Tuesday, April 21, 2015

አንዳንድ ሕጋዊና ሕገ ወጥ መንገዶችን እያጣቀሱ በመሄድ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለማወክና ከሚያውኩት ሃይሎች ጋርም እጅና ጓንት ሆነው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች አሸባሪው አይ. ኤስ.አይ. ኤስ ቡድን በንፁሃን ኢትዮያውያን ላይ የወሰደው ዘግናኝና ኢ-ሰብአዊ ግድያ ለርካሽ የፖለቲካ ዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ፍፁም ተቀባይነት የሌለውና ሰብአዊነት የጎደለው ድርጊት ነው። እነዚህ ሃይሎች ኢትዮጵያ የሽብር አደጋ አይመለከታትም፣ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግም አያስፈልጋትም እያሉ ሌት ተቀን እንዳልወተወቱን ሁሉ ዛሬ ላይ ደርሰው የአዞ እንባቸውን ለማሳየት መሞከራቸው እና በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ተንተርሰው የፖለቲካ ትርፍ ለመሸመት መራወጣቸው የሚያሳዝንም የሚያስተዛዝብም ጭምር ነው። እናም መላው የሀገራችን ዜጎች መንግስት በጀመረው የፀረ አሸባርነትና ጸረ ሃይማኖት አክራሪነት ትግል ድርሻችንን በመወጣት የሀገራችንና  የህዝባችን ሰላምና ድህንነት በማረጋገጥ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት በቁርጠኝነት መስራት ይኖርብናል።

No comments:

Post a Comment