚሊዮን፣ በመደበኛ ቴሌፎን ደግሞ 820 ሺህ እንዲሁም በዳታና በኢንተርኔት አገልግሎት 8 ሚሊዮን ደንበኞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡  በተመሳሳይ መልኩ ከምንም የተነሳው የገጠር ቴሌኮም  ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡ ይህም የሀገራችን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ከፈጣን ሀገራዊ ዕድገቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ነው።
የውጭ የኒዮሊበራል ሃይሉና የውስጥ ተላላኪዎች መንግስት የቴሌኮም ዘርፉን ወደግል እንዲያዞር ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። አብዛኛዎቹ የአገራችን ተቃዋሚዎችም የቴሌኮም አገልግሎት ለግሉ ዘርፍ እንዲሸጥ አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ የሀገር ውስጥ ባለሀብት አቅም ባልጠነከረበት፣ ዘርፉ የሚጠይቀው መሰረተ ልማት ባልተሟላበት እንዲሁም የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ገና ባልዳበረበት ነባራዊ ሁኔታ ተቃዋሚዎች ይህን መሰል አቋም መያዛቸው ውግንናቸው ከህዝብ ጋር እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ በቂ ማሳያ ነው። መንግስት በልማቱ በመሳተፉ ከፍተኛ የቴሌኮሙዩኒኬሽን መሰረተ ልማት በመዘርጋት በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበው በተለይ ከልማቱ ርቆ የቆየውን የገጠር ህዝብ ጭምር ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለው፡፡
የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነትን በዘላቂነት ማረጋገጥ ማለት የገጠርና የከተማ ህዝባችን  ከሀገሪቱ እድገት ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ የአገራችንን እድገት ቀጣይነት የማረጋገጥ ጉዳይ በመሆኑ ኢህአዴግ የገፀ ምድርና የከርሰ ምድር የውሃ ሃብቶቻችንን በአግባቡ በማልማትና በማጎልበት የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ በቀጣይነት ለማሻሻል በሚያስችል መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አከናውኗል፣ በማከናወን ላይም ይገኛል። የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነትን ለማሳደግ  በተደረገው ጥረት ከፍተኛ ስኬት ተመዝግቧል፡፡ በዘርፉ በተካሄደው ልማት የሴቶችን የስራ ጫና በማቃለል እንዲሁም ዜጎቻችን ከውሃ ወለድ በሽታዎች ጋር ተያይዞ ይገጥም የነበረው የጤና ጠንቅም እየቀነሰ ይገኛል።
ዘርፉ ከነበረበትና አሁን ከደረሰበት አንፃር ሲመዘን ጉልህ የሚባል ስኬት ተመዝግቦበታል፡፡ ሆኖም  ፈጣኑ እድገታችን ሰፊና የማይቋረጥ ፍላጎት የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አሁንም ሰፊና ተከታታይ ስራ የሚፈልግ ዘርፍ ነው፡፡ አሁንም በልማቱ ተጠቃሚ ያልሆኑ ዜጎች ያሉ መሆናቸውና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑትም በከተሞች እየመጣ ካለው ከፍተኛ ልማት ጋር ተያይዞ የአገልግሎት መቆራረጥ የሚያጋጥም መሆኑን በመገንዘብ ችግሩን ለመቅረፍ ርብርብ በመደረግ ላይ ሲሆን ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ 
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፣
ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ስናካሂድ ልማታችን ከጎረቤቶቻችን ጋር የሚኖረውን ትስስርም ከግምት ውስጥ አስገብተናል። የባቡር መስመር ዝርጋታችንን ስናስብ አገራችንን ከጅቡቲ፣ ከደቡብ ሱዳንና ከኬንያ ጋር በማስተሳሰር የወጪና የገቢ ንግዳችንን እንዲያሳልጥና ከአገራት ጋር ያለን ወዳጅነት ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገርን ታሳቢ በማድረግ ነው። የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቻችን ፋይዳ አገራችንን ከብክለት ነፃ የሆነ ሃይል በማምረት ከራሷ አልፋ ለጎረቤቶቿ ሃይል የምታቀርብ ጠንካራ አገር መገንባት ነው። የአውራ መንገዶች ግንባታችን ጎረቤቶቻችን ጋር በየብስ ትራንስፖርት በማስተሳሰር ላይ ይገኛል። አየር መንገዳችን ከአካባቢው አልፎ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ላይ የሚገኝ የአገራችንንና የአህጉራችን ኩራት ሆኗል።
