Monday, April 20, 2015

ከኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

በትናትናው ዕለት ISIC የተባለው አሸባሪ ቡድን ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን መረጃዎች በተለያዩ የብዙሀን መገናኛዎች መውጣት መጀመራቸውንና መረጃውን ለማጣራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከመንግስት ተገልጻል። 
የተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ አስነዋሪና አረመኔያዊ ድርጊት በመሆኑ መንግስት በምሬት እንደሚያወግዘው መግለፁ ይታወሳል።በአሁኑ ጊዜ የሟቾቹ መስል እየተጣራ ከተለያዩ አካላትም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ መንግስት በንፁሀን ዜጎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት በእጅጉ ማዘኑን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
ቀጣይ መንግስት የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚገለፁ ሲሆን በነገው ዕለትም የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትየሚሰበሰብ ሲሆን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በገፍ ለተገደሉ ዜጎቻችን የ3ቀናት የሀዘን ቀን እንደሚታወጅና በመላው ሀገራችንና በኢትዮጵ ኢንባሲዎች ባንዲራችን ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ውሳኔ ያሳልፋል።
በትናትናው ዕለት እንደተገለፀው መንገስት አስቀድሞ የጀመረውን የፀረ ሽበር ትግል አጠናክሮ የሚቀጥልበት ሲሆን በንጹሀን ላይ የደረሰው የሽብር አደጋ ለአፍታም ቢሆን ከጀመረው ትግል እንደማያዘናጋው ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማረጋገጥ ይወዳል። 
በዚህ አጋጣሚ መላው የሀገራችን ዜጎች በፀረ ሽብር ላይ የከፈትነውን ዘመቻ አጠናክረን እንድንቀጥልበት መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።
በሀገራችን ሰርቶ የመለወጥ ዕድል እየሰፋ በመሆኒና በቀጣይነት በህዝባችን ርብርብ ይበልጥ እየሰፋ የሚሄድ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት ጥበቃ ሊያገኙ በማይችሉበት አቅጣጫ በመሄድ አደጋ ላይ ከሚጥላቸው ህገወጥ ስደት እንዲታቀቡ የሃይማኖት ተቋማትና ቤተሰቦች በዚሁ ላይ ጠንክረው እንዲሰሩ ያሳስባል።

No comments:

Post a Comment