እኛ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ISIS በግፍ በተገደሉ ንፁሃን ዜጎቻችን ምክንያት ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል፤ ቀስማችንም ተሰብሯል። ይህንን እኩይ ተግባር ለማውገዝም ነቅለን በመውጣት በመስቀል አደባባይ ተሰባስበን ሀዘናችን ገልፀናል፣ ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁናቴ ለተገደሉ ወንድሞቻችን ቤተሰቦችንም መፅናናትን ተመኝተናል፣ አሸባሪዎችና ሽብርተኝነንም በጥብቅ አውግዘናል። በቀጣይም መንግስት በፀረ-ሽብር ትግሉ በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ የበኩላችንን ድርሻ እንደሚንወጣ አረጋግጠናል። ለዘመናት ተቻችለንና ተከባብረን የኖርንና ለወደፊቱን ይህንን አንድነታችን ጠብቀንና አስጠብቀን በምንቀጥለው ወገኖች መካከል ልዩነትና አለመተማመን መንፈስ ለመዝራት የሚራወጡ ፀረ-አንድነት ሃይሎችም በምንም ምክንያት እኛን እንደማይወክሉ በግልፅ መልእክታችንን አስተላልፈናል።
ይሁን እና አንዳንድ ሃይሎች ይህንን አሰቃቂና አሳዛኝ ሁኔታ አላግባብ ተጠቅመው የየራሳቸው ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚያሳዝዝ እና በሚያሳፍር ሁኔታ ሲሯሯጡም በትዕዝብት ተመልክተናል። በመሆኑም በወገኖቻችን ኢ-ሰብአዊ ግድያና ለማሰቡ እንኳን በሚሰቀጥጠው የሽብር ጥቃት የሚነግዱና ለመነገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ወገኖች ከድርጊታቸው ቢታቀቡ መልካም ይሆናል። የፖለቲካ ትርፍ ማግኘት የሚፈልግ አካል ከተጎዱት ወገኖች ጎን በመቆም ጥቃት ፈፃሚዎችን ማውገዝና የጉዳቱ ሰለባ የሆኑት ቤተሰቦችን ማፅናናት እንጂ በክፋት መንፈስ ለራስ ርካሽ ትርፍ መሯሯ አይገባውም።
እናም መላ
የሀገራችን ዜጎች የእነዚህ ቡድኖች አረሜናዊ ተግባር በፅናት ሊናወግዘውና ከድርጊታች እንዲቆጠቡም በፅናት ልንታገላቸው ይገባል። መንግስትም በሽብርተኝነትና በአክራሪነት ላይ የጀመረውን ትግል ይበልጥ በማጠናከር ምልአተ-ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ በስፋት መንቀሳቀስ ይኖርበታል። በንፁሃን ዜጎቻችን የግፍ ግደያ ላይ ተንተርሰው ተገቢ ያልሆነ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖችንም ሃይ ሊላቸው ይገባል።
እግዝአብሔር የእነዚህን ንፁሃን ዜጎቻችን ነፍስ በገነት እንዲያኖርልን እንፀልያለን፣ ለቤተሰቦቻችውንም መፅናናትን እንመኛለን፣ መንግስት በሽብርተኝነት፣ በአክራሪነትና በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ለጀመረው ሁሉን አቀፍ ትግልም በሙሉ ልበ በመደገፍ ከጎኑ እንቆማለን።
No comments:
Post a Comment