አገራችንን በመሰረተ ልማት ከጎረቤቶቿ ጋር የሚኖራት ትስስር  የሀገራችን ልማት እነሱንም ጭምር የሚጠቅም መሆኑን በተግባር አይተው ከእኛ ጋር አብሮ ማደግን እንዲያልሙ እኛም ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ለቀጣይ ዕድገት ተጨማሪ አቅም እንድናገኝ ያስችለናል። በአገራችንና በቀጣናው ሀገራት መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ፣ ለሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ትኩረት የሚሰጥ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲፈጠርም ያስችላል።
የአገራችን ተቃዋሚዎች ከመሰረተ ልማት ግንባታዎች በተለይም ከቴሌኮምና ከመብራት ጋር በተያያዘ በጊዜያዊነት የሚያጋጥመውን የአገልግሎት መቆራረጥ ችግር እንደ መሰረታዊ የፖሊሲ ችግር አድርገው አጣመው በማቅረብ መንግስት የሚያደርጋቸውን የልማት ስራዎች  ጥላሸት መቀባት የተለመደ ተግባራቸው ሆኗል።  መንግስት ከመሰረተ ልማት ግንባታዎች እጁን እንዲያወጣ ከውጪ አዛዦቻቸው ጋር በመሆን የተለያየ ጫናዎችን ለመፍጠር ይሞክራሉ። የአገራችን ተቃዋሚዎች ህዝቡ በገሃድ የሚያውቃቸውን በመሰረተ ልማት የተመዘገቡ ስኬቶችን ሸምጥጠው ይክዳሉ፡፡ አማራጭ ብለው የሚያቀርቡትም አገራችን የውጭ ሃይሎች መፈንጫ እንድትሆን የሚያደረግና የተጀመረውን ለውጥ ወደኋላ የሚመልስ የውድቀት መንገድ ነው፡፡
ሁሌም ተጠሪነቱና አገልጋይነቱ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ብቻ የሆነው ኢህአዴግ ግን አሁንም በጠራ መስመሩ እየተመራ በስኬት ጎዳና ላይ በመገስገስ ለተሻለ ለውጥና ስኬት እንደሚሰራ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል።
ኢህአዴግ እንደሌሎች ዘርፎች ሁሉ በመሰረተ ልማቱም ረገድ ያሉትንን እጥረቶች ከመላ ህዝባችንን ጋር በመሆን እንደሚፈታቸው እርግጠኛ ነው። በቴሌኮም አገልግሎት ዙሪያ ሲያጋጥም የነበረው መቆራረጥ ከሞላ ጎደል የፈታንበትና አሁንም የሰለጠኑ አገሮች የሚጠቀምበትን በዘርፉ አራተኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ መዘርጋት መጀመራችን ከጊዜያዊ ችግሮች ማዶ ዘላቂ መፍትሄዎችን ቀርጸን የመተግበር ብቃታችንን የሚያሳይ ነው። በመብራት ሃይል መሰረተ ልማት በኩል የሚታየውም የሃይል  መቆራረጥ በህዝባችን ቅሬታ እንደፈጠረ ኢህአዴግ ይገነዘባል። ችግሩን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍታት የሚስችል እቅድ ተዘጋጅቶ  ችግሮችን ለመፈታት የሚያስችል ስራ እየተሰራ ሲሆን ልማቱን በማፋጠን ችግሮቹን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍታት ኢህአዴግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡
ኢህአዴግ በሌሎችም መሰረተ ልማት ስራዎቻችን የሚታዩ የጥራት ጉድለቶችንም በአግባቡ በመረዳት መፍትሄዎችን አስቀምጦ በመረባረብ ላይ ይገኛል። እነዚህ ችግሮች በፈጣኑ እድገታችን ውስጥ የሚጠበቁና አንዳንዶቹም በአፈፃፀም ሂደት የሚፈጠሩ እንጂ የፖሊሲና የአቅጣጫ ችግር እንዳልሆኑ በመረዳት ህዝባችንም ከጎናችን በመሆኑ ችግሮቹ ሙሉ በሙሉ የሚቀረፉበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ኢሕአዴግ ያረጋግጣል።
በመሰረተ ልማት አንጸባራቂ ስኬቶችን ያስመዘገበውንና የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ቁርጠኛ የሆነውን ኢህአዴግን በመምረጥ የህዳሴ ጉዟችን አጠናክረን እናስቀጥል፡፡

ኢህአዴግን ይምረጡ፣ ምልክታችንም ታታሪዋ ጣፋጩን ማርን የምትሰራው ንብ ነች!!

Wednesday, April 22, 2015

በንፁን ዜጎቻችን አሰቃቂ ግድያ የሚነግዱ ቡድኖች ከኢ-ሰብአዊ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ በጋራ እንታገላለን!

እኛ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ISIS በግፍ በተገደሉ ንፁሃን ዜጎቻችን ምክንያት ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል፤ ቀስማችንም ተሰብሯል። ይህንን እኩይ ተግባር ለማውገዝም ነቅለን በመውጣት በመስቀል አደባባይ ተሰባስበን ሀዘናችን ገልፀናል፣ -ሰብአዊ በሆነ ሁናቴ ለተገደሉ ወንድሞቻችን ቤተሰቦችንም መፅናናትን ተመኝተናል፣ አሸባሪዎችና ሽብርተኝነንም በጥብቅ አውግዘናል። በቀጣይም መንግስት በፀረ-ሽብር ትግሉ በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ የበኩላችንን ድርሻ እንደሚንወጣ አረጋግጠናል። ለዘመናት ተቻችለንና ተከባብረን የኖርንና ለወደፊቱን ይህንን አንድነታችን ጠብቀንና አስጠብቀን በምንቀጥለው ወገኖች መካከል ልዩነትና አለመተማመን መንፈስ ለመዝራት የሚራወጡ ፀረ-ንድነት ሃይሎችም በምንም ምክንያት እኛን እንደማይወክሉ በግልፅ መልእክታችንን አስተላልፈናል።
ይሁን እና አንዳንድ ሃይሎች ይህንን አሰቃቂና አሳዛኝ ሁኔታ አላግባብ ተጠቅመው የየራሳቸው ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚያሳዝዝ እና በሚያሳፍር ሁኔታ ሲሯሯጡም በትዕዝብት ተመልክተናል። በመሆኑም በወገኖቻችን -ሰብአዊ ግድያና ለማሰቡ እንኳን በሚሰቀጥጠው የሽብር ጥቃት የሚነግዱና ለመነገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ወገኖች ከድርጊታቸው ቢታቀቡ መልካም ይሆናል። የፖለቲካ ትርፍ ማግኘት የሚፈልግ አካል ከተጎዱት ወገኖች ጎን በመቆም ጥቃት ፈፃሚዎችን ማውገዝና የጉዳቱ ሰለባ የሆኑት ቤተሰቦችን ማፅናናት እንጂ በክፋት መንፈስ ለራስ ርካሽ ትርፍ መሯሯ አይገባውም።
እናም መላ የሀገራችን ዜጎች የእነዚህ ቡድኖች አረሜናዊ ተግባር በፅናት ሊናወግዘውና ከድርጊታች እንዲቆጠቡም በፅናት ልንታገላቸው ይገባል። መንግስትም በሽብርተኝነትና በአክራሪነት ላይ የጀመረውን ትግል ይበልጥ በማጠናከር ምልአተ-ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ በስፋት መንቀሳቀስ ይኖርበታል። በንፁሃን ዜጎቻችን የግፍ ግደያ ላይ ተንተርሰው ተገቢ ያልሆነ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችንም ሃይ ሊላቸው ይገባል።
እግዝአብሔር የእነዚህን ንፁሃን ዜጎቻችን ነፍስ በገነት እንዲያኖርልን እንፀልያለን፣ ለቤተሰቦቻችውንም መፅናናትን እንመኛለን፣ መንግስት በሽብርተኝነት፣ በአክራሪነትና በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ለጀመረው ሁሉን አቀፍ ትግልም በሙሉ ልበ በመደገፍ ከጎኑ እንቆማለን።